×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 16301

      Sorry, pritning is not allowed

የሰበር መ / ቁ 16301
ኅዳር 2 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ
ሓጉስ ወልዱ
ተጉ ጌታነህ
ዳኜ መላኩ
ደስታ ገብሩ
ኦመልካችፉ ተገኝ እንግዳ ተጠሪ አስናቀች ኪዳኔ
የመጥሪያን አደራረስ አስመልክቶ የሚቀርብ ስለሚስተናገድበት ሁኔታ - በሥነ ሥርዓት ሕጉ መሠረት ተከሳሽ በሌለበት ክስ እንዲታይ የሚደረግበት ሁኔታ - የፍ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁጥር 103 ፣ 105 ( 1 ) አመልካች እሱ በሌለበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ እንዲታገድለትና እሱም ወደ ክርክሩ እንዲገባ እንዲፈቀድለት የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱም አመልካች የሥነ - ሥርዓት ሕጉ በደነገገው መሠረት ተጣርቶ ባለመቅረቡ ክርክሩ እሱ በሌለበት መታየቱ ባግባቡ ነው ሲል ሰመወሠን ጥያቄውን ሳይቀበለው ቀርቷል :: በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተመሣሣይ ውሣኔ በመስጠቱ የቀረበ አቤቱታ ፡፡ ዉሳኔ፡- የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውና የፌዴራሉ
ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያፀናው ውሣኔ ፀንቷል ፡፡ 1. በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁጥር 103 እንደተመለከተው መጥሪያ አድራሻ
( ሰጪው ) መጥሪያውን ለማድረስ ያልቻለበትን ምክንያት በቃለ መሐላ አረጋግጦ መጥሪያውን ለፍርድ ቤቱ ይመልሳል ፡፡ ፍርድ ቤቱም የቀረበለትን ምክንያት እንደየሁኔታው በመመዘን ተገቢ ሆኖ ያገኘውን ትዕዛዝ ይሰጣል ፡፡
ፍርድ ቤቱ መጥሪያው እንደተመለሠስት በሕጉ በተመለከተው African Law ሠረት it ጋቢ ሆኖ ይገኘውን ምትክ የሙጥሪ : ኣደራረስ ስርአት
ማስተላለፉ ሕጋዊ ውጤት ያለው ይሆናል ፡፡
የሰበር መ / ቁ 16301
ኀዳር 2 ቀን 1998 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ
ሕጉስ ወልዱ ተገኔ ጌታነህ ዳኜ መላኩ
ደስታ ገብሩ ኣመልካች ተገኝ እንግዳ - ቀረበ ተጠሪ ፦ አስናቀች ኪዳኔ አልቀረበችም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፡፡
ፍ ር ድ አቤቱታው እንዲቀርብ የተደረገው የመጥሪያን አደራረስ በተመለከተ የተነሣውን ቅሬታ ከሕጉ ጋር አገናዝቦ ለመመርመር ተብሉ ነው ፡፡ ጉዳዩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት ሲሆን
ከሣሽ የነበረችው የአሁኗዋ ተጠሪ ናት :: አመልካቹ በተደረገለት ጥሪ መሠረት አልቀረበም ስለተባለ ክርክሩ እሱ በሌለበት
በሌለበት ታይቶ መወሰኑን ከመዝገቡ ተመልክተናል ፡፡ ከዚህ በኋላ መዝገቡ የተንቀሣቀሰው አመልካች እሱ በሌለበት ታይቶ የተሰጠው ውሣኔ እንዲታገድለትና እሱም ወደክርክሩ እንዲገባ እንዲፈቀድለት በመጠየቁ ነው ። ጥያቄው የቀረበለት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ፣ ተከሣሽ የስነ ሥርዓት ሕጉ በደነገገው መሠረት ተጣርቶ ባለመቅረቡ ነው ክርክሩ እሱ በሌለበት እንዲታይ የተደረገው :: የሚል ምክንያት በመስጠት ሣይቀበለው ቀርቶአል ። በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤትም ተመሣሣይ ውሣኔ ሰጥቶአል ። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ማለትም የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ.ቁ 859 ሚያዝያ 5 ቀን 96 ዒ.ም በሰጠው ትእዛዝ ላይ ነው ፡፡
አመለካች በሌለበት እንዲታይ የተደረገው መጀመሪያ በቀጥታ በአድራሻው በመቀጠልም በጋዜጣ በተደረገለት ጥሪ መሠረት ሊቀርብ አልቻለም በሚል እንደሆነ ከመዝገቡ ተመልክተናል ። መጀመሪያ በቀጥታ በአድራሻው የተላከለትን መጥሪያ ሊገኝ ባለመቻሉ መስጠት
መስጠት እንዳልተቻለና መጥሪያውን አልቀበልም ስለማለቱ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁ . 103 መሠረት በመሐላ ተረጋግጦ ለፍ / ቤቱ በመቅረቡ ፍ / ቤቱ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁ
105 ( 1 ) መሠረት የጋዜጣ ጥሪ እንዲተላለፍ ማዘዙኑንም ተመልክተናል ፡፡
አመልካች ሕ tp ረታዊ የሕቅ እህት ያለበት c ትእዛዝሰሉብኝ -ሸማሸት የሰበር አቤቱታ ያቀረበው እነዚህን የሥነ - ሥርዓት ደንቦች በመከተል የተከናወነው
ሂደት ትክክል አይደለም :: መጥሪያው በደንብ እንዲደርሰኝ ሣይደረግ ክርክሩ በሌለሁበት እንዲታይ የተደረገው :: የውጥሪያው መጥቶልኝ አልቀበልም አላልኩም ፡፡ ስራዬ ሾፌርነት በመሆኑም ጋዜጣውን ማየት ይችላል መገመት የለበትም በማለት ነው ::
ከፍ ሲል ከተመለከቱት ሁኔታዎች ማየት እንደሚቻለ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ በቶደነገገው መሠረት መጥሪያውን ለአመልካች ልኮአል ። ሆኖም አመልካቹ በአድራሻው ተፈልጎ ባለመገኘቱ እና ሌላም መጥሪያውን መቀበል የሚችል ሰው ሊገኝ ባለመቻሉ በታቀደው ሁኔታ መጥሪያውን ማድረስ ሣይቻል ቀርቶእል ፡፡ ይህን መሰል ችግር ሲያጋጥም የሥነ ሥርዓት መፍትሄ እስቀምጦአል ፡፡ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁ . 103 እንደተመለከተው መጥሪያ አድራሹ (
ሰው ) መጥሪያውን ለማድረስ ያልቻለበትን ምክንያት አረጋግጦ መጥሪያውን ለፍ / ቤቱ ይመልሳል ፡፡ ፍ / ቤቱም የቀረበለትን ምክንያት እንደየሁኔታው በመመዘን ተገቢ ሆኖ ያገኘነውን ትእዛዝ ይሰጣል ፡፡ ይህም ማለት ተከሣሽ መጥሪያውን ለመቀበል ፈቃደኛ ያለመሆኑ ወይም ደረሰኝ ለመስጠት እምቢተኛነቱ በመሐላ በተሰጠ ቃል ከተረጋገጠለት መጥሪያው በትከከል እንደደረሰ በመቁጠር ክርክሩ ተከሣሹ በሌለበት እንዲታይ ያደርጋል ፡፡ መጥሪያው በትክክል እንደደረሰ
በትክክል እንደደረሰ ለመቁጠር የሚያስችል ምክንያት ካላገኘ ነገርግን የመጀመሪያው ባለመገኘቱ ምክንያት መጥሪያው መመለሱን ካመነ ደግሞ ቀጥሉ ያለውን ሌላው የመጥሪያ አሰጣጥ ሥርዓት ( አማራጭ ይጠቀማል ፡፡ ይህ አማራጭም በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁ . 105 ከተመለከቱት አንዱ ይሆናል ማለት ነው ::
በተያዘው ጉዳይ እንደሚታየው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት መጥሪያው እንደተመለሰለት ወዲያውኑ አመልካች በሌለበት ክርክሩ እንዲታይ አላዘዘም ፡፡ ተገቢ ሆኖ ያገኘው አካሄድ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁ 105 ( 1 ) ከተመለከቱት ከምትክ የመጥሪያ አደራረስ ሥርዓቶች አንዱን ማለትም የጋዜጣ ጥሪ ማስተላለፍ ነው ። በዚህ ረገድ ተገቢ ነው ያለውን ኣማራጭ የመወሰን
ሥልጣንም የፍ / ቤቱ ነው ። በጋዜጣ የሚደረግ ጥሪ በሕጉ ከተፈቀዱት ምትክ የመጥሪያ አሰጣጥ ሥርዓቶች አንዱ በመሆኑም ሕጋዊ ውጤት ያለው ነው ። የሥር ፍ / ቤቶች አመልካች በመጨረሻ ያቀረበውን ጥያቄ ያልተቀበሉትም በዚህ
ምክንያት እና ጥሪው የተላለፈው ተገቢውን የሥርዓት ደንብ ተከትሉ መሆኑን በማረጋገጣቸው ነው ፡፡ በመሆኑም በዚህ ረገድ የፈፀሙት መሠረታዊ የሕግ ስህተት የለም ።
ው ሣ ኔ 1. አቤቱታ የቀረበባቸው የሥር ፍ / ቤቶች ትእዛዞች ፀንተዋል ፡፡
2. መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?