የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፳፬ አዲስ አበባ የካቲት ፳ ቀን ፲፱፻ኝ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፪ / ፲፱፻፲ ዓ.ም የመንግሥት ሠራተኞች ደንብ ማሻሻያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፮፻፶፭ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፪ / ፲፱፻፲ የ፲፱፻፶፭ የመንግሥት ሠራተኞች ደንብ ቁጥር አንድን ለማሻሻል የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ T ፯ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ « የመንግሥት ሠራተኞች ደንብ ማሻሻያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፪ ፲፱፻፵ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ማሻሻያ የ፲፱፻፶፭ የመንግሥት ሠራተኞች ደንብ ቁጥር አንድ አንቀጽ ፴፰ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) ተሠርዘው በሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጾች ተተክተዋል፡ « ፴፰ የወሊድ ፈቃድ ፩- ነፍሰጡር የሆነች ሲቪል ሠራተኛ ፣ ሀ ) ከእርግዝናዋ ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ ሐኪም በሚያዘው መሠረት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣታል፡ ለ ) ከመውለዷ በፊት ዕረፍት እንድታደርግ ሐኪም ካዘዘ ደመወዝ የሚከፈልበት እረፍት ይሰጣታል ። ያንዱ ዋጋ 2.30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ . ፱ሺ፩ ገጽ ፮፻፲፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ የካቲት ፳ ቀን ፲፱፻፲ ዓ • ም • ፪ • ነፍሰጡር የሆነች ሲቪል ሠራተኛ መውለጃዋ ሲደርስ እወል ዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት ፴ ተከታታይ ቀናት የወሊድ ፈቃድ ፡ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ ፳ ተከታታይ ቀናት የወሊድ ፈቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጣታል ፤ ፫ ሠራተኛዋ ከመውለዷ በፊት የወሰደችው የ፴ ቀናት ፈቃድ ሲያልቅ ያልወለደች እንደሆነ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት ለመውለድ ከገመተችበት ቀን በፊት ከወሰደችው ፴ ተከታታይ ቀናት በፊት ያሉት የሥራቀናት በበጀት ዓመቱካላት ከመደበኛው የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ይተካል ፤ ፬ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) መሠረት በበጀት ዓመቱ ውስጥ ለወሰደችው ፈቃድ የሚተካ የዓመት ዕረፍት የሌላት እንደሆነ ከሚቀጥለው የበጀት ዓመት የዕረፍት ፈቃድ በብድር ይሰጣታል፡ የ፴ ቀን ፈቃዷ ሳያልቅ ከወለደች በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት የምተወስደው የወሊድ ፈቃድ ይጀምራል ፤ ፭ ሠራተኛዋ በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) የተወሰነውን \ የወሊድ ፈቃድ ከጨረሰች በኋላ በወሊድ ምክንያት ብትታ መምና ተጨማሪ ፈቃድ የሚያስፈልጋት መሆኑ በሐኪም ከተረጋገጠ በነባሩ ደንብ የሕመም ፈቃድ ድንጋጌዎች መሠረት ፈቃድ መውሰድ ትችላለች ። » ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳ ቀን ፲፱፻፲ ዓ.ም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ