×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 66/1989 ዓ•ም• የመንገድ ፈንድማቋቋሚያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፳፬ አዲስ አበባ - - የካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐ ' ብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፷፮ / ፲፱፻፫፱ ዓ•ም• የመንገድ ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ . . . . . . . . . . . . . . . . ገጽ ! ደጋጀ አዋጅ ቁጥር ፳፮ ፲፱የቸሀ የመንገድ ፈንድ ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የመንገዶች ልማት ጥገናና ማሻሻያ ለአገሪቱ የተቀላጠፈ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት አስፈላጊ በመሆኑ ፡ የመንገዶች መካር በቀር የማያቀcጥ የገንዘብ የመሸ ሆኖ | rehabilitation of roads are essential for an accelerated socio በመገኘቱ ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ « የመንገድ ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፳፮ ፲፱፻ዥሀ• » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፡ _ ፩ « መንገድ » ማለት አውራ ጐዳና ፡ የገጠር መንገድና | የከተማ መንገድ ሲሆን ድልድይን ይጨምራል ፡ ያንዱ ዋጋ 1 340 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ . ፱ሺ፩ ገጽ ፫፻፷፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ የካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 24 6 March 1997 – Page 362 ፪ « የመንገድ ደኅንነት እርምጃዎች » ማለት በመንገድ አጠቃቀም ላይ አደጋ እንዳይደርስ የሚከላከሉ ሥራዎችን መሥራትንና የትራፊክ እንቅስቃሴ መቆጣ ጠሪያ ምልክቶችንና መሣሪያዎችን በመንገድ ላይ ማኖርን ያጠቃልላል ። « የመንገድ ተጠቃሚ » ማለት የተሽከርካሪ ባለቤት ወይም የመንገድ ትራንስፖርት ተጠቃሚ የሆነ ማንኛውም ሰው ነው : ፬ « ባለሞተር ተሽከርካሪ » ማለት በሜካኒካል ወይም በኤሌ ክትሪክ ኃይል የሚንቀሳቀስ ሆኖ የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪ : የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ፡ የግል አውቶሞቢል : ጐታች መኪና ወይም ባለሞተር ብስክሌት በሚል ስያሜ የሚጠራ ተሽከርካሪ ነው : : ፭ « መንግሥት » ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ነው ፡ ፮ « ክልል » ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፯ የተጠቀሰው ማንኛውም ክልል ሲሆን ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ሲባል የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ አስተዳደርንም ይጨምራል ፡ ጊ « የመንገድ ኤጀንሲ » ማለት መንገዶችን ለማልማት ፡ ለመጠገንና ለማስተዳደር ኃላፊነት የተሰጠው የመን ግሥት ፡ የክልል ወይም የከተማ አስተዳደር አካል ነው : ቿ « ቦርድ » ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ ( ፩ ) ( ሀ ) መሠረት የተቋቋመ የመንገድ ፈንድ ቦርድ ነው : ህ - « ሰው » ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ። የመንገድ ፈንድ ( ከዚህ በኋላ « ፈንዱ » እየተባለ የሚጠራ ) ቋሚ የፋይናንስ ምንጭ ሆኖ የገንዘብ ሚኒስቴር በሚከፍተው ልዩ የባንክ ሂሣብ ውስጥ ተቀማጭ እንዲሆን በዚህ አዋጅ | 4 . Objectives of the Fund ተቋቁሟል ። ፬ . የፈንዱ ዓላማ የፈንዱ ዓላማ ለመንገድ ጥገናና ለመንገድ ደኅንነት እርም ጃዎች የሚያስፈልጉትን ወጪዎች የመሸፈን ይሆናል ። የፈንዱ ምንጮች ፩ ፈንዱ ከሚከተሉት ምንጮጮች ይሰበሰባል ፡ ሀ ) በመንግሥት ከሚመደብ በጀት ፡ ለ ) ለመንገድ ጥገና ከተጣለ የነዳጅ ታሪፍ ፡ ሐ ) በክብደት ላይ ከተመሠረተ ዓመታዊ የተሽከርካሪ ፈቃድ ማደሻ ክፍያ ፡ መ ) ከተፈቀደው ክብደት በላይ በመጫን ከሚጣል ቅጣት ፡ ሠ ) እንደአስፈላጊነቱ ከሚጣል ከማናቸውም ሌላ የመንገድ ታሪፍ ። ፪ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ ( ሐ ) ድንጋጌ መንገዶችን በሚጠቀሙ ባለሞተር ተሽከርካሪዎች ላይ ሁሉ ተፈጻሚ ይሆናል ። ፮ የፈንዱ ተሰብሳቢ ገንዘብ ፩ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ( ፩ ) ( ለ ) ፡ ( ሓ ) ፡ ( መ ) እና ( ሠ ) ! መሠረት የሚሰበሰበው ገቢ መጠን በሚኒስትሮች ምክር | ቤት ይወሰናል ። ፪ በመንግሥት የሚመደበው በጀት በየወሩ መጀመሪያ በፈንዱ ሂሣብ ገቢ ይደረጋል ። ፫ ለመንገድ ጥገና የተጣለ የነዳጅ ታሪፍ የሚሰበሰበውና በፈንዱ ሂሣብ ገቢ የሚደረገው በኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት አማካይነት በየወሩ መጨረሻ ይሆናል ። ገጽ ፫፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ የካቲት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 24 6 March 1997 - – Page 363 _ ፬ በክብደት ላይ የተመሠረተ ዓመታዊ የተሽከርካሪ ፈቃድ ማደሻ ክፍያ የሚሰበሰበውና በፈንዱ ሂሣብ ገቢ የሚደረገው በእያንዳንዱ ክልል የትራንስፖርትና መገናኛ ቢሮ ወይም አግባብ ባለው ሌላ የክልሉ አካል ሲሆን የተሰበሰበው ገንዘብ እስከየወሩ መጨረሻ ገቢ ይሆናል ። ፭ ከተፈቀደው ክብደት በላይ በመጫን የሚጣል የገንዘብ ቅጣት የሚሰበሰበውና በፈንዱ ሂሣብ ገቢ የሚደረገው የተሽከርካሪ ክብደት መቆጣጠሪያ ደንብን ለማስፈጸም ሥልጣን በተሰጠው አካል ሲሆን የተሰበሰበው ገንዘብ እስከየወሩ መጨረሻ ገቢ ይሆናል ። ፮ እንደአስፈላጊነቱ ከሚጣል ከማናቸውም ሌላ የመንገድ ታሪፍ የሚገኝ ገቢ የሚሰበሰበውና በፈንዱ ሂሣብ ገቢ የሚደረገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚሰይመው አካልና በሚወስነው ጊዜ ይሆናል ። ፯ . በዚህ አንቀጽ መሠረት ገንዘብ በፈንዱ ሂሣብ ገቢ ያደረገ ማንኛውም አካልና የገንዘብ ሚኒስቴር በየወሩ ማብቂያ ከ፲፭ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ስለገቢው ለቦርዱ ሪፖርት ያቀርባሉ ። ፯ ስለክፍያዎች ከፈንዱ ሂሣብ ገንዘብ ወጭ ሆኖ የሚከፈለው በጸደቀው ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራም መሠረት ለተከናወኑ ሥራዎች : ለተገዙት ዕቃዎችና አገልግሎቶች ሲሆን አከፋፈሉም ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይሆናል ። | • ስለፈንዱ አካላት ፩ ፈንዱ ፡ ሀ ) ከመንግሥት : ከክልሎችና ከመንገድ ተጠቃ ሚዎች የሚወከሉ አባላት የሚገኙበት ቦርድ ፡ እና ለ ) የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ ጽሕፈት ቤት ፡ ይኖረዋል ። ፪• የቦርዱ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ፬ ስለቦርድ አባላት ፩ የቦርዱ አባላት ቁጥርና የአወካከላቸው ሥርዓት በመን | ) The number of members of the Board and ግሥት ይወሰናል ። ፪• የቦርዱ ሰብሳቢ በመንግሥት ይሰየማል ። ፫ የቦርዱ አባላት የሥራ ዘመን ሁለት ዓመት ይሆናል ። ሆኖም ማንኛውም አባል በወከለው አካል ለተጨማሪ ሥራ ዘመናት እንደገና ሊመደብ ይችላል ። ፬ . አንድን የቦርድ አባል የመደበ አካል በማናቸውም ጊዜና ምክንያት ሊያነሳውና በሌላ ሊተካው ይችላል ። የቦርድ አባላት ቁጥር በሞት ፡ ሥራን በፈቃድ በመልቀቅ ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት ቢቀነስ ክፍት ቦታው በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ይሞላል ። ፮ የቦርዱ ሥልጣን በቦርዱ አባላት ቁጥር ማነስ ምክንያት አይነካም ። ቪ ማንኛውም የቦርድ አባል በቦርዱ ውስጥ ካለው ሥራ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚጋጭ ማንኛውም ተግባር ማከናወን የለበትም ። በቦርዱ ውስጥ ካለው ሥራ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚጋጭ ጉዳይ ሲያጋጥመው ይህንኑ ለቦርዱ በማሳዉቅ ጉዳዩ ከሚታይባቸው የቦርዱ ስብሰባዎች ሁሉ ራሱን ማግለል አለበት ። ገጽ ፫፻፳፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ የካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፫፱ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta – No . 24 65 March 1997 – Page 364 ፲ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ ፈንዱን ያስተዳድራል ፡ ፪ . ስለፈንዱ አሰባሰብና ከፈንዱ ገንዘብ ወጪና ተከፋይ ስለሚሆንበት ሥርዓት መመሪያ ያወጣል ፣ ፫• ለፈንዱ መግባት ያለባቸው ገቢዎች በወቅቱ መሰብሰባቸ ውንና በፈንዱ ሂሣብ መግባታቸውን ያረጋግጣል ፤ ፬• የመንገድ ኤጀንሲዎችን ዓመታዊ የመንገድ ጥገና ፕሮግ ራሞች ከመጽደቃቸው በፊት ይገመግማል ፡ ፕሮግራሞቹ በተቀነባበረና በተቀናጀ ዘዴ እንዲዘጋጁ ያማክራል ፤ ፭ በዓመቱ ውስጥ በፈንዱ የሚሸፈኑ ሥራዎችን በተመ ለከተ ለመንግሥት ሃሳብ ያቀርባል ፡ ሲፈቀድም በዕቅዱ መሠረት የፈንዱን ገንዘብ ያከፋፍላል ፤ ፮ በፈንዱ አከፋፈል ላይ ተጠያቂነትና ግልጽ አሠራር መኖሩን ያረጋግጣል ፡ - - . ፯ የመንገድ ኤጀንሲዎችን የሥራ አመራር ሪፖርቶች እየተ ቀበለ ይገመግማል ፡ የፈንዱን አጠቃቀም በተመለከተ የሚጠናቀሩ ሪፖርቶችን አዘገጃጀት ይቆጣጠራል ፤ ፰ በፈንዱ የተከናወኑትን የመንገድ ጥገና እና የመንገድ ደኅንነት እርምጃዎች ተግባራት ፡ የፋይናንስና የቴክኒክ ኦዲት ያስደርጋል : የኦዲት ሪፖርቶችን ይገመግማል ፣ በኦዲት ሪፖርቶቹ መሠረት ተገቢ እርምጃዎች መወሰዳ ቸውን ያረጋግጣል ፡ ሀ ለመንገድ ጥገና ፕሮግራም የሚያስፈልጉ ተጨማሪ የፋይ ናንስ ምንጮችና የታሪፍ ደረጃዎችን በተመለከተ ለመን ግሥት ሃሳብ ያቀርባል ፡ ፲ ከመንገድ ጥገናና ከፈንዱ ጋር በተያያዙ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ መንግሥትን ያማክራል ፤ ፲፩ . በኦዲተር የተመረመረ የፈንዱ ዓመታዊ ሂሣብ እንዲጠና ቀርና ይፋ እንዲሆን ያደርጋል ፤ ፲፪ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው አማካሪ ኮሚቴዎችን ያቋቁማል ፣ ሥራቸውን ይመራል ፡ ያስተባብራል ። ፲፩ የቦርዱ ስብሰባዎች ፩ . የቦርዱ መደበኛ ስብሰባ በየሦስት ወሩ አንድ ጊዜ ይደረጋል ፣ ሆኖም በሰብሳቢው ሲጠራ ቦርዱ በማና | 11 . Meetings of the Board ቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል ። ፪ . በቦርዱ ስብሰባ ላይ አብዛኛው አባላት ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ የቦርዱ ውሳኔ የሚተላለፈው በስብሰባው ከተገኙ አባላት በአብዛኛው ድምጽ ሲደገፍ ነው ። ሆኖም ድምጹ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። [ ፬ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲፪ : ስለፈንዱ ጽሕፈት ቤት ፩ የፈንዱ ጽሕፈት ቤት ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ይሆናል ። ፪• ጽሕፈት ቤቱ በቦርዱ አቅራቢነት በመንግሥት የሚሾም አንድ ኃላፊና አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፲፫• የጽሕፈት ቤቱ ሥልጣንና ተግባር ጽሕፈት ቤቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ ገጽ ፫፻፷፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ የካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta – No . 24 6 March 1997 – Page 365 ፩ የቦርዱ ውሳኔዎችና መመሪያዎች በትክክል ሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል ፡ ያረጋግጣል ፣ ፪• የፈንዱን ሂሣብና ሪኮርድ ይይዛል ፣ ፫ የቦርዱን ሥራ አመራር ስብሰባዎች ሪኮርዶች ይይዛል ፡ ለፈንዱ መግባት የሚገባው ገንዘብ ሁሉ በወቅቱ በፈንዱ ሂሣብ ገቢ መደረጉን ይከታተላል ፡ የፈንዱን የሂሣብ መግለጫዎች እያዘጋጀ በየዓመቱ ለቦርዱ ያቀርባል ፡ ፮ ስለፈንዱ ገቢዎችና አጠቃቀም : ስለመንገድ ጥገና ጠቀሜታ ፡ መንገድን አለመጠገን ስለሚያስከትላቸው ውጤቶች : ጥራት ያለው መንገድ ለተጠቃሚዎች ስለሚያስገኘው ቁጠባና ስለመሳሰሉት የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችንና ወቅታዊ ሕትመቶችን ያመነጫል ፡ ያሠራጫል ፡ _ ፯ የንብረት ባለቤት ይሆናል ፡ ውል ይዋዋላል ፡ በስሙ ይከሳል ፡ ይከሰሳል ። ፲፬ . የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ሥልጣንና ተግባር _ ፩ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ከቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የጽሕፈት ቤቱን ሥራዎች ያቅዳል ፡ ይመራል ፡ ያስተዳድራል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር | ሳይወሰን ፡ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ፡ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፫ የተመለከቱትን የጽሕፈት ቤቱን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፡ ለ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ ዓላማዎች በመከተል ቦርዱ በሚያጸድቀው መመሪያ መሠረት የጽሕፈት ቤቱን ሠራተኞች ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፡ ሐ ) የጽሕፈት ቤቱን ዓመታዊ በጀትና የሥራ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፡ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል ፡ መ ) ለጽሕፈት ቤቱ በተፈቀደው በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፡ ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ጽሕፈት ቤቱን ይወክላል ፡ የጽሕፈት ቤቱን ዓመታዊ እና አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ የሥራ ክንውን ሪፖርት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፡ ሰ ) ከቦርዱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከና የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ለጽሕፈት ቤቱ ሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። እርሱን ሙሉ ለሙሉ ተክቶ ከ፴ ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የሚሠራ ኃላፊ ሲወክል ውክልናው በቅድሚያ ለቦርዱ ቀርቦ መጽደቅ አለበት ። ፲፭ በጀት ፩ የጽሕፈት ቤቱ በጀት በመንግሥት ይመደባል ። ፪ የፈንዱ የበጀት ዓመት ከሐምሌ ፩ ቀን ጀምሮ ሰኔ ፴ ቀን ያበቃል ። ፲፮ ስለኦዲት ፩ ለዋናው ኦዲተር በሕግ የተሰጠው ሥልጣን እንደተ ጠበቀ ሆኖ ፡ የፈንዱ ሂሣብ ቦርዱ በሚሰይመው የውጭ ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራል ። ገጽ ፫፻፷፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ የካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 24 6 March 1997 - - Page 366 ፪• ሂሣቡ የሚመረመረው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት | ባለው የሂሣብ ምርመራ መርሆዎችና ሥርዓት መሠረት ሆኖ የኦዲት ሪፖርቱ ቦርዱና የገንዘብ ሚኒስቴር አስተ ያየት እንዲሰጡበት ይቀርብላቸዋል ። ፫• የቴክኒክ ምርመራ በተመረጡ ተግባራት ላይ በየዓመቱ ይከናወናል ። ፲፯ . ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጐች ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማናቸውም ሕግ በዚህ አዋጅ | 17 . Inapplicable LaWS በተደነገገባቸው ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። ፲፰ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፫፱ ዓ . ም . ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻ኵ፱ ዓ . ም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?