×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮችምክር ቤትደንብ ቁጥር 16/1989 ዓ.ም የኢትዮጵያ የዕፅዋት ዘር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

* ትሮች ምክር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፴፩ አዲስ አበባ - መጋቢት ፩ ቀን ፲፱፻፳፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፯ / ፲፱፻፵፱ ዓም የኢትዮጵያ የዕፅዋት ዘር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ገጽ ፬፻፱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፮ / ፲፻፰፬ የኢትዮጵያ የዕጽዋት ዘር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ መሠረት የሚከተ ለውን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ የዕፅዋት ዘር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፮ / ፲፱፻፫፱ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም ባልሰጠው በስተቀር በዚህ ደንብ ፣ ፩- “ ምክር ቤት ” ማለት አግባብ ያላቸው መሥሪያ ቤቶች ተወካዮች በአባልነት የሚገኙበት ሥልጣንና ተግባሩ በአዋጅ ቁጥር ፵፯ / ፲፱፻፳፭ ተወስኖ የተሰጠው አካል ፪ • “ ድርጅት ” ማለት ብሔራዊ የዕፅዋት ዘር ኢንዱስትሪ ድርጅት ነው ፤ ፫ “ ዝርያ ” ማለትከሌሎችዝርያዎች በግልጽ የሚለይበት ተወራራሽ የሆነ መለያ ጠባይ ያለው የዕፅዋት ዘር ነው ፤ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፭፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩ መጋቢት ፩ ቀን ፲፱፻፱ ዓም ፬ . “ የተመሠከረለት ዘር ” ማለት በአገር ውስጥ የተመረተ ወይም ወደ አገር ውስጥ የገባ አስፈላጊዎቹን የዘር መስፈርቶች ( ደንቦች ) ማሟላቱን በድርጅቱ ወይም ይህንን ሥራ ለማከናወን በሕግ በተፈቀደለት ሌላ አካል የተረጋገጠለት፡ በቀጥታ ለተጠቃሚዎች ቀርቦ በዘርነት የሚውል ነው ፤ ፭ “ ዘር ” ማለት እውን ዘር፡ አኩራች ድንች ቅጥፍ ተክል ፥ የማሳ ሰብሎችና የጓሮ አትክልት ችግኞች ወይም ለሰብል ማራባት የሚያገለግል የተክል ክፍል ወይም አካል ነው ፤ • “ የተደነገገ ዘር ” ማለት የዚህ ደንብ አንቀጾች ተፈጻሚ የሚሆንበትና ድርጅቱ በሚያወጣው መመሪያ የተወሰነ ዘር ነው ፤ ፯ “ አጽዳቂ ኮሚቴ ” ማለት ብሔራዊ የዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ ነው ፤ ፰ . “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ፤ ፱ . “ የዘር መረጃ ማዕከል ” ማለት የብሔራዊ ዕፅዋት ዘር ኢንዱስትሪ ድርጅት የዘር መረጃ ማዕከል ነው ፤ ፲ “ ንጽሕና ” ማለት በመቶኛ በክብደት ወይም በሌላ መንገድ የተገለጸ ትንታናዊ ንጽሕና ነው ፤ ፲፩ . “ ውግዝ የአረም ዘር ” ማለት በዚህ ደንብ ድንጋጌዎች መሠረት ተለይቶ የታወቀ ልዩ የአረም ብቸኛዝርያ ዘር ማለት ነው ፤ ፲፪ . “ ምልክት ” ማለት ማብራሪያ ' ምስል ወይም ንድፍ ፲፫ . “ ማስታወቂያ ” ማለት በጋዜጣ በስእል፡ በፖስተር በቅርጽ ወይም ቦሌላ ሕትመቶች ሕዝቡ እንዲያ ውቀው የሚቀርብ ነው ፤ “ የዘር ማበጠሪያና ማዘጋጃ ” ማለት የማይፈለጉ ነገሮችን ከዘሩ ውስጥ ለማስወገድ አስፈላጊውን የዘር አቅርቦት ዝግጅቶችን ለማድረግ የሚያገለግል የተከለለ ቦታ ነው ፤ ፲፭ “ ውሱን ዘር ” ማለት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ወይም ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ የተከለከለ ወይም ገደብ የተደ ረገበት ዘር ነው ። ፫ . የተፈጻሚነት ወሰን ፩ ይህ የዕፅዋት ዘር ደንብ ምክር ቤቱ በሚወስነው በማናቸውም የተጠቃሽ ዝርያ የተደነገገ ዘር ላይ ተፈጸ ሚነት ይኖረዋል ። የዚህ ደንብ ድንጋጌዎች በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ በተመረተ ዘርና ከአምራች አርሶ አደር ወደ ሌላ አርሶ አደር በሚሸጥ ዘር ላይ ተፈጻሚ አይሆንም ፡፡ ሆኖም ግን በዘርሽያጭ ሥራ ላይ ለመሠማራት ዘሩን በአስተዋወቀ በማንኛውም አምራች፡ አዘጋጅና አከፋፋይ ላይ የደንቡ ተፈጻሚነት የተጠበቀ ነው ። ፫ ለዘር የሚውሉ ካልሆነ በስተቀር የዚህ ደንብ ድንጋጌ በሌላ ጥቅም በሚውሉ ዕፅዋቶች ተፈጻሚ አይሆንም ። ፬ ዝርያዎችን ስለማጽደቅ፡ ስለመሰየምና ስለመመዝገብ የዚህ ደንብ አንቀጾች እንደተጠበቁ ሆነው የማናቸውም ተክል ብቸኛ ዝርያ አዲስ ዝርያ የሚፀድቀው የሚሰየመው እና የሚመዘገበው ይህ ዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴው ካወጣቸውና ከሚያወጣቸው ዝርዝር ሁኔታዎች ጋር ሲጣጣም ብቻ ነው ። ፭ ስለ ምዝገባና ሥራ ፈቃድ ፩ : ድርጅቱ የተደነገገ ዘር አምራቾች አዘጋጆች አከፋፋ ዮችና ሻጮች የሚመዘገቡበትን መመሪያ ያወጣል ። ጽ ፭፻፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩መጋቢት ፩ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም Federal Negarit Gazeta No. 31 10 March 1997 – Page 501 ፪ በድርጅቱ ካልተመዘገበ በስተቀር ማናቸውም ሰው የተደነገገ ዘር ማምረት ማስመጣት ፡ ማዘጋጀት ፡ ማከፋፈልና የሽያጭ ንግድ ሥራ ላይ መሰማራት አይቻልም ። የተደነገገ ዘር አምራች አስመጪ፡ አዘጋጅ፡ አከፋፋይና ሻጭ ሆኖ ለመመዝገብ ለድርጅቱ የሚቀርብማመልከቻ ለሚሰጠው አገልግሎት የሚከፈለውን ክፍያ ጨምሮ በተወሰነው መሠረት ይሆናል ። ፬ አመልካቹ በዚህ ደንብ አንቀጾች የተጠቀሱትንና ሌሎች ግዴታዎችን ማክበሩን ለማረጋገጥ ድርጅቱ እንደአስፈላጊነቱ በምዝገባ ወቅት በማናቸውም የተደ ነገገ ዘር አምራች አስመጪ ' አዘጋጅ አከፋፋይ ወይም ሻጭ ላይ የተለየ ሁኔታንና ገደብን ሊጥል ይችላል ። እንዲሁም የተወሰነ ዝርያ የሚዘራበትን የመሬት ስፋት በአመልካቹ የሚመረቱትን ዝርያዎች ወቅቱን ክልሉን የቦታውን የመገለል አስፈላጊነት ' ወይም ሌሎች ሁኔታዎች መወሰንን ይጨምራል ። በዚህ አንቀጽ መሠረት የሚደረገው ምዝገባ በደንቡ አንቀጾች መሠረት እስኪሰረዝ ድረስ ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን ክፍያው በተወሰነ መሠረት በየዓመቱ ተግባራዊ ይሆናል ። የምዝገባው ማብቂያ ዘመን ከመድረሱ በፊት ድርጅቱ በቂ በሆነ ምክንያት ሊሠርዝ ወይም በማናቸውም ነገር ላይ ለውጦችን ማድረግ የሚችል ሲሆን በዚህም ጉዳይ ላይ የሚከተሉት ንዑስ አንቀጾች ተፈፃሚነት ይኖራ ሀ ) ድርጅቱ ምዝገባውን ለመሠረዝ ወይም ለውጦች ለማድረግ መፈለጉን ከበቂ ምክንያት ጋር በመግለጽ የአሥራ አራት ቀን የቅድሚያ ማስጠን ቀቂያ በጽሑፍ ለተመዘገበው ሰው ካልሰጠ በስተቀር ምዝገባውን ሊሠርዝ ወይም ለውጦች ሊያደርግ አይችልም ። ለ ) የተደረጉ ለውጦችን ወይም ስረዛን አስመልክቶ የተመዘገበው ሰው በዚህ አንቀጽ ( ሠ ) መሠረት ለደረሰው ማስጠንቀቂያ ቅሬታውን ለድርጅቱ ከገለጸ ድርጅቱ ቅሬታው እንደደረሰው በአሥራ አራት ቀናት ውስጥ ውሳኔውን ለተመዘገበው ሰው በጽሁፍ መስጠት ይኖርበታል ፡፡ የተደነገገ ዘር አምራች ' አስመጭ ፣ አዘጋጅ ፤ አከፋፋይና ሻጭ ሆኖ ለመመዝገብ የቀረበ ማመልከቻ ተቀባይነት ማጣት ድርጅቱን በሚያጠግብ ሁኔታ አስፈላጊውን እርማት አድርጎ በሚቀጥለው ጊዜ ለምዝገባ አዲስ ማመልከቻ ለማቅረብ አመልካቹን አያግደውም ። ፰ የተደነገገ ዘር አምራች አስመጭ አዘጋጅአከፋፋይና ሻጭ ለመሆን የምዝገባ ማመልከቻ ለመቀበል ሲባል ድርጅቱ ወይም እሱ የወከለው ባለሥልጣን በማና ቸውም ተስማሚ በሆነ ጊዜ አመልካቹ ለማምረትና ለንግድ የሚጠቀምበትን ቦታ፡ መጋዘን ፥ ማከማቻ እና ሌሎች ነገሮችን ተገኝቶ መመርመር ይችላል ። መረጃ ስለመያዝ ማንኛውም የተመዘገበ የተደነገገ ዘር አምራች አስመጭ አዘጋጅ አከፋፋይ እና ሻጭ ፤ ፩ . እያንዳንዱን ማሣያ ያመረተውን ዘር ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባውን ያዘጋጀውን፡ የገዛውና የሸጠውን ዘር በዝርዝር መዝግቦ ይይዛል ፡፡ ፪ . ትንተና የተካሄደባቸውን የተክል ናሙናዎች ይይዛል ። ወይም ገጽ ጆደ፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥርቋቋመጋቢት ፩ ቀን ፲፱ ዓም ፫ . ከላይ በንዑስ አንቀጽ ( ፰ ) እና ( ፱ መሠረት የያዘውን መረጃ በተጠየቀ ጊዜ ለድርጅቱ የዘር መረጃ ማዕከል ወይም ኢንስፔክተር ለቁጥጥር ያቀርባል ። ፮ ስለጥራት ቁጥጥር ፩ የኢትዮጵያደረጃዎችመዳቢ ባለስልጣን የማንኛውንም ተጠቃሽ ዝርያ ዘር የጥራት ደረጃ ይወስናል ። ለዚህ ደንብ ሲባል ድርጅቱ የተወሰነውን የጥራት ደረጃ ተግባራዊ ያደርጋል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት በዘር መርማሪው አማካኝነት ምርመራ ተካሂዶ ማናቸውም የተደነገገ ዘር ከተወሰነው የጥራት ደረጃ ጋር የማይ ጣጣም ሆኖ ሪፖርት የተደረገ ከሆነ ባለቤቱ ወዲያውኑ የተደነገገው ዘር እንዲታከም ወይም እንዲጸዳማድረግ ይኖርበታል ። ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፬መሰረት ማናቸውም የተደነገገ ዘር ከታከመ ወይም ከጸዳ ባለቤቱ የዘር ተቆጣጣሪውን የዘሩን ናሙና ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ምርመራው ማዕከል እንዲልክ ሊጠይቀው ይችላል ። የተደነገገው ዘር በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ መሠረት ከተወሰነው የጥራት ደረጃ ጋር መጣጣሙን የዘር መርማሪው ሪፖርት እስከሚያደርግ ድረስ ባለቤቱ የተደነገገውን ዘር በተጨማሪማሳከም ወይም ማጽዳት ይኖርበታል ። ፩ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ መሠረት ለሚደረገው ተደጋጋሚ የዘር ምርመራ ባለቤቱ ለእያንዳንዱ ለሚደ ረገው ምርመራ የተወሰነውን ክፍያ ይከፍላል ። ፰ መለያ ምልክት ስለማድረግ የዚህ ደንብ አንቀጾች እንደተጠበቁ ሆነው በአንቀጽ ፯ | 8. Labelling መሠረት የተመረመረማናቸውም የተደነገገ ዘርን የሚሸጥና በአንቀጽ ፱ ላይ የተገለጹትን ሁኔታዎች የሚያሟላ ማናቸውም የተመዘገበ የዘር ሻጥ ከታች የተዘረዘሩትን ተግባሮች የመፈጸም ግዴታ አለበት ። ፩ : የሚሸጠው የተደነገገ ዘር በታሸገ መያዣ ከሆነ ሀ ) የአምራቹ ኩባንያ ስምና አርማ ለ ) እንደሁኔታው “ የተመሰከረለት ዘር ” “ ወደ አገር ውስጥ የገባ የተመሰከረለት ዘር ” የሚል ቃል፡ ሐ ) የተደነገገው ዘር የተመረመረበት ቀንና ዓመተ ምህረት ፡ እና መ ) ሌሎችየተወሰኑዝርዝሮችን መያዣው ላይእንዲ ታተም ወይም በተወሰነ መለያ ምልክት ላይ ተጽፈው እንዲለጠፉ ያደርጋል ። ፪ • የተደነገገው ዘር በብዛት የሚሸጥ ከሆነ ሀ ) ምርመራው እንዲከናወን ያደረገው እራሱ ሻጩ ከሆነ ሽያጩ በሚፈጸምበት ጊዜ ምርመራ የተካሄ ደበትን ማዕከል ስምና አድራሻ፡ ምርመራ የተካሄ ደበትን ቀንና ዓም፡ ምርመራው ሲከናወን የተወ ደው ናሙና ከተሽጠው ዘር በከፊል ወይም በሙሉ መሆንና ሌሎች ዝርዝሮችን የያዘ ዝርዝር መግለጫ በጽሑፍ ለገዢው ያቀርባል ። ገጽ ፭፻፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩ መጋቢት ፩ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta - No. 31 10 March 1997 - Page 503 ለ ) ምርመራው እንዲከናወን ያደረገው ሻጩ ካልሆነ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ ( ሀ ) መሠረት ምርመራውን እንዲካሄድ ያደረገው ሰው ያዘጋጀውን መግለጫ ግልባጭ እንዲሁም መግለጫው የተሸጠውን ዘር በሙሉ ወይም በከፊል ይሸፍን እንደሆነ ማረጋገጫ ለገዥው ይሰጣል ። ፱ የዘር ሽያጭን ስለመቆጣጠር ፩ . ማናቸውም ሰው በሥራ ፈቃድ ላይ በተዘረዘሩት ሁኔታዎች መሠረት የሚዘራ የተደነገገ ዘር ለመሸጥ የሚያስችል የዘር ሻጭ የሥራ ፈቃድ ካልኖረው በስተ ቀርማናቸውንም የተደነገገ ዘር ለመሸጥ አይችልም ። ፪ • አመልካቹ የዚህን ደንብ ድንጋጌዎች ወይም በደንቡ መሠረት የሚወጡትን ማናቸውንም አስፈላጊ ነገሮች ማክበሩን ለማረጋገጥ ድርጅቱ እንደአስፈላጊነቱ የሥራ ፈቃድ መስጠትን በተመለከተ የተለያዩ ሁኔታዎችን ሊያስቀምጥ ይችላል ። ፫ . ማንም ሰው ማንኛውንም የተደነገገ ዘር ለመሽጥ፡ ለሺያጭ ለማስቀመጥ፡ ለሺያጭ ለማቅረብ ' በዓይነት ለመለወጥ ፥ ለማቅረብ የሚችለው ፣ ሀ ) የተባለው ዘር የተጠቃሹዝርያ ለመሆኑ ሲረጋገጥ ለ ) በዚህ ደንብ በተወሰነው መሠረት የተወሰደው የዘሩ ናሙና በታወቀ የዘር መመርመሪያ ጣቢያ የተመረመረ ሲሆን፡ ሐ ) ዘሩ በአንቀጽ ፯ ከተገለጸው የዘር የጥራት ደረጃ ማለትም ከመብቀልና ከንጽህና ዝቅተኛ ገደብና እንዲሁም ከእርጥበቱና ከውጉዝ የአረም ዘር ከፍተኛ መጠን ጋር ተጣጥሞ ሲገኝ መ ) መያዣው በአንቀጽ ፰ በተደነገገው መሠረት ይዘቱ ግልጽ በሆነና በተወሰነው መሠረት ምልክት የተደረገበት ሲሆን ። ፲ ዘርን ስለማረጋገጥ የዚህ ደንብ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፤ ፩ . በኢትዮጵያ ውስጥ የተመረተ ዘር ከሆነ የተመሰከረለት ዘር መሆኑ ፥ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ዘር ከሆነ ፤ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ የተመሰከረለት ዘር መሆኑብድርጅቱ ወይምይኸን ሥራ ለመሥራት በተፈቀደለት ሌላ አካል መረጋገጥ አለበት ። - ፲፩ የውጭ ሀገር የዘር አረጋጋጭ ድርጅቶችን እውቅና ስለመስጠት ለዚህ ደንብ አፈጻጸም ሲባል ድርጅቱ ውጭ ሀገር ለተቋቋሙ ማናቸውም የዘር አረጋጋጭ ድርጅቶች እውቅና ሊሰጥ ይችላል ። ፲፪ የምስክር ወረቀት ስለመስጠት ፩ ማናቸውንም የተጠቃሽ ዝርያን የተደነዝ ዘር የሚሸጥ፡ የሚያስቀምጥ፡ የሚያቀርብ የሚለውጥ ወይም በሌላ አኳኋን የሚያቀርብ ሰው ፤ ሀ ) የተባለውን ዘር የምስክር ወረቀት እንዲኖረው ፍላጎት ካለው የምስክር ወረቀቱን ለማግኘት ለድርጅቱማመልከት ይኖርበታል ፤ ለ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ ( ሀ ) መሠረት የሚቀርበው ማመልከቻ ከተወሰነው ክፍያ ጋር በዝርዝር በተገለጸው መሠረት መቅረብ ይኖር ፪ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ በሚከተለው ሁኔታ ይፈጸማል ገጽ ፭፻፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩'መጋቢት ፩ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ሀ ) በኢትዮጵያ ውስጥ የተመረተ የተደነገገ ዘርን በተመለከተ ፤ ፩ በቅርብ ጊዜ በተዘጋጀ የዝርያ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ ዝርያ መሆኑን ፤ ፪ • የምስክር ወረቀት ከሚሰጣቸው ደረጃዎች ውስጥ መሆኑን ፤ ፫ . በተመዘገበ አምራች የተመረተ መሆኑን ፤ ፬ • በተወሰነው መሠረት መመረቱን ፤ በተወሰነው መሠረት በእርሻ ወቅት ቁጥጥር የተደረገበት መሆኑን ፤ ፮ በዚህ ደንብ ድንጋጌዎች መሠረት የተመ ረመረ መሆኑንና ከአስፈላጊዎቹ የጥራት ደረጃዎች ማለትም ከመብቀልና ከንጽህና ዝቅተኛ ገደብ ፥ ከእርጥበት ከፍተኛ መጠን ጋር የተጣጣመና እንዲሁም የተደነገገ ተጠቃሽ ዝርያን አስመልክቶ የተገለጸውን የዘር አረም ያስወገደ መሆኑን አመልካቹ ለድርጅቱ ያሳያል ። ለ ) ወደ ኢትዮጵያ የገባ የተለየ የተደነገገ ዘርንበተመለከተ ፩ . በተመዘገበ የዘር አስመጪ ወደ ኢትዮጵያ የገባ መሆኑን ፤ ፪ . በዚህ ደንብ አንቀጽ፯እና፰ ድንጋጌዎች መሠረት የተመረመረ መሆኑን ፤ ዘሩ ከመጣበት ሀገር ሕግ መሠረት የተመሰከረለት ዘር ተብሎ የተረጋገጠ ሲሆን ፤ ፬ • በዚህ ደንብ መሠረት የተመሰከረለት ዘር የሚመረ ትበትን ደረጃ በመብለጥ ወይም እኩል በመሆን የተመረተ መሆኑን ፤ ፭ በዕፅዋት ኳራንቲን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፳፭ የተደነገጉ የኳራንቲን መስፈርቶችን ያሟላ መሆኑን ፤ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፬ የተደነገገውን ያሟላ መሆኑን አመልካቹ ለድርጅቱ ያሳያል ። ሐ ) ድርጅቱ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ ( ሀ ) እና ( ላ ስር የተዘረዘሩት ሁኔታዎች በአጥጋቢ ሁኔታ መሟላታ ቸውን ካረጋገጠ በኋላ በወሰነውሁኔታ እና በአዘጋጀው ፎርም እንደሁኔታው ዘሩ ሀገር ውስጥ የተመረተ የተመ ሠከረለት ዘር ወይም ወደ ሀገር ውስጥ የገባ የተመሠከ ረለት ዘር ነው በማለት ሊያረጋግጥ ይችላል ። መ ) ድርጅቱ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ ( ሀ ) እና ( ለ ) መሠረት ማንኛውም ዘር የተመሰከረለት ዘር ነው በማለትካረጋገጠ በኋላ እንደሁኔታው የምስክር ወረቀት በተወሰነው ፎርምና ሁኔታ ለተመዘገበ አምራች ወይም አስመጭ ይሰጣል ። ምሥክር ወረቀትን ስለመሰረዝ ፩ . ድርጅቱ በዚህ ደንብ መሠረት የሰጠውን የምሥክር ወረቀት የሚረሰልኝ መሠረት ሀ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲፪ መሠረት የተሰጠው የምሥክር ወረቀት አስፈላጊ ሁኔታዎችን በተመ ለከተ የማጭበርበር ተግባር በመፈጸም የተገኘ ሲሆን ፤ ወይም ለ ) የምሥክር ወረቀቱ ባለቤት የምሥክር ወረቀቱን ለማግኘት ሲል የገባውን ግዴታ ያለበቂ ምክንያት ያላሟላ ከሆነና የዚህን ደንብ ድንጋጌዎች ወይም በዚህ ደንብ መሠረት የወጡ መመሪያዎችን ጥሶ ሲገኝ ይሆናል ። ገጽ ፭፻፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩መጋቢት ፩ ቀን ፲፱፻ዥ፱ ዓም . Federal Negarit Gazeta - No. 31 10 March 1997 - Page 505 ፪ • ድርጅቱ የምሥክር ወረቀቱን ከመሠረዙ በፊት ለባለቤቱ ጉዳዩን የማስረዳት ዕድል ሊሠጥ ይችላል ። ፫ . ከላይ የተደነገገው ባይኖርም የድርጊቱ ፈጻሚ አግባብ ባለው የወንጀል ድንጋጌ መጠየቁ የተጠበቀ ነው ። ፲፬ . የዘር ምርመራ ማዕከላትን ስለማቋቋምና ለተቋቋሙት ዕውቅና ስለመስጠትና የዘር ተንታኞች ስለመመደብ ፩ ድርጅቱ ከምክር ቤቱ ጋር በመመካከር በተወሰነው መሠረት የተደነገገ ዘር ምርመራ የሚከናወንባቸውን የዘር ምርመራ ማዕከላትን ያቋቁማል፡ የተቋቋሙትን እና / ወይም የሚቋቋሙትን ያውቃል ። ፪ • በተወሰኑት ሁኔታዎች መሠረት የዘር ምርመራ እንዲከ ናወን የዘር ተንታኞች ይመድባል ። ፲፭ የዘር ናሙና ስለመውሰድና ትንተና ስለማካሄድ ጥራቱ ያልተመረመረ የተደነገገ ዘር ያመረተ ወይም የያዘ ማናቸውም ሰው ዘሩን ለመሸጥ ከፈለገ ከመሽጡ | 15. Sampling and Analyses for Seed Testing በፊት በዚህ ደንብ በተወሰነው መሠረት የዘሩን ናሙና በድርጅቱ ለተቋቋመ ወይም ዕውቅና ላገኘ ለዘር ምርመራማዕከል ያቀርባል ። ፪ ከላይእንደተመለከተው የዘር ናሙና ለምርመራ የሚያ ቀርብ ሰው ዘሩ ከየት እንደመጣ ዓይነቱንና ድርጅቱ በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰኑ ሌሎች ዝርዝሮችን ያካተተ መግለጫ ማቅረብ አለበት ። ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ለሚደረገው የተደነገገ ዘር ናሙና ምርመራ አስመርማሪው የተወሰ ነውን ክፍያ የመክፈል ግዴታ አለበት ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የተወሰደው ናሙና በዘር ምርመራ ማዕከል እንደደረሰ የተመደበው የዘር ተንታኝ የተወሰነውን ሥርዓት በመከተል በናሙናው ላይ ምርመራ አካሂዶበት ምርመራው እንዲ ካሄድለትና የምርመራው ውጤት እንዲደርሰው ለፈለገው ሰው የምርመራውን ውጤትና ለሪፖርቱ አስፈላጊ ናቸው የሚላቸውን ሌሎች ዝርዝሮች በመግለጫ ይሰጣል ። ፲፮ ስለዘር ኢንስፔክሽን ፩ . ለዚህ ደንብ አፈጻጸም ሲባል ድርጅቱ ክተር ይመድባል ። ፪ ድርጅቱ ለእያንዳንዱ የዘር ኢንስፔክተር የመቆጣጠር ሥልጣን እንዳለው የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ይሰጣል ። የዘር ኢንስፔክተሩ በዚህ ደንብ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት ቁጥጥሩ የሚካሄድበት ማናቸውም ሰው በጠየቀ ጊዜ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) የተመለከተውን የምስክር ወረቀት ማሳየት አለበት ። የዘር ኢንስፔክተሩ ፤ ሀ ) ዘሩ የተጠቃሽ ዝርያ የተደነገገ ዘር መሆኑን ለመወሰን እንዲቻል፡ ለ ) ተጠቃሹ ዝርያ የተመረተው ከተወሰነው ደረጃ ጋር በተጣጣመ መልኩ መሆኑን፡ ሐ ) የተደነገገው ዘር በዚህ ደንብ መሠረት ከተወ ሰነው የጥራት ደረጃ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ለማረጋገጥ ይችል ዘንድ ምርመራ ለማካሄድ ፡ እና በዚህ ደንብ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አስፈላጊ ነው ብሎ ላመነባቸው ለሌሎች ምክን ያቶች ሁሉ የዘር ወይም የተክል ናሙናዎች ሊወስድ ይችላል ። ገጽ ፭፻፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩ መጋቢት ፩ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. የዘር ኢንስፔክተሩ ደንቡን ለማስፈጸም ሲባል በማና ቸውም ተገቢ በሆነ ሰዓት ይህንን ደንብ በመጣስ የተደነገገ ዘር ንግድ ይካሄድበታል ብሎ በሚያምንበት በማናቸውም መሬት፡ ሕንፃ፡ መኪናእና የዘርማበጠሪያ ውስጥ በመግባት ቁጥጥር አድርጎ ንግዱን ለማካሄድ የሚያስችለውን ፈቃድ ይዞ ማቆየት ይችላል ። ፮ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ፈቃዱን ይዞ ያቆየ የዘር ኢንስፔክተር ፈቃዱ ለተያዘበት ሰው ፈቃዱ መያዙን የሚገልጽና ፊርማው ያለበትን ደረሰኝ ይሰጠዋል ። ፯ . በዚህ አንቀጽንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ላይእንደተመለከተው ኢንስፔክተሩ ፈቃዱን ይዞ ካቆየ በኋላ በአሥራአምስት ቀን ጊዜ ውስጥ አግባብ ላለው ፍርድ ቤት ጉዳዩን ማቅረብ ይኖርበታል ። ፲፯ ዘር ከውጭ ስለማስገባትና ወደውጭ ስለመላክ ፩ የተመዘገበ የዘር አስመጪ ወይም ላኪ ካልሆነ በስተቀር ማናቸውም ሰውየተደነገገ ዘርን ለሽያጭ ወደኢትዮጵያ ለማስገባት ወይም ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ለመላክ አይችልም ። ፪ • ማንኛውም የተመዘገበ የዘር አስመጪ ወይም ላኪ የተደነገገ ዘርን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ወይም ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ለመላክ የሚችለው ሀ ) ዘሩ ውስን ዘር ያልሆነ ሲሆን ለ ) ዘሩ ከመብቀል ዝቅተኛ የጥራት ደረጃ ' ንጽህናና የእርጥበት ከፍተኛ መጠን ጋር የተጣጣመና ወይም የተደነገገ ተጠቃሽ ዝርያን አስመልክቶ የተገለጸን ውጉዝ የዘር አረም ያስወገደ ሲሆን ሐ ) በዚህ ደንብ ድንጋጌዎች መሠረት ዘሩ መለያ ምልክት የተደረገለትና በመያዣ የታሸገ ሲሆን መ ) በዕፅዋት ኳራንቲን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፴፭ የተደነገጉትን የኳራ ንቲን መስፈርቶች አሙዋልቶ ሲገኝ ሠ ) ዘሩ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፬ መሠረት ካፀደቀ ከተሰየመና ከተመዘገበ ዝርያ የተገኘ ሲሆን ' እና ረ ) የዝርያው ስም ከመጣበት አገር የዝርያ መዝገብ ውስጥ የተመዘገበና በማስረከቢያ ቅጽ ወይም በሌላ ሰነድ ላይ የተገለጸ ሆኖ ሲገኝ ነው ። ዘሩን በአስቸኳይወደሀገርውስጥ ለማስገባት ከመፈለግ የተነሳ የዘሩን የምስክር ወረቀት ከመጣበት ሀገር መቀበል ካልተቻለ ወይም ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው ዘር ለምርምር ተግባር የሚውል ከሆነ ወይም በምክር ቤቱ በሚወሰኑ ሌሎች ሁኔታዎች ምክንያት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ ( ረ ) ላይ ከተገለጹት ሁኔታዎች ምክር ቤቱ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባን የተደነገገ ዘር ነፃ ሊያደርግ ይችላል ። ፲፰ ይግባኝ ስለማቅረብ ፩ . በዚህ ደንብ አንቀጽ ፬፡፭፡፲፪፲፫ መሠረት ድርጅቱ በሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ የተሰማው ማንኛውም ሰው ውሳኔው በደረሰው በ፴ ቀናት ውስጥ ሊኖር የሚገባውን ክፍያ በመክፈል ለምክር ቤቱ ወይም እሱ ለመደበው ባለሥልጣን ይግባኝ ማቅረብ ይችላል ። ፪ ይግባኝ ሰሚው ባለሥልጣን ይግባኝ ባዩ በጊዜው ይግባኙን ማቅረብ ያልቻላው በበቂ ምክንያት መሆኑን ከተረዳ የይግባኝጊዜ ገደብ ፴ ቀን ቢያልፍም ይግባኙን ተቀብሎ ማየት ይችላል ። ጅ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽሠረትይባኝለሚው ባለሥልጣን ይባኝ እንዲፈረሰው አቤቱታውን ሰምቶ በተጠነ ሁኔታ ውሳኔይሰጣል ። ፩ በዚህ አንቀጽ መሠረት በይባኝ ሰሚ ባለሥልጣን የተለጠ ማናቸውም ውሳኔ የመጨረሻና ተፈጻሚ ይሆናል ። ፲፬ መመሪያ ስለማውጣት ሀ ) አዲስ ዝርያዎችን የዘር አምራቶችን አስመጪ ዎችንአዘችን፡ የአከፋፋዮች እና የዛፎች ምዝገባ የዘር ጥራት ቁጥጥርን፡ ር ሽያጭን ' የዘር ፖለክር ወረቀትን የዘር ምርመራን እና ዘር ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባትና ወደ ውጭ ለ ) የተደነገገ ዘር አምራች አስመጣ፡ላይ፡አዘጋጅ አከፋፋይና ሻጥ በዚህ ሥራ እንዲሠራ በድርጅቱ የሚሰጠውን የሥራ ፈቃድ ስለማ ውጣት፡ ስለላንስ ፈቃይ እንተ ስለሚቆይበት ጊዜ ስለሚታደሰበትና ስለሚሠረዝበት ዝርዝር ሁኔታ፡እና ሓ ) ሌሎች በደንብ የተካተቱ ጉዳዮችን ለማስፈፀም መመሪያ ሊያመጣ ይችላል ። ፳ ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸውደንቦች ከዚህደንብጋርዮሚቃረኑማናቸውም ደንቦችይህንን ደንብ በሚመለከት ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ። ፳፩ ደንቡ የማወናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፈዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጀምሮ የናይሆናል ። አዲስ አበባ መጋቢት ፩ ፡ ፲፱፻፴፪ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላምተሚያ ቤትታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?