ሠላሣ አንደኛ ዓመት ቍጥር ፩
የ ኢ ት ዮ ጵ ያ ን ጉ ሠ ነ ገ ሥ ት መ ን ግ ሥ ~ ።
ነ ጋ ሪ ት ጋ ዜ ጣ ።
'
የጋዜጣው ዋጋ
ባገር ውስጥ q መት
በ፮ ወር
____ ለውጭአገር እጥፍ ይሆናል ።
፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
የመንግሥት ማስታወቂያ ቊጥር ፬፻፳፩ ፲፱፻፷፬ ም.
በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በጽሕፈት ሚኒስቴር ተጠባባቂነት የቆመ ።
የመንግሥት ማስታወቂያ ቊጥር ፬፻፳፪ ፲፱፻፷፬ ዓ. ም. የማዕርግ ዕድገት
የመንግሥት ማስታወቂያ ቊጥር ፬፻፳፫ ፲፱፻፷፬ ዓ.ም.
የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቊጥር ፬፻፲፪ ፲፱፻፷፬ ዓ. ም. የ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. የጠቅላይ ጤና ጥበቃ አማካሪ ቦርድ አባሎች ስያሜ
ቊጥር ፬፻፳፩ ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. የመንግሥት ማስታወቂያ ።
ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት መልካም ፈቃዳቸው ሆኖ ከዚህ የሚከተሉውን ሹመት ሰጥተዋል ።
ሐምሌ ፲፭ ቀን ፲፱፻፷፫ ዓ. ም.
አፈ ንጉሥ ቅጣው ይታጠቁ የፍርድ ሚኒስቴር ዋና አማካሪ ፤
አቶ አበጀ ደባልቅ አፈ ንጉሥ ተብለው የግርማዊ ንጉሠ ነገሥት የዙፋን ችሎት የፍርድ አጣሪዎች ጉባኤ ፕሬዚዴንት አቶ መሐመድ አብዱራህማን በፍርድ ሚኒስቴር ሚኒ ስትር ደ ኤታ ፤
አቶ አበራ ጀምበሬ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ደ ኤታ ፤
አቶ ይልማ ኃይሉ በፍርድ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ቀኛዝማች አየነው አዳል የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል !
አቶ ንጉሤ ፍትሕ ዐወቀ በመሬት ይዞታና አስተዳደር ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ፤
አቶ ጥበቡ በየነ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ፕሬዚዴንት ፤ አቶ ሰሎሞን ተካልኝ በፍርድ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒ ስትር ፤
- አቶ መኩሪያ ወርቁ በመንግሥት አገልግሎት ጡረታ ጉባኤ ኮሚሽነር ፤
ብላታ ደምሴ ወርቅ አገኘሁ ምክትል አፈ ንጉሥ ፤ አቶ በቀለ ሀብተ ሚካኤል ምክትል አፈ ንጉሥ ፤ አቶ ኃይሉ ገብረ ሥላሴ በፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን እንስቲትዩት ዋና ሥራ አስኪያጅ
አዲስ አበባ መስከረም፪ ቀን ፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
ቢያንስ በወር አንድ ጊ " ይታተማል
የፖስታ ሣጥን ቍጥር ፩ሺ | ፻፷፬ (1364)