ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ በከፊል እንዲደራጅ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ሊ ር . የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፵፪ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲስ አበባ መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፲፭ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ ኣዋጅ ቁጥር ፫፻፳፪ / ፲፱፻፶፭ ዓም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማደራጃ ገጽ ፪ሺ፩፻፴፭ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፪ ፲፱፻፲፭ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን በተወሰኑ ክልሎች ለማደራጀት የወጣ አዋጅ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፻፰ ( ፪ ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኣስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሆነ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሀገሪቱ በሙሉ ወይም ሚችል በመደንገጉ ፣ በተወሰኑ ክልሎች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ማደራጀት በማስፈለጉ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፻፰ ( ፪ ) እና አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማደራጃ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፪ / ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ • የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ስለማደራጀት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ባደረገው ስብሰባ በአፋር ክልል ፣ በቤንሻንጉል ክልል ፣ በጋምቤላ ክልል ፣ በሶማሌ ክልል እና በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች እንዲደራጁ ወስኗል ። ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ ፰ሺ፩ ያንዱ ዋጋ ገጽ ፪ሺ፩፻፴፮ ፌዴራል ቁጥር ፵፬ መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. በመታየት ላይ ስላሉ ጉዳዮች ይህ ኣዋጅ ከመጽናቱ በፊት በሕገ - መንግሥቱ አንቀጽ ፪፰ ( ፪ ) በተሰጣቸው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን መሠረት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ በተመለከቱት ክልሎች በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች በመታየት ላይ ያሉ ጉዳዮች በተጀመሩበት ፍርድ ቤቶች ታይተው ይወሰናሉ ። ፪ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ቢኖርም ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች በመታየት ላይ ያሉ ጉዳዮች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲታዩ ለማድረግ ይችላል ። ፬ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከመጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ