×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 208/92 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፴፰ አዲስ አበባ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱የን፪ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር የፒ ህየን፪ ዓ.ም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድ ማቋቋሚያ ገጸ ፩ሺ፫፻፴፰ አዋጅ ቁጥር ፪፻፰ ፲፱፻፲፪ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ወደ ግል ይዞታ የተዛወሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድ ኃላፊነት ወደ አክሲዮን ማኅበርነት የሚለወጡ የልማት ድርጅቶችን የማይተላለፍ ሀብትና ዕዳ መረከብን | include the taking over of residual assets and liabilities of እንዲሁም የሚፈርሱትን የልማት ድርጅቶች ሂሣብ የማጣራት | public enterprises being converted into share companies and ሥራ እንዲጨምር ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፡፡ የባለአደራ ቦርዱ ስያሜ የኃላፊነት ድርሻውን እንዲያንፀባርቅ በማድረግና ሥልጣንና ተግባሩን እንደገና በመወሰን በአዲስ መልክ | responsibilities , its powers and duties are redefined accordin እንዲቋቋም ማደረግ በማስፈለገ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲ ፲፱የን፪ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ : 340 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ዝሺ፩ ገጽ ፩ሺየጫህ ፈዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፰ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም : ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡ ፩ . “ የልማት ድርጅት ” ማለት በአዋጅ ቁጥር ዝጊ ገሀየዝጊ ወይም በአዋጅ ቁጥር ፩፻፵፮ ፲፱፻፲፩ መሠረት ወደ ግል ይዞታ የተዛወረ ወይም ወደ አክሲዮን ማኅበርነት የተለወጠ ወይም በአዋጅ ቁጥር ፳፭ በሀየዝ፬ መሠረት እንዲፈርስ የተወሰነ የመንግሥት የልማት ድርጅት ሲሆን በአዋጅ ቁጥር ፩፻፲ ፱፻፳፯ መሠረት ለቀድሞ ባለቤቱ የተመለሰ የመንግሥት የልማት ድርጅትን ይጨምራል፡ ፪ “ ኤጀንሲ ” ማለት የኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ነው ፡፡ • “ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ” ማለት የመንግሥት የልማት ደርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ነው ። • መቋቋም ፩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድ ከዚህ በኋላ “ ባለአደራ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። የባለአደራ ቦርዱ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የባለአደራ ቦርዱ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። የባለአደራ ቦርዱ ዓላማ፡ ፩ . የልማት ድርጅት ወደ ግል ይዞታ በሚዛወርበት፡ ወደ አክሲዮን ማኅበር በሚለወጥበት ወይም ለቀድሞ ባለቤቱ በሚመለስበት ጊዜ ወደአዲሱ ባለቤት፡ ወደ አክሲዮን ማኅበሩ ወይም ወደ ቀድሞ ባለቤቱ የማይተ ላለፉ ተሰብሳቢ ሂሳቦችን መሰብሰብ፡ ዕዳዎችን መረከብና ከነዚሁ ጋር የተያያዙ የፍርድ ቤት ጉዳዮችን መከታተልና ማስፈጸም፡ እና ፪ . የሚፈርስ የልማት ድርጅትን ሂሳብ ማጣራት፡ ይሆናል ። ሥልጣንና ተግባር ባለአደራ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታ'ል ። ፩ በአዋጅ ቁጥር ፩የዛኔ በህየን፩ መሠረት የሚተላለፉ ለትን የልማት ድርጅት ተሰብሳቢ ሂሳቦችና ዕዳዎችን የሚመለከቱ ሰነዶችን በመረከብ፡ ሀ ) ተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦችን ከሚመለከታቸው ሶስተኛ ወገኖች ጋር ያስታርቃል፡ ለ ) ተሰብሳቢ ሂሳቦችን ይሰበስባል፡ ለመሰብሰብ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፡ ሐ ) ዕዳዎችን ለመንግሥት እያቀረበ እንዲከፈሉ ያደርጋል፡ መ ) ሊሰበሰቡና ሊከፈሉ የማይችሉሂሳቦችን እያጣራ ከመዝገብ እንዲሰረዙ ለመንግሥት ሃሳብ ያቀርባል፡ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሐ ) ድንጋጌ ቢኖርም በፍርድ ቤት የተወሰኑ ወይም በመንግሥት መመሪያ ተለይተው ውክልና የተሰጠባቸውን ዕዳዎች በቀጥታ ይከፍላል ። ግጽ ፩ሸየሣ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፰ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ • ም • ፫ . በአዋጅ ቁጥር ፩፻፵፮ ፲፱፻፵፩ እና በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፭ ) መሠረት የተላለፉለትን የልማት ድርጅት ንብረቶች ስለመንግሥት ንብረት አወጋገድ የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሠረት ያስወግዳል፡ ከተላለፈለት የልማት ድርጅት ሀብትና ዕዳዎች ጋር የተያያዙ የፍርድ ቤትገዳዮችን ይረከባል፡ይከታተላል፡ ክርክሮችን ከፍርድ ቤት ውጭ በስምምነት ሊጨርስ ይችላል፡ ፭ ኤጀንሲው የተጠቀመው የልማት ድርጅት ፕራይቬታ ይዜሽን ስልት የንብረት ሽያጭ ከሆነ እንዲሁም የልማት ድርጅት ለቀድሞ ባለንብረቱ እንዲመለስ በኤጀንሲው ሲወሰን፡ ሀ ) ርክክብ በሚጀመርበት ጊዜ በልማት ድርጅቱ የባንክ ሂሳብ የተቀመጠውና በካዝና የሚገኘው ጥሬ ገንዘብ ለዚሁ ዓላማ ወደተከፈተ ልዩ የባንክ ሂሳብ ገቢ መደረጉን ያረጋግጣል፡ ለ ) ለገዢው ወይም ለቀድሞው ባለንብረት የተላ ለፈው ቋሚና አላቂ ንብረት፡ ጥሬ ዕቃና ምርት በመዝገብ በሚታየው መጠን ለመሆኑ ዝርዝር የማስታረቅ ሥራ ያካሂዳል፡ ሐ ) ርክክብ እስከተፈጸመበት ዕለት ያለውን የሂሳብ ምዝገባና የሂሳብ መዝጋት ሥራ እንዲከናወንና በውጭ ኦዲተር እንዲመረመር ያደርጋል፡ ፮ የልማት ድርጅት በአዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፳፬ አንቀጽ ፴፱ ( ፩ ( ፭ ) በተደነገገው መሠረት እንዲፈርስ ሲወሰን በዚሁ አዋጅ ከአንቀጽ ፴፩ እስከ ፴፭ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት የሂሳብ አጣሪነት ተግባሮችን ያከናውናል ። ጊ ከዚህ አዋጅ ጋር ተያይዞ በሚገኘው ሠንጠረዥ የተመለከቱት የመንግሥት ድርጅቶች ጊዜያዊ ባለአደራ ቦርዶች ያላጠናቀቋ ቸውን ሥራዎች በተቆጣጣሪ ባለሥልጣኑ አረካካ ቢነት ተረክቦ ያጠናቅቃል፡ ፰ የተረከባቸውን የልማት ድርጅት ሰነዶች የልማት ደርጅቱን ሂሳብ የማጣራቱ ሥራ ከተጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ ለአሥር ዓመት ጠብቆ ያቆያል፡ ሰነዶቹን ለማየት የሚፈልጉ ሰዎችም እንዲያዩ ይፈቅዳል፡ ያልተሠራሳቸውን ሰነዶችም አግባብ ባለው መንገድ ያስወግዳል፡ ሀ . ኣስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው አግባብነት ያላቸው ተቋሞች የተወሰኑ ሥራዎችን በውክልና እንዲፈጽሙለት ሊያደርግ እንዲሁም ብቃት ካላቸው አማካሪዎች ጋር ተዋውሎ ሊያሠራ ይችላል፡ ፲ የንብረት ባለቤት ይሆናል፡ ውል ይዋዋላል፡ በስሙ ይከስሳል፡ ይከሰሳል፡ ዓላማውን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባ ሮችን ያከናውናል ። የባለአደራ ቦርዱ አቋም ባለአደራ ቦርዱ፡ የሥራ አመራር ቦርድ፡ ፪ በመንግሥት የሚሾም አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ፡ እና ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች፡ ይኖሩታል ። ፰ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢውን ጨምሮ በመንግሥት የሚሰየሙ አባላት ይኖሩታል፡ ቁጥራቸውም እንደአስፈላ ጊነቱ ይወሰናል ። ገጽ ፭ሺ፫፻፵፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፰ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም ፱ የሥራ አመራር ቦርዱ ሥልጣንና ተግባር የሥራ አመራር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡ ፩ የባለአደራ ቦርዱን ሥራዎች በበላይነትይመራል፡ ይቆጣ ፪ ለመንግሥት የሚቀርቡ የዕዳ ክፍያ ጥያቄዎችን እንዲሁም የተሰብሳቢና የተከፋይ ሂሳቦችን ከመዝገብ የመሠረዝ ሃሳቦችን መርምሮ በአግባቡ ተጣርተው መቅ ረባቸውን ያረጋግጣል፡ I የሚፈርሱ የልማት ድርጅቶችን ሂሳብ የማጣራት ሂደት ሕጋዊ ሥርዓቱን ተከትሎ መፈጸሙን ያረጋግጣል፡ የባለአደራ መዋቅርና የሥራ ፕሮግራም እንዲሁም ለመንግሥት የሚቀርበውን ዓመታዊ በጀትና ሪፖርት ያፀድቃል፡ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ ዓላማ በመከተል የሚዘጋጀውን የባለአደራ ቦርዱ ሠራተኞች የሚተዳደሩበትን መመሪያ ያጸድቃል፡ ለዋናው ሥራ አስኪያጅ ተጠሪ የሆኑትን የባለአደራ ቦርዱን ኃላፊዎች ቅጥርና ምደባ ያጸድቃል፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ] ከተመለከተው ልዩ ፈንድ የተፈቀደ ክፍያ የሚፈጸምበትን ሥርዓት የሚመለከት ዝርዝር መመሪያ ያወጣል፡ የሥራ አመራር ቦርዱ ስብሰባ የሥራ አመራር ቦርዱ በወር አንድ ጊዜ ይሰበሰባል፡ ሆኖም ኣስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሰብሳቢው ጥሪ በማና ቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል ። ፪ ከሥራ አመራር ቦርዱ አባላት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በሰብሰባ ላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። • የሥራ አመራር ቦርዱ ውሳኔ የሚያሳልፈው በድምጽ ብልጫ ይሆናል፡ ሆኖም ድምጽ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ያለበት ወገን ሃሳብ የቦርዱ ውሳኔ ሆኖ ያልፋል ። የዚህ ኣንቀጸ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ የሥራ አመራር ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲፩ የዋናው ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር ዋናው ሥራ አስኪያጅ የባለአደራ ቦርዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ የሥራ አመራር ቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የባለአደራ ቦርዱን ሥራዎች ይመራል፡ ያስተዳድራል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ፡ ዋናው ሥራ አስኪያጅ፡ ሀ ) በቦርዱ ስብሰባዎች በአባልነት ይሳተፋል፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ የተመለከቱትን የባለአደራ ቦርዱን ሥልጣንና ተግባሮች በሥራ ላይ ያውላል፡ ሐ ) የሥራ አመራር ቦርዱ ባጸደቀው የሠራተኞች አስተዳደር መመሪያ መሠረት የባለአደራ ቦርዱን ሠራተኞች ይቀጥራል፡ ያስተዳድራል፡ መ ) የባለአደራ ቦርዱን በጀትና የሥራ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለሥራ አመራር ቦርዱ ያቀርባል፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል፡ ሠ ) ለባለአደራ ቦርዱ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጭ ያደርጋል ፡፡ ረ ) ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉግንኙነቶች ሁሉ ባለአደራ ቦርዱን ይወክላል፡ ሰ ) የባለአደራ ቦርዱን የሥራ አፈጻጸምና የሂሳብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሥራ አመራር ያቀርባል ። ገጽ ፭ሺ፫፻፴፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፰ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ • ም • ዋናው ሥራ አስኪያጅ ለባለአደራ ቦርዱ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለባለአደራ ቦርዱ ኃላፊዎችና ሌሎች ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል፡ ሆኖም እርሱ በማይኖ ርበት ጊዜ ተክቶት የሚሠራው ኃላፊ ከ፴ ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የሚሠራ ከሆነ ውክልናው አስቀድሞ ለሥራ አመራር ቦርዱ ቀርቦ መፈቀድ አለበት ። ፲፪ . በ ጀ ት የባለአደራ ቦርዱ በጀት በመንግሥት ይመደባል ። ልዩ ፈንድ የባለአደራ ቦርዱ ልዩ ፈንድ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፈንዱ የሚከተሉት የገንዘብ ምንጮች ይኖሩታል፡ ሀ ) ከፕራይቬታይዜሽን ገቢ ላይ መንግሥት በሚወ ስነው መቶኛ መሠረት የሚቀነስ ሂሳብ፡ ለ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ( ፩ ) ( ) መሠረት የሚገኝ ተሰብሳቢ ገቢ፡ ሐ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ) መሠረት የሚገኝ የንብረት ሽያጭ ገቢ፡ መ ) በዚህ አዋጅ ኣንቀጽ ፮ ( ፩ ) ( ሀ ) መሠረት የሚተ ላለፍ ገንዘብ፡ ሠ ) እንደአስፈላጊነቱ በመንግሥት ከሚመደብ በጀት ፡፡ ፈንዱ የሚከተሉትን ክፍያዎች ለመፈጸም ጥቅም ላይ ይውላል፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሐ ) እና ( ፪ ) መሠረት የሚፈጸሙ የዕዳ ክፍያዎችን፡ ለ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ) መሠረት ለሚቀጠሩ አማካሪዎች የሚፈጸሙ የአገልግሎት ክፍያ ሐ ) ባለአደራ ቦርዱ ከሚከታተላቸው የፍርድ ቤት ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የፍርድ ቤት ወጪዎችና የጥብቅና አገልግሎት ክፍያዎችን፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ( ፩ ) መሠረት ከሚከናወን ሂሳብ የማጣራት ሥራዎች ጋር የተያያዙ ወጪዎችን ። ፬ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) ( መ ) መሠረት ከፈንዱ ‹ ወጭ ተደርጎ የተፈጸመ ክፍያ የፈረሰው የልማት ድርጅትንብረት ሲሸጥከሚገኘው ገቢ ተቀንሶየሚተካ ይሆናል ። የዚህ ኣዋጅ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሐ ) እና ( ፪ ) ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ፡ ከፈንዱ ላይ የሚደረግ ማናቸውም ክፍያ በባለአደራ ቦርዱ የሥራ አመራር ቦርድ መፈቀድ አለበት ። የፈንዱ ሂሳብ ከባለአደራ ቦርዱ የበጀት ሂሳብ ተለይቶ ይያዛል፡ የተለየ ሪፖርትም ይቀርብበታል ። የሂሳብ መዛግብት ባለአደራ ቦርዱ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ . የባለአደራ ቦርዱ የሂሳብ መዛግብትናገንዘብ ነክ ሰነዶች በየዓመቱ በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይመው ኦዲተር ይመረመራሉ ፡፡ ፲፭ የመተባበር ግዴታ ፩ . የልማት ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድና ማኔጅመንት ባለአደራ ቦርዱ ስለሚረከባቸው የፋይናንስና የሕግ ጉዳዮች ዝርዝር መግለጫ በመስጠት የመተባበር ግዴታ አለባቸው ። ግጽ ፩ሺ፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፰ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ • ም • ፪ . የልማት ድርጅት ኣዲሱ ባለቤት ወይም ኔጅመንት፡ ሀ ) ባለአደራ ቦርዱ በዚህ አዋጅ መሠረት ሊረከባቸው የሚገቡ ሰነዶችና መዝገቦችን እስከሚረከባቸውና እስከሚያነሳቸው ድረስ ባሉበት ቦታና ሁኔታ ተጠብቀው እንዲቆዩ በማድረግ፡ እና ለ ) ለባለአደራ ቦርዱ የተላለፉና ከሠራተኞች የሚፈለጉ ተሰብሳቢዎችን በመሰብሰብ ረገድ የመ ተባበር ግዴታ አለበት ። ፲፮ የተሻረ ሕግ ወደ ግል ይዞታ የተዛወሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፲፯ / ፲፬፻፰፰ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ፲፯ ስለመብትና ግዴታ መተላለፍ በአዋጅ ቁጥር ፲፯ / ፲፱፻፳፰ ተቋቁሞ የነበረው ወደ ግል ይዞታ የተዛወሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድ መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለባለአደራ ቦርዱ -- ተላልፈዋል ። ፲፰ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ ገጽ ፭ሺ፫፻፵፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፫ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም : ሠ ን ጠ ረ ዥ የፈረሱ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጊዜያዊ ባለአደራ የባለአደራ ቦርዱ ስም የኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽኖች ባለአደራ ቦርድ የመንግሥት እርሻዎች ኮርፖሬሽን ባለአደራ ቦርድ የኢትዮጵያችርቻሮ ንግድ ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ድርጅት ባለአደራ ቦርድ የብሔራዊ ሆቴሎች ኮርፖሬሽን ባለአደራ ቦርድ የኢትዮጵያ የመድሃኒትና የሕክምና መገልገያዎች አቅራቢ ኮርፖሬሽን ባለአደራ ቦርድ የማዕድን ሀብት ልማት ኮርፖሬሽን ባለአደራ ቦርድ የጭነት ማመላለሻ ኮርፖሬሽን ባለአደራ ቦርድ የሕዝብ ማመላለሻ ኮርፖሬሽን ባለአደራ ቦርድ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?