የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፲ አዲስ ኣበባ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፳፪ / ፲፱፻፳፰ ዓ.ም የማዕድን ( ማሻሻያ ) ኣዋጅ ገጽ ፻፲፯ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፪ / ፲፱፻፳፰ ዓ.ም የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ( ማሻሻያ ) ደንብ ገጽ ፻፲፰ አዋጅ ቁጥር ፳፪ / ፲፱፻፰፰ የማዕድን አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ የማዕድን ሀብት ልማትን ለማስፋፋት የወጣውን አዋጅ ማሻሻል በማስፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ኣዋጅ “ የማዕድን ( ማሻሻያ ) አዋጅ ቁጥር ፳፪ ፲፱፻፷፰ ” | 1. Short Title ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ማሻሻያ የማዕድን አዋጅ ቁጥር ፴፪ / ፲፱፻፳፭ እንደሚከተለው ተሻሽሏል ፤ | 2. Amendment ፩ በአንቀጽ ፴፬ የመጀመሪያ ዐረፍተ ነገር ውስጥ “ እስከ አሥር በመቶ ( ፲ ፐርሰንት ) የሚደርስ አክሲዮን ያለምንም ክፍያ ሊይዝ ይችላል ” የሚለው ሐረግ ተሰርዞ “ ሁለት በመቶ ( ፪ ፐርሰንት ) አክሲዮን ያለምንም ክፍያ ይይዛል ” በሚል ተተክቷል ። ፪ . የአንቀጽ ፴፮ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተተክቷል ፤ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፻፲፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፲፰ ዓም . Federal Negarit Gazeta _No.10-15 February 1996 Page 118 “ ፩ / የብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ለባህላዊ የማዕድን ማምረት ሥራዎችና በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ለሚካሄዱ የኮንስትራክሽን ማዕድናት ፈቃድ የመስጠት ሥልጣን የተሰጠው ሲሆን ፤ ሌሎች ማናቸ ውንም የማዕድን ሥራዎችን በተመለከተ የፍለጋና የምርመራ ፈቃድ ከሆነ ሚኒስቴሩ ፡ ጣምራ ፈቃድና የማዕድን ማምረት ፈቃድ ሲሆን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያ ጸድቀው ደንብ መሠረት ሚኒስቴሩ ፡ ይሰጣል ። ” ፫ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፰፰ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፷፰ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፪ / ፲፱፻፳፰ የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ ደንብን ለማሻሻል የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን \ Duties of the Executive Organs of the Federal Democratic በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፴፯ አንቀጽ ፭ እና በዓለም አቀፍ | Republic of Ethiopia Proclamation No. 4/1995 and Article 4 የተዋሀደ የሸቀጦች አሰያየምና አመዳደብ ሥርዓት ኮንቬንሽን | of the International Convention on the Harmonized Com ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፳፯ / ፲፱፻፴፭ ኣንቀጽ ፬ መሠረት ይህን | modity Description and Coding System Ratification ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ( ማሻሻያ ) ደንብ ቁጥር ፪ / ፲፱፻፳፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ማሻሻያ ከጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ ደንብ ቁጥር ፻፳፪ / ፲፱፻፷፭ ጋር ተያይዞ የሚገኘው የጉምሩክ የዕቃ ቀረጥ ሥርዓትና ተመን ከዚህ ደንብ ጋር ተያይዞ በሚገኘው ሠንጠረዥ ተሻሽሏል ። ፫ : ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ ከጥር ፩ ቀን ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ ።