የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፳፯ አዲስ አበባ ሐምሌ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፪ / ፲፱፻፲፩ ዓም • ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩትን በልማት ድርጅ ትነት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ..ገጽ ፩ሺ፩፻፵፮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፪ / ፲፱፻፲፩ ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩትን በልማት ድርጅትነት ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / w ፬ አንቀጽ / ፩ / ( ሀ ) Republic of Ethiopia Proclamation No. 4/1995 and Article መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩትን በልማት ድርጅትነት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፪ / ፲፱፻፵፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ መቋቋም ፩ ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት ከዚህ በኋላ “ ኢንስቲትዩቱ ” እየተባለ የሚጠራ / የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ ኢንስቲትዩቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፳፬ መሠረት ይተዳደራል ። ፫ . ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በመንግሥት የሚሰየም አካል የኢንስቲትዩቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ይሆናል ። ያንዱ ዋጋ 2:30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ኢንስቲትዩቱ ካሎም , ገጽ ፩ሺ፩፻፯ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣቁጥር፳፮ሐምሌ f ቀን ጀ፩ዓም ዋና መሥሪያ ቤት፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤትደብረዘይት ሆኖ እንደአስ ፈላጊነቱ በማንኛውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ፭ ዓላማ ፡ ኢንስቲትዩቱ የተቋቋመባቸው ዓላማዎች የሚከተሉት ፩ ለተለያዩ የእንስሳት በሽታዎች ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው ክትባቶች ማምረት፡ ፪ ልዩ ልዩ የእንስሳት መድኃኒቶችን ማቀነባበርና ማዋሃድ ፡ • ለምርትና ለእንስሳት በሽታ ምርምር ሥራየሚያገለግሉ ባዮሎጂካሎችንና ሪኤጀንቶችን ማምረት ፡ ፬ ምርቶችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ አቅርቦት በመሸጥ ትርፍና ትርፋማነትን ማሣደግ ፣ ፭ በተጨማሪ ሌሎች ተዛማጅ ምርቶችን ማምረት ። ፮ ካፒታል ፡ ለኢንስቲትዩቱ የተፈቀደው ካፒታል ብር ፴፭ ሚሊዮን ፯፻፴፯ሺ፩፻፳፪ ( አርባ አምስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰላሳ ሰባት ሺ አንድ መቶ ሃያ ሁለት ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብር ፵ ሚሊዮን ፩፻፴፬ሺ ፩፻፳፪ ( አርባ ሚሊዮን አንድ መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሺ አንድ መቶ ሃያ ሁለት ብር ) በዓይነትና በጥሬ ገንዘብ ተከፍሏል ። ፯ የኃላፊነት ወሰን ጠቅላላ ንብረት በላይ በዕዳ ተጠያቂ አይሆንም ። ፰ ኢንስቲትዩቱ የሚቆይበት ኢንስቲትዩቱ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል ፡ ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ፡ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሐምሌ ፳፫ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ