የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ
አሥራ ሰባተኛ ዓመት ቁጥር፩
የተሽከርካሪ መለያ ፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ
ደንብ ቁጥር ፪፻፮ / ፪ሺ፫
መመርመሪያና መመዝገቢያ ክፍያ ገጽ ፭ሺ፯፻፺፰
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፪፻፮ / ፪ሺ፫ የተሽከርካሪ መለያ ፣ መመርመሪያና መመዝገቢያ ክፍያን ለመወሰን የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞኪራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተ a ዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፮፻፺፩ / ፪ሺ፫ አንቀጽ ፭ እና በተሽከርካሪ መለያ ፣ መመዝገቢያና መመርመሪያ አዋጅ ቁጥር ፮፻፹፩ / ፪ሺ፪ አንቀጽ ፵፯ (፩) መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ፡፡
አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ የተሽከርካሪ መለያ ፣ መመርመሪያና መመዝገቢያ ክፍያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፪፻፮ / ፪ሺ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል::
ያንዱ ዋጋ
በተሽከርካሪ መለያ ፣ መመርመሪያና መመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር ፮፻፹፩ / ፪ሺ፪ አንቀጽ ፪ የተሠጡ ትርጓሜዎች ለዚህ ደንብም ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል ፡፡
የተፈጻሚነት ወሰን
ይህ ደንብ በፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን በሚመዘገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ፡፡
ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣ.ቁ ፹ሺ፩