×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፲፯/፲፱፻፷፯ ዓም “የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባበር ብሔራዊ ምክር ቤት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አሥራ አንደኛ ዓመት ቁጥር ፴፩ አዲስ አበባ - ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፲፯ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፲፯ / ፲፱፻፵፯ ዓ.ም “ የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባበር ብሔራዊ ምክር ቤት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ . … ......... ገጽ ፪ሺ፲፰ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፲፯ / ፲፱፻፲፯ የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባበር ብሔራዊ ምክር ቤት ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ ኣካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፩ መሠረት ይህን ደንብ | Pursuant to Article 5 of the Definition ofPowers and Duties of አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል ኣከባበር ብሔራዊ ምክር ቤት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፲፯ / ፲፱፻፲፯ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ “ የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል ” ማለት ኢትዮጵያ በምትከተለው የዘመን አቆጣጠር መሠረት ሦስተኛው ሚሌኒየም ከመግባቱ ቢያንስ ከሦስት ወር በፊት ጀምሮ ዓመቱን በሙሉ ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ነው ። ፫ • መቋቋም ፩ የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባበር ብሔራዊ ምክር ቤት ( ከዚህ በኋላ “ ምክር ቤት ” እየተባለ የሚጠራ ) በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ • የምክር ቤቱ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ ፱ሺ፩ · ሳባር ገጽ ፫፻ሺ ፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩ ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም የምክር ቤቱ ዓላማዎች ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባበር አጋጣሚን በመጠቀም የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፣ መላው ኅብረተሰብ በልማትና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ረገድ የጋራ የሆነ አገራዊ አመለካከት በመገ ንባት የተሻለ ገጽታ ያላት ኢትዮጵያን ለማየት ብሩህ ተስፋ ሰንቆ ወደ አዲሱ የኢትዮጵያ ሚሌኒየም እንዲሸ ጋገር የማስቻል ፣ ፪ ኅብረተሰቡን በልማትና በመልካም አስተዳደር ሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ በማንቀሳቀስ ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር የማስቻል ፣ ፫ • በመንግሥትና በሕዝቦች ሙሉ ተሳትፎ የአገሪቱን መልካም ገጽታ ሊገነቡ የሚችሉ ብሔራዊ እሴቶቻችን ለመላው ዓለም በማስተዋወቅ አገሪቱን በኢንቨስት መንት ፣ በቱሪዝም ፣ በንግድና በሌሎች መስኮች ተመራ ጭነት የሚያሰጣት መልካም ገጽታ እንዲገነባ የማስቻል ፣ ፬ • ለመላው ኅብረተሰብ ፣ ለወጣቱ ትውድና በአጠቃላይ ለመላው ዓለም ብሔራዊ ዓላማዎቻችንን ፣ ተልዕኮአች ንንና የትኩረት አቅጣጫዎቻችንን የሚያመላክቱ ዐበይት መልዕክቶችን ለማስተላለፍ የማስቻል ። ፭ የምክር ቤቱ አባላት ምክር ቤቱ ከሚከተሉት አካላት የተውጣጡ አባላት ይኖሩታል ፣ ፩ . ከፌዴራልና ከክልል መንግሥታት ፣ ፪ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ፣ ፫ . ከግል ባለሃብቶች ፣ ከታዋቂ ግለሰቦች ፣ ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ፣ በውጭ አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ፣ እና ፬ . ለበዓሉ አከባበር አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ከሚችሉ ሌሎች | 6. Powers and Duties of the Council አካላት ። ፮ : የምክር ቤቱ ሥልጣንና ምክር ቤቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ ፩ . በዚህ ደንብ አንቀጽ ፬ የተመለከቱትን ዓላማዎች ለማስ ፈጸም የሚረዱ መርሀ ግብሮችንና ፕሮጀክቶችን ለመንደፍ የሚያስችል ሃሳብ ያቀርባል ፣ መንግሥትን ያማክራል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ የሚውልበትን ሁኔታ ያመቻቻል ፣ ፪ : ለሚሌኒየም በዓሉ አከባበር በሚደረገው ዝግጅት መንግ ሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋሞችና ድርጅቶች ፣ በአጠቃላይ መላው ኅብረተሰብ ፣ እንዲሁም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ያበረታታል ፣ ፫ • ለበዓሉ አከባበር የሚያስፈልገውን የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር በማፈላለግ ያሰባ 7. Organs of the Council ስባል ፣ ፬ • ዓላማውን ከግብ ለማድረግ የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል ። ፯ የምክር ቤት አካላት ምክር ቤቱ የሚከተሉት አካላት ይኖሩታል ፣ ፩ በክልል ፣ በዞንና በወረዳደረጃ የሚቋቋሙምክር ቤቶች ፣ ፪ እንዳስፈላጊነቱ በውጭ አገር የሚቋቋሙ ምክር ቤቶች ፣ ፫ . የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፣ እና ፬ • ብሔራዊ ጽሕፈት ቤት ። ፰ ስለምክር ቤቱ ፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በመንግሥት ይመደባሉ ። ገጽ ፫ሺ ፩፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩ ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓም ፱ የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሥልጣንና ተግባር የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ፣ ፩ . በዚህ ደንብ አንቀጽ ፮ መሠረት ለምክር ቤቱ የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ባግባቡ መፈጸማቸውን በበላይነት ይቆጣጠራል ፤ ፪ የምክር ቤቱንና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን ስብሰባዎች ይመራል ፣ ፫ • የምክር ቤቱን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ጽሕፈት ቤት የሥራ እንቅስቃሴ በበላይነት ይቆጣጠራል ፣ አፈጻጸማቸ ውንም ይከታተላል ፣ ፩ ለኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባበር የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል ። የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሥልጣንና ተግባር የምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፣ ፩ . የምክር ቤቱን አስተያየት መሠረት በማድረግ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፬ የተመለከቱትን ዓላማዎች ለማስፈጸም የሚረዱ መርሀ ግብሮችን ፣ ፕሮጀክቶችንና የአፈጻጸም ዕቅዶችን በመንደፍ ለመንግሥት ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም ተከታትሎ ያስፈጽማል ፣ ፪ • የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባበር ሲጠናቀቅ በሥሩ በመከናወን ላይ ያሉትን መርሀግብሮችና ፕሮጀክቶችን ለመንግሥት አቅርቦ በማስወሰን አግባብነት ላላቸው መንግሥታዊ አካላት ያስረክባል ፣ ለኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባበር የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል ። ፲፩ ስለምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ፩ . የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ፣ ሀ ) ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ይኖረዋል ፣ ለ ) ዋና መሥሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላ ጊነቱ ከአገር ውጭ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ፣ ሐ ) በመንግሥት በሚሾም አንድ ዋና ዳይሬክተር የሚመራ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱና ምደባቸው በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የሚጸድቅ ረዳት ዳይሬ ክተሮች ይኖሩታል ፣ መ ) ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት የሚውጣጡና ሌሎችጊዜያዊ ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፪ ጽሕፈት ቤቱ የምክር ቤቱን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ይከታተላል ፣ ይፈጽማል ። ፲፪ • የስብሰባና የውሳኔ አሰጣጥ ሥነ - ሥርዓት ፩ ምክር ቤቱ የራሱን የስብሰባና የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት መመሪያ ያወጣል ። የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የራሱን የስብሰባ ሥርዓትና የምክር ቤቱን መተዳደሪያ መመሪያ ያወጣል ። ፲፫ : በጀት የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት የሥራ ማስኬጃ በጀት | 13. Budget በመንግሥት ይመደባል ። ፪ ለኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባበር ዝግጅት የሚያስፈ ልገው ወጪ ፣ ሀ ) በመንግሥት በሚመደብ በጀት ፣ ለ ) በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ከሚደረጉ ኤግዚቢ ሽኖች ፣ ባዛሮችና ሌሎች የገቢ ማሰባሰቢያ መድረኮች በሚገኝ ገቢ ፣ ሐ ) ከልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና ተቋሞች በሚገኝ ድጋፍ ፣ እና መ ) ከሌሎች ምንጮች በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ፣ የሚሸፈን ይሆናል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት የሚገኝገንዘብ በምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ስም በሚከፈት የባንክ ሂሳብ ተቀማጭ ሆኖ ለኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል ዝግጅት ማስፈጸሚያ ይውላል ። ገጽ ፫ሺ ፩፻፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩ ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም ፲፬ • ስለሂሳብ መዛግብት ፩ የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ የጽሕፈት ቤቱ የሂሳብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በፌዴራሉ ዋና ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች ይመረመራሉ ። ፲፭ መመሪያ የማውጣት ሥልጣን የምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይህን ደንብ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መመሪያዎች ሊያወጣ ይችላል ። ፲፮ : ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ ከግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፶፯ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል አዲስ አበባ ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?