የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ጽr አዲስ አበባ - - የካቲት ፳ ቀን ፲፱፻፳፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፫፬ ዓ . ም የፍትሐ ብሔር ሕግ ( ማሻሻያ ) አዋጅ . . . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፫፻፱ አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፷፬ የፍትሐ ብሔር ሕግን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ባንኮች ለተለያዩ የንግድና የልማት እንቅስቃሴ የሚሰጧቸው ብድሮችን በተቀላጠፈ መንገድ ለመሰብሰብ እንዲችሉና ከዚህም | amounts , that banks provide for various commercial and አኳያ ለኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፡ ለባንኮች በዋስትና የተያዘ ንብረት እንዲሽጥ ለፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ለማስወሰንና ውሳኔውንም ለማስፈጸም የሚወስደው ጊዜ በጣም ረጅም በመሆኑ ፡ በቁጠባ ሂሣብ መልክ ከሕዝብ የሰበሰቡትን ገንዘብ በማበደር በሚገኘው የወለድ ገቢ በሚተዳደሩ ባንኮች ሥራ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ በማሳደሩ ፡ ለባንክ ብድር መያዣ የተደረጉ ንብረቶችን ሽያጭ በሚመ ለከት የፍትሐ ብሔር ሕግን ማሻሻል በማስፈለጉ ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የፍትሐ ብሔር ሕግ ( ማሻሻያ ) አዋጅ ቁጥር፳፩ | ፲፱፻፳፱ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ 1 5 . 30 ነጋሪት ጋዜጣ ሣቁ ተቪ፩ ገጽ ፫፻ቷ ፌዴራልኝጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፫ የካቲት ፳ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም• Federal Negarit Gazeta - No . 23 27 February 1997 - - Page 360 ፪ . ማሻሻያ በ፲፱፻ሃ፪ የወጣው የፍትሐ ብሔር ሕግ እንደሚከተለው ተሻሽሏል ፡ ፩ በአንቀጽ ፪ሺህ ፰፻፵፩ ሥር ከንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) በኋላ የሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጾች ( ፫ ) ፡ ( ፬ ) ፡ ( ፭ ) እና ( ፮ ተጨምረዋል ፡ “ ፫ ) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) ድንጋጌ ቢኖርም ለባንክ ብድር የተሰጠ መያዣን ለመያዣ ሰጭው ከ፴ ቀናት ያላነሰ ማስጠንቀቂያ በመስጠት በጨረታ ለመሽጥና የባለቤትነት መብቱን ለገዢው ለማስተላለፍ ለአበዳሪው ባንክ ሥልጣን የሚሰጥ ስምምነት ተፈጻሚነት ይኖረዋል ። ፬ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) መሠረት በአበዳሪው ባንክ የተደረገ ሽያጭ መያዣ ሰጭውን በመወከል እንደተፈጸመ ይቆጠራል ። ፭ ) ባንኩ መያዣውን የመሸጥ ሥልጣኑን በሥራ ላይ በሚያውልበት ጊዜ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ከቁጥር ፫፻፲ ፱፻፵፬ የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደ አግባብነታቸው ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል ። ፮ ) ባንኩ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተጠቀሱትን አግባብነት ያላቸውን የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ሳይከተል ሽያጩን በመፈጸሙ በመያዝ ሰጭው ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት በኃላፊነት ተጠያቂ ይሆናል ። ” በአንቀጽ ፪ሺ፰ ሥር ከንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) በኋላ የሚከተሉት | 2 ) The following new sub - Articles ( 3 ) , ( 4 ) , ( 5 ) and ( 6 ) are አዲስ ንዑስ አንቀጾች ( ) ፡ ( ፬ ) ( ፭ ) እና ( ፮ ) ተጨምረዋል ፤ | “ ቦ ) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) ድንጋጌ ቢኖርም ለባንክ ብድር መያዣ የተደረገን የማይንቀ ሳቀስ ንብረት አስቀድሞ ለመያዣ ሰጭው ከ፴ ቀናት ያላነሰ ማስጠንቀቂያ በመስጠት በጨረታ ለመሸጥና የባለቤትነት መብቱን ለገዢው ለማስተላለፍ ለአበ ዳሪው ባንክ ሥልጣን የሚሰጥ ስምምነት ተፈጻሚነት ይኖረዋል ። ፬ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) መሠረት በአበዳሪው ባንክ የተፈጸመ ሽያጭ መያዣ ሰጪውን በመወከል እንደተፈጸመ ይቆጠራል ። ባንኩ መያዣ የተደረገውን የማይንቀሳቀስ ንብረት የመሽጥ ሥልጣኑን በሥራ ላይ በሚያውልበት ጊዜ | በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ከቁጥር ፫፻፲፫ ፬፻፵፱ የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደአግባብነታቸው ተፈጻ ሚነት ይኖራቸዋል ፡ ፡ ባንኩ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተጠቀሱትን አግባብነት ያላቸውን የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ሳይከተል ሽያጩን በመፈጸሙ በመያዣ ሰጭው ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት በኃላፊነት ተጠያቂ ይሆናል ። ” _ ፫ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳ ቀን ፲፱፻፱ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ ኣበባ ፡ የካቲት ፳ ቀን ፲፱፻፰፱ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተመሚያ ቤት ታተመ