የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስራሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፳፯ አዲስ አበባ ግንቦት ፲፩ ቀን ፲፱፻፵፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፳፭ / ፲፱፻፵፰ የጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ማዕከል ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ .ገጽ ፫ሺ፪፲፬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፳፭ / ፲፱፻፵፰ የጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ማዕከል ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬፻፵፩ / ፲፱፻፵፰ አንቀጽ ፭ መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን ደንብ አውጥቷል ፡፡ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ የጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ኢንዱስትሪ | 1.Short Title ልማት ማዕከል ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፳፭ / ፲፱፻፶፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ ፤ ፩ . “ ሚኒስቴር ” ወይም “ ሚኒስትር ” ማለት እንደ ቅደም ተከተሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው ። ፪ . “ የጨርቃ ጨርቅና ቆዳ ኢንዱስትሪ ” ወይም “ ዘርፍ ” ማለት ውጤቶችን ሁለቱንም አካቶ የያዘ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ነው ፡፡ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣ.ቁ. ፰ሺ፩ ያንዱ ዋጋ ገጽ ፫ሺ፪፻፲፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ ግንቦት ፲፩ ቀን ፲፱፻፲፰ ዓ.ም. ፫ . “ የቅብብሎሽ ሰንሰለት ” ማለት በጨርቃ ጨርቅና በቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ከሚያስፈልጉ የተለያዩ ግብዓቶች እስከ ገበያ መዳረሻ ባለው ማዕቀፍ ውስጥ ተዋናይ የሚሆኑ አካላት የሚኖራቸው የኋልዮሽና የፊትዮሽ ተያያዥነትና ተመጋጋቢነት ፬ . “ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ” ማለት በጨርቃ በቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ያለውን የቅብብሎሽ ሰንሰለት ትስስር በማስፋትና በማጠናከር አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችንና አገልግሎቶችን በአንድ የተማከለ ቦታ ለተጠቃሚዎች በመስጠት ወይም በማሰጠት የዘርፉን ተወዳዳሪነት በማጎልበት ለውጤት እንዲበቁ ማስቻል ነው ፡፡ ፫ . መቋቋም ፩ . የጨርቃ ጨርቅና ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ማዕከል ከዚህ በኋላ “ ማዕከሉ ” ተብሎ የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መስሪያ ቤት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ፡፡ ፪ . ማዕከሉ ተጠሪነቱ ለሚኒስቴሩ ነው ፡፡ ፬ . የማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት የማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ይሆናል ፣ እንደአስፈላጊነቱም ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶችን ማቋቋም ይችላል ፡፡ ፩ . የማዕከሉ ዓላማ የማዕከሉ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ልማት የሚያስፈልጉ ድጋፎችንና ኣገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል አገልግሎት ፅንሰ ሃሳብ መሠረት አሰባስቦ በመስጠት ወይም በማሰጠት የዘርፉን የተወዳዳሪነት አቅም ማጎልበት ነው ፡፡ ፮ . የማዕከሉ ሥልጣንና ተግባር ፩ . በጨርቃ ጨርቅና በቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚሰማሩና የተሰማሩ ባለሀብቶችን ለውጤት | 6. Powers and Duties of the Center ለማብቃት የሚያግዙ የቴክኒክ ድጋፍና ምክር አገልግሎቶች ይሰጣል ፣ በዘርፉ የአመራረትና የንግድ ሥራ ቅብብሎሽ ሰንሰለት ትስስር ማዕቀፍ ውስጥ ተሳታፊ የሚሆኑ አካላትን በመለየት የምርትና የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበትን መንገድ ያመቻቻል ፣ ያስተባብራል ፣ የተፈጠረው ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከር ያደርጋል ፤ ፫ የጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍን ልማት ሊያፋጥኑ የሚችሉ የሴክተር ጥናቶች ያካሂዳል ፣ የረጅም ፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ እቅዶችን ያዘጋጃል ፣ መርሃ - ግብር በመቅረፅ እንዲተገበሩ ያደርጋል ፣ በዘርፉ የተለያዩ የገበያ ጥናቶችን ያካሂዳል ፣ በገ በያ መዳረሻ ጥናቱ መሠረት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ስልቶችን ይነድፋል ፣ ጥናቱንም ውጤት ለተጠቃሚዎች ያሰራጫል ወይም ያሳውቃል የፖሊሲ ሃሳብ ያቀርባል ፣ ፭ . ለጨርቃ ጨርቅና ቆዳ ኢንዱስትሪው ዘርፍ የልማት እንቅስቃሴ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎች ይሰበስባል ፣ ይተነትናል ፣ ያደራጃል ፣ ለተጠቃሚዎች ይሰጣል ወይም እንዲሰራጩ ያደርጋል ፣ ፮ . በጨርቃጨርቅና በቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተ ሰማሩ ወይም የሚሰማሩ አገልግሎትና ድጋፍ ፈላጊዎችንና አገልግሎትና ድጋፍ ሰጪ አካላትን ስርዓት የሚተሳሰሩበትን አሠራር ይዘረጋል ፣ ደረጃ የመረጃ ፍሰት ሊኖር እንዲችል ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ፣ . $ ሆኖ ፣ ገጽ ፫ሺ፪፻፲፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ ግንቦት ፲፩ ቀን ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. ፯ አግባብነት ያለው በዘርፉ የአገልግሉት ፈላጊዎችን በመቀበል በማዕከሉ እንዲሰጥባቸው ያደርጋል ወይም በሌላ አካል እንዲፈጸሙ ያደርጋል ፣ ፰ . በመስኩ ለተሰማሩና ለሚሰማሩ የመንግሥትና የግል የልማት ሃይሉች የእርስ በእርስ ትስስርና ትብብር ለማጠናከር የሚያግዙ የተለያዩ ድጋ ፎችን ይሰጣል ፣ ፱ . የዘርፉን የመንግሥትና የግል የጋራ የምክክር መድረክ እንዲካሄድ ያደርጋል ፣ ያስተባብራል ፣ ይመራል ፣ ፲ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እንዲካሄድ ያደርጋል ፣ ሪፖርትም ያዘጋጃል ፣ ፲፩ . ለሚሰጣቸው የተለያዩ አገልግሎቶች ክፍያ መጠየቅ ይችላል ፣ የጨርቃ ጨርቅና ቆዳ ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ልማት ከማፋጠን አንጻር ከሌሎች መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ መ / ቤቶች በሚሰጠው የሥራ ውክልና መሠረት አግባብነት ያላቸውን ተግባራት ያከናውናል ፣ ፯ . የማዕከሉ አቋም ማዕከሉ ፤ ፩ . በመንግሥት የሚሾም አንድ ዋና ዳይሬክተር እና ፪ . አስፈላጊ ሠራተኞች } ይኖሩታል :: ፰ . የዋናው ዳይሬክተር ሥልጣንና ተግባር ፩ . ዋና ዳይሬክተሩ የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ከሚኒስቴሩ በሚስጠው አጠቃላይ መመሪያ | 8. Powers and Duties of the General Director የማዕከሉን ይመራል ፤ ያስተዳድራል ፡፡ ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ የተመለከተው አጠቃላይ እንደተጠበቀ ዳይሬክተሩ ፣ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፮ የተመለከቱትን የማዕከሉን ሥልጣንና ተግባራት ሥራ ላይ ያውላል ፤ በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ሕግና በመንግስት በሚፈቀድ የደመወዝና ጥቅሞች አወሳሰን መመሪያ መሠረት የማዕከሉን ሠራተኞች ይቀጥ ራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ሐ ) የማዕከሉን የሥራ ፕሮግራምና በጀት አዘ ጋጅቶ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል ፣ ያደርጋል ፤ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙ ነቶች ማዕከሉን ይወክላል ፤ የማዕከሉን የሥራ አፈጻጸምና ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ፣ ፫ . ዋና ዳይሬክተሩ ለማዕከሉ የሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለማዕከሉ ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በው ክልና ሊሰጥ ይችላል ፡፡ “ ጽ ፪ሽ፲፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ ግንቦት ፲፩ ቀን ፲፱፵፰ ዓ.ም. ማዕከሉ በፌዴራል መንግሥት በሚመደብለት በጀት ሥራውን ያከናውናል ። ፲ የሂሳብ መዛግብት ፩ . ማዕከሉ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ | 10. Books occounts መዛግብት ይይዛል ፣ 4. የማዕከሉ የሂሳብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይመው ኦዲተር በየአመቱ ይመረመራሉ ፡፡ ፲፩ . ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌደዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፪ ቀን ፲፱፻፶፰ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ