የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፲፩ ኣዲስ ኣበሳ – የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻ቸ፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ ኣዋጅ ቁጥር ፳፫ / ፲፱፻፰፰ ዓ . ም የማዕድን ሥራዎች ገቢ ግብር ( ማሻሻያ ) ኣዋጅ . . . . . ገጽ ፻፲፱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፫ / ፲፱፻፰፰ ዓ - ም የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ . . አዋጅ ቁጥር ፳፫ / ፲፱፻T፰ የማዕድን ሥራዎች ገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ የማዕድን ሥራዎች ገቢ ግብር አዋጅን ማሻሻል በማስ ፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | Mining Income Tax Proclamation ; መንግሥትአንቀፅ ፴፭ ( 6 ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የማዕድን ሥራዎች ገቢ ግብር ( ማሻሻያ ) ኣዋጅ ቁጥር ፳፫ / ፲፱፻፷፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ማሻሻያ የማዕድን ሥራዎች ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር ፲፫ / ፲፱፻T፭ | 2 . Amendment አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተተክቷል ፤ “ ፩ ማንኛውም በከፍተኛ ወይም በአነስተኛ ደረጃ የማዕድን ማምረት ሥራ የተሰማራ ባለፈቃድ ግብር ከሚከፍልበት | ገቢው ላይ ፴፭ ፐርሰንት የገቢ ግብር ይከፍላል ። ” ፫ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅከየካቲት፯ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ንቶ ዋጋ 280 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ተሺ፩ ገጽ ፻፮ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፫ ፲፱፻ዥ፰ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ! የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፑብሊክ አስፈጻሚ አካሳትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻፴፯ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ እውጥቷል ። ክፍል አንድ _ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፫ ፲፱፻ዥ፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። 8 የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ( ከዚህ በኋላ “ ኮሌጁ ” ተብሎ የሚጠራ ) እራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ጅ ኮሌጁ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ኮሌጁ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፤ ፩ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት አፋጠን በተለይ በክልሎች በሲቪል ሰርቪስ ውስጥ የሚያገለግሉ ሠራተኞችን በሥነ ጥበባትና በልዩ ልዩ ያዎች ማሰልጠን ኅብረተሰቡን በሚገባ ሊያገለግሉ የሚችሉበትን ሁኔታዎች መፍጠር : ምልመላ ላይም ለሴቶችና ለኋላ ቀር ክልሎች ልዩ ግምት እንዲሰጥ ማድረግ ፤ ጀ ዕውቀት ማዳበር ፣ ማስፋፋትና ማስተላለፍ ፡ ፫ ከዘር ፣ ከብሔር ፣ ከጾታ ፣ ከኃይማኖትና ፣ ከመሳሰሉት አድሎዎች ነጻ የሆነ በመከባበር ፣ በመተማመን ፣ በመተሳ ሰብና መቻቻል ላይ የተመሠረተና ሁለንተናዊ ስብዕናን የሚያበለጽግና የሰው ልጅ ክቡርነትን የሚያጠናክር ትምህርት መስጠት ፤ ፬ . የሥራ ክቡርነትንና የኅብረተሰብን ብልጽግና የሚያራምድ አስተሳሰብ እንዲሰርጽ ማድረግ ፤ ፭ በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች ሳይንሳዊ የሆነ ጥናትና ምርምር ማካሄድና ጠቃሚ ውጤቶችን ማሰራጨት ። ፬ . ስለኮሌጁ ሥልጣንና ተግባር ኮሌጁ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ ፋክሊቲዎችና ሌሎች የትምህርትና የምርምር ክፍሎች ወይም ተቋሞች ማቋቋም ፤ ፪ የቅድመ ምረቃና የድህረ ምረቃ ፕሮግራም መቀየስናሥራ ላይ ማዋል ፤ ፫ የምስክር ወረቀት ፣ ዲፕሎማና ዲግሪ እንዲሁም ለከፍተኛ ውጤትና አስተዋጽኦ አካዳሚክ ሜዳይ ሽልማትና ማዕረግ መስጠት ፤ ፩ ሴሚናሮች ፣ ወርክሾፖችና ሲምፖዚየሞችን ማዘጋጀትና ማካሔድ ፤ ኑ በሀገሪቱ ውስጥና በሌሎች ሀገሮች ከሚገኙ አቻ ተቋሞች ፡ የምርምር ተቋሞችና ተመሣሣይ ዓላማ ካላቸው ጋር ግንኙነት መመስረት 1 ፮ የትምህርት መጽሔቶችና ጋዜጦችማቋቋምናማሰራጨት ፤ ገጽ ፻፳፩ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ የካቲት ፯ ቀን ፲nይተቿ ዓም : Negarit Gazeta No . 11 15February 1996 Page 121 ፯ የንብረት ባለቤት መሆን ፤ ፰ ውል መዋዋል ! ፩ በስሙ የመክሰስና የመከሰስ ፤ ፲ ዓላማውን የሚያራምዱ ሌሎች ተግባሮችማከናወን ። ክፍል ሁለት ስለኮሌጁ የፖሊሲና የሥራ አስፈጻሚ አካላት ጅ ስለኮሌጁ ቦርድ መቋቋም ፩ . ኮሌጁ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሾሙ ሰባት አባላት ያሉት | 5 . Establishment of Board of Govemos of the College ቦርድ ይኖረዋል ። ፪ ቦርዱ የራሱ ፀሐፊ ይኖረዋል ። ፩ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ 6 የኮሌጁን የአካዳሚክና የአስተዳደር አጠቃላይ ፖሊሲ | ያወጣል ፣ ይወስናል ፤ ፪ ኮሌጁ የሚተዳደርበትን ቻርተር አዘጋጅቶ ለመንግሥት ያቀርባል ፤ ፫ የኮሌጁን አደረጃጀት ይወስናል ፤ ፩ የኮሌጁን ም / ፕሬዚዳንቶች ሹመት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርቦ ያስፀድቃል ፤ ፭ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያፀድቃል ፤ ፩ በኮሌጁ በማስተማር ወይም በምርምር ተግባር ላይ የተሰማሩ የአካዳሚክ ሠራተኞች የሚቀጠሩበትንና የሚ ተዳደሩበትን ሁኔታ ይወስናል ፤ ፯ የኮሌጁን ዕቅድና ረቂቅ በጀት ያፀድቃል ፤ ፰ የኮሌጁ መለያ ምልክት የሚሆነውን አርማ እንዲዘጋጅ ያደርጋል ፤ ጅ ኮሌጁ የሚያስከፍላቸውን ክፍያዎች ይወስናል ፤ ፲• ኮሌጁን በሚመለከት በማንኛውም የኮሌጁ አካል ወይም በኮሌጁ በተሰጠ ውሣኔ ቅር የተሰኘ ግለሰብ የሚያቀር በውን አቤቱታ መርምሮ ውሣኔ ይሰጣል ፤ ፲፩ ኮሌጁ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር የትምህርት ተቋማት ጋር የሚያደርጋቸውን የአካዳሚክ ስምምነቶች መርምሮ ያፀድቃል ፤ ፲፪ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ያወጣል ! | ፲፫ የኮሌጁን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተግባ ሮችን ያከናውናል ። ፯ የፋክሊቲካውንስል መቋቋም ( ሴኔት ) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አባላት የያዘ የኮሌጁ ፋክሊቲ ካውንስል ይቋቋማል ፤ ፩• የኮሌጁ ፕሬዚዳንት ፪ የኮሌጁ ም / ፕሬዚዳንቶች . . ፫ የፋክሊቲው ዲኖች ፩ የኮሌጁ ሬጂስትራ ጅ የተማሪዎች ዲን . . . . . . . . . . . . . . 5 ከኮሌጁ በቋሚ መምህራን ተመራጭ የሆኑ ሦስት መምህራን ፯ በተማሪዎች የሚመረጥ አንድ የተማሪዎች ተወካይ . . . ፰ ፡ በፋክሊቲ ካውንስሉ የሚመረጥ . . . . . . . . . . . . . . ፰ የክሊቲ ካውንስል ሥልጣንና ተግባር የፋክሊቲካውንስሉተጠሪነቱ ለኮሌጁፕሬዚዳንት ሆኖ ቦርዱ | በሚሰጠጨው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ 6 የኮሌጁን የትምህርት ካሌንደር መርምሮ ያፀድቃል ፤ ገጽ ደs ! ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓ . ም . NegaritGazeta No . 11 159February 1996 Page 122 + ኮሌጁን ልዩ ልዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ያፀድቃል ! | ፫ ግሪዎች እንዲሁም ማዳይና ሽልማቶች የሚሰጡበትን ሁኔታ ይወስናል ፤ ጅ የተማሪዎች አቀባበልን ፣ የትምህርት ደረጃ አወሳሰንን ፣ የዲስፕሊን ጉዳዮችንና ሦረቃን የሚመለከቱ መመዘኛ መስፈርቶችን ያወጣል ፣ በነዚህ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች ቅሬታዎችን መርምሮ ውሣኔ ይሰጣል ፣ ጅ አጠቃላይ የፈተና አሰጣጥ ዘዴና ሁኔታን ይወስናል ! 5 የፕሮፌሰርነት ማዕረግእንዲሰጥ ለቦርዱ ሀሣብ ያቀርባል ፣ ሌሎች የአካዳሚክ እድገቶችን ይወስናል ፤ ፮ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ያወጣል ፤ ፰ በቦርዱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። # ስለ ኮሌጁ ፕሬዚዳንትና ም / ፕሬዚዳንቶች ሹመትና ተጠሪነት ፩ የኮሌጁ ፕሬዚዳንት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሾማል ፣ | 9 . Appointment and Accountablity of the Pesident and the ተጠሪነቱም ለቦርዱ ይሆናል " የኮሌጁ ም / ፕሬዚዳንቶች በዚህ አዋጅ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት ይሾማሉ ፣ ተጠሪነታቸውም ለፕሬዚዳንቱ ይሆናል ። ፤ ስለኮሌጁ ፕሬዚዳንት ሥልጣንና ተግባር የኮሌጁ ፕሬዚዳንት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች | 10 . Powes and Duties of the President of the College ይኖሩታል ፤ ፩ : የኮሌጁን ሥራ በበላይነት ይመራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ይቆጣጠራል ፤ ጅ በቦርዱና በፋክሊቲ ካውንስሉ የሚሰጡ ውሣኔዎችና መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል ፡ ያረጋ ግጣል ፤ በኮሌጁ በማስተማር ወይም በምርምር ተግባር ላይ የተሰማሩ የአካዳሚክ ሠራተኞችን ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ደመወዝና አበላቸውን ይወስናል እንዲሁም የኮሌጁን የአስተዳደር ሠራተኞች በመንግሥት ሠራተኞች ሕግ መሠረት ያስተ ጻድራል ፤ የኮሌጁን ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት ለቦርዱ አቅርቦ ያስወስናል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፡ ጅ በቦርዱ ሲፈቀድ በኮሌጁ ስም የሚደረጉትን ማናቸውንም ስምምነቶችና የውል ሰነዶች ይፈርማል ፤ 5 በኮሌጁ ስም የባንክ ሂሣብ ይከፍታል ፣ ያንቀሳቅሳል ፤ ፮ ኮሌጁን በሶስተኛ ወገኖች ዘንድ ይወክላል ፤ ፰ ፡ በየሶስት ወሩ ስለ ኮሌጁ የሥራ እንቅስቃሴ ለቦርድ | ሪፖርት ያቀርባል ፤ ፱ . በቦርዱና ስፋክሊቲ ካውንስሉ የማሰጡትን ሌሎች | ተግባሮች ያከናውናል ። ፲፩ ስለ ኮሌጁ ም ፕሬዚዳንቶች ሥልጣንና ተግባር ፪ የኮሌጁ ም ፕሬዚዳንቶች ከኮሌጁ ፕሬዚዳንት በሚሰ | 1 . Power and Duties of the Vice - Presidents of the College ጣቸው መመሪያ መሠረት የሚከተሉት ሥልጣንና | ተግባሮች ይኖሩዋቸዋል ፣ ሀ ) የኮሌጁን ሥራ በሚመለከት የኮሌጁን ፕሬዚዳንት ያማክራሉ ፣ ይረዳሉ ፤ ለ ) ለነርሱ ተጠሪ የሆኑ የሥራ ክፍሎችና በቦርዱና በፋክሊቲ ካውንስሉ የተሰጡ ውሣኔዎችና መመሪ ያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላሉ ! ያረጋግጣሉ ፡ ሐ ) ኮሌጁ የሚሰጣቸው ትምህርቶችበፋክሊቲ ካውንስሉ በፀደቀው የትምህርት ካለንደርና የትምህርት ፕሮ ራሞች መሠረት መካሄዳቸውን ይክታተላሉ ' ያረጋ ግጣሉ | ገጽ ፻፳፫ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ የካቲት ፯ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም - Negarit Gazeta – No . 11 159February 1996 – Page 123 መ ) በመማር ማስተማሩ ሂደት አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችና አገልግሎቶች እንዲሟሉ ያደርጋሉ ፤ ) የቦርዱ ፣ በፋክሊቲ ካውንስሉና በፕሬዚዳንቱ ተለይተው የሚሰጧቸውን ሌሎች ተግባሮች ያከና ፪ የኮሌጁ ፕሬዚዳንት በማይኖርበትጊዜየኮሌጁ የአካዳሚክ | ጉዳዮች ም / ፕሬዚዳንት ፕሬዚዳንቱን ተክቶ የኮሌጁን | ሥራ ይመራል ፣ ያስተባብራል ። ፲፪ ስለ አካዳሚክ ኮሚሽን መቋቋም እያንዳንዱ የትምህርት ፋክሊቲ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አባላት የያዘና ተጠሪነቱ ለካውንስሉ የሆነ የራሱን የአካ | ዳሚክ ኮሚሽን ያቋቁማል ፤ ፩ የፋክሊቲው ዲን . . ፪ የፋካልቲው ም / ዲን ፫ የዲፓርትመንት ኃላፊዎች . . . . . ፩ በፋክሊቲው ቋሚ መምህራን የተመረጡ የምስት መምህራን . . . . . . . . . . . . . . ፭ ከሦስቱ የመምህራን ተወካዮች አንዱ . . . . . ፀሐፊ ፲፫ የአካዳሚክ ኮሚሽን ሥልጣንና ተግባር አካዳሚክ ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች | ይኖሩታል ፤ ፩ የኮሌጁን የአካዳሚክ ፖሊሲ በመከተል የፋክሊቲውን የትምህርት ካሌንደርና የትምህርት ፕሮግራሞች ያዘጋጃል ፣ በፋክሊቲ ካውንስሉ ሲፀድቅም በሥራ ላይ ያውላል ፤ የ ለየትምህርት ዓመቱ በሚፀድቀው የትምህርትካሌንደርና የትምህርት ፕሮግራሞች መሠረት በፋክሊቲው የሚሰጡ ፈተናዎችን ይወስናል ፤ ፫ ትምህርታቸውን በሚገባ ላጠናቀቁየፋክሊቲው ተማሪዎች ዲግሪ እንዲሰጥ ለፋክሊቲ ካውንስሉ ሃሣብ ያቀርባል ፤ ፩ ወደሚቀጥለው የትምህርት እርከን የሚሸጋገሩ ተማሪ ዎችን ዝርዝር ለፋክሊቲ ካውንስሉ አቅርቦ ያስወስናል ፤ ፭ ፋክሊቲውን የሚመለከቱማናቸውንም የአካዳሚክችግሮች መርምሮ ይወስናል ። ክፍል ሦስት ልዩ ልዩ ፲፩ የኮሌጁ ሌሎች አካላት የኮሌጁ ልዩ ልዩ የትምህርትና የምርምር ክፍሎች የአመራር አካላት ኣመሠራረትና አሰራር በቦርዱ ይወሰናል ። ፲፭ በጀት የኮሌጁ በጀት ከሚከተሉት ምንፎች የተውጣጣ ይሆናል ፤ ፩ ከፌዴራል መንግሥቱ ከሚመደብለት በጀት ፣ ጀ ኮሌጁ ከሚሰበስባቸው የአገልግሎት ክፍያዎች እና ፫ ከሌሎች ምንጮች ። ፲ . ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጐች ይህን ደንብ የሚቃረኑ ደንቦችና መመሪያዎች ተፈጻሚነት | አይኖራቸውም ። ገጽ ፻፳፩ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓ . ም . Negarit Gazeta - No . 11 15February 1996 Page 124 ፲፯ ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። ኣዲስ ኣበባ የካቲት ቀን ፲፱፻፳፰ ዓቅ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ "