የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜ H ል ሰባተኛ ዓመት ቁጥር ፳፯ አዲስ አበባ -ሰኔ ፭ ቀን ፲፱፻፫ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፱ ፲፱፻፶፫ ዓ.ም የፀረ - ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ( ማሻሻያ ) ገጽ ፭ሺ፭፻፲፮ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፱ / ፲፱፻፫ የፀረ - ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ የፀረኀሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ማሻሻል በማስፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የፀረ - ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ( ማሻሻያ ) ኣዋጅ ቁጥር ፪፻፴፱ / ፲፱፻፶፫ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ማሻሻያ በፀረ - ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፮ / ፲፱፻፶፫ በክፍል ሰባት ከአንቀጽ ፶፩ በፊት የሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፲፩ ተጨምሮ ፣ የቀድሞው አንቀጽ ፲፩ ፣ ፲፪ ፣ እና ቸ እንደቅደም ተከተላቸው አንቀጽ ፲፪፡ እና ፲፬ ሆነዋል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፭ሺ፭፻፲፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ ሰኔ ፭ ቀን ፲፱፻፷ ዓ • ም • “ H ፩ ስለምርመራና ስለዋስትና ፩ የሙስና ወንጀልን የሚመለከት የመያዝ ፣ የብርበራ ፡ የቀነ ቀጠሮ ፡ በማረፊያ ቤት የማቆየት ፣ የዕገዳ እና ሌላ ከምርመራ ጋር የተያያዘ ተመሣሣይ ጉዳዩን የሚመለከቱ ማመ ልከቻዎች ወይም ጥያቄዎች የሚታዩት የሙስና ወንጀል ጉዳይን ለማየት ሥልጣን በተሰጠው ፍርድ ቤት ይሆናል ። ፪ . በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘ ሰው የዋስትና መብት አይኖረውም ። ” ፫ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፭ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፭ ቀን ፲፱፻፫ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ