የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እስራ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፭ አዲስ አበባ - ህዳር ፲፭ ቀን ፲፱የህ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የኢንፎርሜሽን ደኅንነት ኤጄንሲ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ .. ገጽ ፫ሺ፪፻፮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፴ / ፲፱፻፳፱ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬፻፸፩ / ፲፱፻፵፰ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ፡፡ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ | Republic of Ethiopia Proclamation No. 47 1/2006 . ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፬ / ፲፱፻ህ " ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ፡፡ ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም ካላሰጠው በስተቀር ፤ ፩ . " ቁልፍ ተቋም " ማለት ለኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አደጋ የተጋለጠና በሚፈጠረው አደጋም በሀገሪቱ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ጥቅሞች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያመጣ የሚችል ተቋም ነው ፧ ፪ . " የኮምፒውተር ደህንነት " ማለት የኮምፒውቲንግ ፕላትፎርም ደህንነት ለማረጋገጥ ከኮምፒውተር አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ስጋቶችን መቆጣጠር ያንዱ ዋጋ ፖ.ሣ.ቁ. ፰ሺ፩ ገጽ ፫ሺ፪፻፲፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፭ ህዳር ፲፭ ፲፱የኝ፱ ፫ . " የኢንፎርሜሽን ሥርዓት " ማለት ኢንፎርሜሽን ለመሰብሰብ ፣ ለመተንተን ፣ ለመጠበቅና ለተጠቃ ሚዎች ለማስተላለፍ የሚያስችል ሥርዓት ነው ፤ ፬ ' የኢንፎርሜሽን ሥርዓት ደህንነት " የኢንፎሜሽን ሥርዓትን ሆን ተብሎ ከታቀደ በስህተት ከሚፈጠር ያልተፈቀደ አጠቃቀም በተከማቸበት ፣ በሚተነተንበት ወይም በሚተላለፍበት ወቅት ከሚከሰት መረጃውን ከሚቀይር እንዲሁም የተፈቀደለት ተጠቃሚ አገልግሎት እንዳያገኝ ከሚያግድ ያልተፈቀደለት አገልግሎት እንዲያገኝ ከሚያደርግ መከላከል ድርጊቱን ለመከታተል ፣ ለመመዝገብና ለመውሰድ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ይጨምራል ፤ ፭ " ኢንፎርሜሽን ሽበራ " ማለት የኢንፎርሜሽን መረብን በመጠቀም ሽብርና አመጽን የመቀስቀስ ተግባር ነው ፤ ፮ . የኢንፎርሜሽን ጦርነት " ማለት ኢንፎሜሽንን ፣ ኢንፎርሜሽንን መሠረት ያደረገ የውሳኔ አሰጣጥ ሃደትን ፣ የኢንፎርሜሽን ሥርዓትና ኮምፒውተር ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገን መረብ ሆን ተብሎ ከሚታቀድ ጥቃት የመከላከልና ኣፀፋዊ ምላሽ የመስጠት ተግባር ነው ፤ ፯ . ' የኢንፎርሜሽን መረብ " ማለት በኢንተርኔት ወይም ኮምፒውተሮችን በማስተሳሰር ኢንፎር የማጓጓዝ የማከማቸትና የማሰራጨት ሥርዓት ነው ፤ “ የኢንፎርሜሽን ደህንነት መንግሥታዊም መንግሥታዊ አካላት የኢንፎርሜሽን መረብ አማካይነት ሊደርስ የሚችል አደጋን የማስወገድ ወይም የመቀነስ ተግባር ነው ፤ ፱ " ኤሌክትሮ ማግኔቲክ ኢነርጂ " ማለት ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ከሆኑ አካላት የሚመነጭ የኒውክሌር ሳይጨምር ለግንኙነት ፣ አሰባሰብና ለኢንፎርሜሽን ውጊያ ጥቅም ላይ የሚውል የጨረር ኃይል ነው ፤ ፲ " ሪሞት ሴንሲንግ " ማለት በሳተላይት ወይም በሌሎች በራሪዎች ላይ በሚገጠም የመረጃ ማሰባሰቢያ አነፍናፊ መሣሪያዎች በመጠቀም የሚካሄድ የኢንፎርሜሽን ኣሰባሰብ ዘዴ ነው ፤ ፲፩ . " ኦፕትሮኒክስ " ማለት የተወሰነ የኤሌክትሮ ማግኔቲክ ኢነርጂ ክልልን በመጠቀም በካሜራ አማካይነት መረጃ የመሰብሰብ ዘዴ ነው ፤ ፲፪ . " ክሪፕቶሎጂ " ማለት የኢንፎርሜሽን ደህንነትና እርግጠኝነትን ለማረጋገጥ ሲባል የሚከናወን የሶፍትዌርና ሀርድዌር ዲዛይንና የኮምፒውተር ቋንቋን የሚመለከት ሃሳባዊ ቀመር ነው ፡፡ ፫ መቋቋም ፩ . የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ( ከዚህ በኋላ " ኤጀንሲ " እየተባለ የሚጠራ ) የህግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ፡፡ ፪ . ኤጀንሲው ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ፡፡ ገጽ ፫ሺ፬፻፵፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ ህዳር ፲፭ ፲፱፻፱ ፬ . ዋና መሥሪያ ቤት የኤጀንሲው ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ፭ ዓላማ የኤጀንሲው ዓላማ ሀገሪቱ የኢንፎርሜሽንና የኢንፎርሜሽን መረብ ቴክኖሎጂንና ቴሌኮሙኒኬሽንን ለብሄራዊ ደህንነቷ ስጋት ሳያስከትል የሰላም ፣ የዲሞክራሲና የልማት መርሃ ግብሮቿን ተግባራዊ ለማድረግ እንድትጠቀምበት ማስቻል ይሆናል ፡፡ ፮ . ሥልጣንና ተግባር ኤጀንሲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፤ ፩ . የኢንፎርሜሽንና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት በሚመለከት መንግሥትን ማማከርና ፖሊሲዎችና ህጎችን አፈጻጸም መከታተል ፤ ፪ . በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነትና የኢንፎርሜሽን ጦርነት ቴክኖሎጂዎች መስክ በጥናትና ምርምር ላይ የተመሠረተ ሀገራዊ አቅም መፍጠርና በዘርፉም የጥናት ፣ የዲቨሎፕመንት ፣ የዲዛይን ፣ የሙከራና ሥራዎችን መንግሥታዊ መሰል ተቋማት ጋር አቀናጅቶ መፈጸም ፤ የኮምፒውተር መረብ ፣ የኢንፎርሜሽን ስርዓትና የኤሌክትሮ ማግኔቲክ አጠቃቀምንና የኢንፎርሜሽን ጦርነትን በሚመለከት የፖሊሲ ፣ የህግ ፣ የዕውቀትና የሌሎች ጉዳዮች ብሔራዊ ቅንጅት የሚፈጠርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ፤ ፬ በሲግናልና ቴክኒካል ኢንፎርሜሽን እንዲሁም በክሪፕቶሎጂ በጥናትና ምርምር ላይ የተመ ለተለያዩ መንግሥታዊ የጸጥታ ተቋማት መስጠት ፤ ኙ የሪሞት ሴንሲንግ ካሜራዎችንና የተለያዩ ማግ ግራቪቲና የኤሌክትሮ ኦፕቲካል አነፍናፊዎችን በመጠቀም የሚደረግ ማንኛውም የዳታ አሰባሰብ ፣ ትንተና ፣ ሥርጭትና ዳታ ባንክ የመገንባት ተግባር ብሔራዊ የመረጃ ደህንነት ደረጃዎችን ጠብቆ መከናወኑን መከታተል ፤ ፮ . በብሔራዊ ደረጃ የክሪፕቶሎጂ ጥናት ፣ ዲዛይንና ዲቨሎፕመንት ሥራዎች በማከናወንና በቴክኖ ሉጂ ሽግግር አማካይነት ብሔራዊ የመረጃ ደህንነት ደረጃዎች መጠበቃቸውን ማረጋገጥ ፤ ፯ . አለም አቀፋዊም ሆነ ሀገራዊ የኢንፎርሜሽን ሥርዓትን በመጠቀም በሀገሪቱ መንግሥታዊ ሥርዓትና ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ የወንጀልና ተግባሮችን መከታተልና በአጥፊዎቹ ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መተባበር ፤ ፰ . በኦፕቶሮኒክስ ፣ በሪሞት ሴንሲንግ ቴክኖሎጂዎችና የአየርና የየብስ ቅኝት ሥርዓቶች ኣማካይነት ከመሬት በላይና በታች አመልካች ዳታዎች ለመሰብሰብ ፣ ለመተንተን ፣ ለማከማ ለማሠራጨት የሚያስችል በጥናትና ምርምር የተደገፈ ስርዓት እንዲኖር ማድረግ ፤ ተቋማትን ኔትወርክ ፣ ሶፍትዌርና ሃርድዌር ቴክኖሎጂ አመራረጥ ፣ የክሪፕቶሎጂ አልጎሪዝም ስታንዳርድ ፣ ኮንፍግሬሽን ፣ አጠቃ ቀምና ደህንነት በሚመለከት በምርምር የታገዘ ገጽ ፫ሺ፪፻፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፭ ህዳር ፲፭ ፲፱፻፱ የቁልፍ ተቋማትን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህን ነት አጠባበቅ ጥንካሬና ተጋላጭነትን ለመለካት የሚያስችል የሪስክ አሰስመንት ጥናትና የሙከራ መሥራትና የእርምት እርምጃዎች እንዲወስዱ ማገዝ ፤ ፲፩ . በመንግሥታዊም ሆነ በግል ተቋማት ሀገራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል ተጋላጭ ጎኖችን ለመከላከል የሚረዳ ከፌደራል የኢንፎርሜሽን ደህንነት ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ የኢንፎርሜሽን ስታንዳርድና ፕሮሲጀር እንዲዘጋጁና እንዲተገበሩ መደገፍ ፤ ፲፪ . የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አጠባበቅ ንቃተ የሚያሳድጉ የትምህርትና ፕሮግራሞች መቅረጽና መስጠት ፤ ፲፫ ወደ ሀገር የሚገቡና ከሀገር የሚወጡ የኢንፎር ኮሙኒኬሽን ፣ ሴንሰሮች ፣ የኢንፎርሜሽን ጦርነትና የክሪፕቶሎጂ ቴክኖሎ ጂዎች ከብሔራዊ ደህንነት አንጻር ሊያስከትሉ የሚችሉትን የመንግሥታዊ የፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መከታተል ፤ ፲፬ ብሔራዊ የኢንፎርሜሽን ደህንነትን በተሟላ መልኩ ለመጠበቅ የሚችል የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት ፤ ፲፭ . ለሚሰጠው ኣገልግሎት ተመጣጣኝ ማስከፈል ፧ ፲፮ የንብረት መዋዋል ፣ በስሙ መከሰስና መክሰስ ፤ ፲፯ . ዓላማውን . ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባሮችን ማከናወን ፡፡ ፯ . የኤጀንሲው አቋም ኤጀንሲው ፣ ፩ . እንዳስፈላጊነቱ በመንግሥት የሚሰየም አማካሪ ፪ . በመንግሥት የሚሾሙ አንድ ዋና ዳይሬክተርና ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ፣ እና ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ፣ ይኖሩታል ፡፡ ፰ . የዋናው ዳይሬክተር ሥልጣንና ተግባር ፩ . ዋናው ዳይሬክተር የኤጀንሲው አስፈጻሚ የኤጀንሲውን ይመራል ፣ ያስተዳድራል ፡፡ ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ዳይሬክተር ፧ ሀ ) በዚህ ፮ የተመለከቱትን የኤጀንሲውን ሥልጣንና ተግባራት በሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ህጎችን መሠረታዊ ዓላማዎች ተከትሎ በመንግሥት በሚፀድቅ መመሪያ መሠረት የኤጀንሲውን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፤ ሐ ) የኤጀንሲውን ፕሮግራምና በጀት ያዘጋጃል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ መ ) ለኤጀንሲው በተሪ ገንዘብ ወጭ ያደርጋል ፤ ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ኤጀንሲውን ይወክላል ፤ ረ ) የኤጀንሲውን አፈጻጸምና አዲስ ኣበባ ታህናዊ ገጽ ፭ሺ፭፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፭ ህዳር ፲፭ ፲፱፻ህ ዋናው ዳይሬክተር ለኤጀንሲው የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ ሥልጣንና ተግባሩን ለኤጀንሲው ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ፡፡ ፬ . በጀት የኤጀንሲው በጀት በመንግሥት ከሚመደብ ገንዘብና በዚህ ደንብ አንቀጽ ፮ ( ፲፭ ) መሠረት ከሚሰበሰብ የአገልግሎት ክፍያ የሚውጣጣ ይሆናል ፡፡ ፲ የሂሣብ መዛግብት ኤጀንሲው የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ፡፡ የኤጀንሲው የሃሳብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በየዓመቱ በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይመው ኦዲተር ይመረመራሉ ፡፡ ፲፩ . ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ በፌዴራል ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ፡፡ • ፮ ቀን ፲፱፻፱ ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር