የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፴፩ አዲስ አበባ -- የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፰ ፲፱፻፵፩ ዓም የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ማቋቋሚያ አዋጅን ለመሻር የወጣ አዋጅ ገጽ ፩ሺህ አዋጅ ቁጥር ፩፻፳ / ፲፱፻፲፩ የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ማቋቋሚያ አዋጅን ለመሻር የወጣ አዋጅ የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ለማቋቋም ወጥቶ የነበረውን አዋጅ መሻር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፡ ሕገመንግሥት አንቀጽ ፶፭ / ፩ / መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ድርጅት ማቋቋሚያ አዋጅን ለመሻር የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፳ / ፲፱፻፲፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ መሻር የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፷፮ / ፲፱፻፷፮ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ፫ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅካየካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም • ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ያንዱ ዋጋ ብር 2 : 30 [ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁቷሺ፩