×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የመሠረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፵፯/፲፱፻፹፱

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ | ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፪ አዲስ አበባ - - ጥቅምት ፳፩ ቀን ፲፱፻፳፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፵፯ / ፲፱፻T፱ ዓ•ም• የመሠረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅ . . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፪፻፲፰ አዋጅ ቁጥር ፵፯ / ፲፱፻፷፱ የመሠረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኤጀንሲን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የመሠረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ እንዲጐለብትና ለአጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ድጋፍ እንዲሰጥ ማድረግ በማስፈለጉ ፤ | በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | and engineering industries to make the sub - sector contribute መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ፡ | to overall economic development ; ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ « የመሠረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱ | Ethiopia , it is hereby proclaimed as follows : ስትሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፯ ፲፱፻፳፱ » ተብሎ | i Shor Title ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ _ ፩ « የመሠረታዊ ብረታብረት ኢንዱስትሪ » ማለት የማዕድናት | ውጤት የሆኑ የተለያዩ ብረታ ብረቶችን ለሌሎች ኢንዱስት ሪዎች በሚያገለግሉበት ሁኔታ የሚያዘጋጅኢንዱስትሪ ነው ፡ | ፪• « የኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ » ማለት የተለያዩ የኢንጂነሪንግ ውጤት የሆኑ መገልገያ ቁሳቁሶችና የካፒታል ዕቃዎች የሚያመርት ኢንዱስትሪ ነው ፤ ፫ « ውዳቂ ብረታ ብረት » ማለት አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረት ነክ የመከላከያ ወይም የሲቪል መሣሪያዎችና የመሣሪ ያዎች አካላትና መለዋወጫዎች ሲሆኑ ከነዚሁ ጋር የተያያዙ ብረታ ብረት ያልሆኑ አካላትን ይጨምራል ። ያንዱ ዋጋ ) ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፪፻፷፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፫ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም•Federal Negarit Gazeta No . 3 31 October 1996 - page 269 ' ፫ : መቋቋም ፩ የመሠረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ( ከዚህ በኋላ « ኤጀንሲው » እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ : ኤጀንሲው ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ፬• ዋና መሥሪያ ቤት የኤጀንሲው ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላ ጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ሊኖረው ይችላል ። ፭ ዓላማ የኤጀንሲው ዓላማ የመሠረታዊ ብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ እንዲጐለብትና ለአጠቃላይ ኢኮኖሚ ዕድገት ድጋፍ እንዲሰጥ ማድረግ ይሆናል ። ፮ . ሥልጣንና ተግባር ( ኤጀንሲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩• የአገሪቱን የኢንዱስትሪፖሊሲን መሠረት በማድረግ የመሠ ረታዊ ብረታ ብረትና የኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚመራበትን ፖሊሲ የማዘጋጀት ፤ ሲፈቀድም ተግባራዊ ነቱን የመከታተል ፤ ፪• የኢንዱስትሪ ዘርፉእንዲስፋፋ የገበያ ጥናትና የማበረታታት ተግባራትን የማከናወን ፤ ፫• የኢንዱስትሪ ዘርፉን ዕድገትና የሙያ ብቃትን ሊያጐለብት _ የሚችል ቴክኖሎጂና ምርት በመምረጥ ረገድ አገልግሎት የመስጠት ፤ ፩• በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፳፬ በሌላ አኳኋን የተደነገገ ቢኖርም ፡ በኢንዱስትሪ ዘርፉ የተሠማሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን የማምረት አቅም ለማጐልበትና በአግባቡ ለመጠቀም እንዲቻል እንደገና አስተካክሎ የማዋቀርና በአጠቃላይ ስለአደረጃጀታ ቸውና ከፋይናንስ አስተዳደራቸው በስተቀር በሌሎች ጉዳዮች ላይ አመራር የመስጠትና የመቆጣጠር ፤ ፭ በኢንዱስትሪ ዘርፉ የተሠማሩ ድርጅቶችን የማምረት አቅምና የቴክኖሎጂ ብቃት በማጥናት ፤ ሀ ) ቁልፍ የሆኑ ምርቶች የሚመረቱበትን መንገድ የማመ | ለ ) በአገሪቱ ለሚቋቋሙ ፕሮጀክቶች አስፈላጊ የሆኑ ምርቶች አገር ውስጥ እንዲመረቱ ጥረት የማድረግ ፤ ሐ ) አዳዲስ ዲዛይኖችና ምርቶች በአገር ውስጥ የመሥራት አቅም እንዲጐለብት መንገድ የመፈለግና ድጋፍ የማድረግ ፤ መ ) ሌሎች ዲዛይኖችና ምርቶች አገር ውስጥ የሚመረቱ በትን መንገድ የመፈለግና ድጋፍ የማድረግ ። ፮• በኢንዱስትሪ ዘርፉ የግል ባለሀብቶችን ተሳትፎ የማበረ ፯• የኢንዱስትሪ ዘርፉን የምህንድስናና የቴክኒክ ሙያን በሚመ ለከት ጥናት በማካሄድ ለአገሪቱ ተስማሚ የሆነ የሙያ ደረጃ ምደባ የማካሄድ ፤ በኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚሠማሩ የአማካሪዎ ችንና ኮንትራክተሮችን ችሎታና የሙያ ብቃት ማረጋገጥ ፥ የሙያ መስኩ እንዲዳብር የማበረታታት ፣ ፰ : የኢንዱስትሪ ዘርፉን የምርት ጥራት ለማሳደግ የሚያስችል ዘመናዊ የማኔጅመንት የምህንድስናና የአመራረት ዘዴን የማበረታታት ፤ ገጽ ፪፻ኛ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፫ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ፀ• በኢንዱስትሪ ዘርፉ የፕሮጀክት ሃሳቦች በማመንጨትና በማዘጋጀት የምክር አገልግሎት የመስጠት ፤ ፲ በኢንዱስትሪ ዘርፉ ጥናትና ምርምር የማካሄድ የምርምርና ሥርጸት ማዕከላት እንዲቋቋሙ የማበረታታት ፤ ፲፩ : የመንግሥት ንብረት የሆኑ ውዳቂ ብረታ ብረቶች እንዲሰ ባሰቡ ፡ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር እንዲሸጡ የማድረግ ፤ ፪• የንብረት ባለቤት የመሆን ፡ ውል የመዋዋል ፡ በስሙ የመክሰስና የመከሰስ ፤ ፲፫• ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን የማከናወን ። – የኤጀንሲው አቋም ኤጀንሲው ፣ ፩• የሥራ አመራር ቦርድ ፡ ፪• በመንግሥት የሚሾሙ አንድኃላፊና አስፈላጊ የሆኑ ምክትል ኃላፊዎች ፡ እና ፫• አስፈላጊ ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፰• የቦርድ አባላት ቦርዱ ቁጥራቸው በመንግሥት ተወስኖ የሚሾሙ አባላት | ይኖሩታል ። ፀ• የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ : የኤጀንሲውን ሥራዎች በበላይነት ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፤ ፪• የኤጀንሲውን የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅድ እንዲሁም ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት ያጸድቃል ፡ በተግባር መተርጐሙን ያረጋግጣል ፤ • ኤጀንሲው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ( ፩ ) መሠረት የሚመራ ቸውን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በሚመለከቱ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል ፤ ፬• የኤጀንሲውን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያጸድቃል ፤ ፭ በኃላፊው በሚቀርቡ የኤጀንሲውን አስተዳደርና አመራር በሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ይወስናል ። ፲ የቦርዱ ስብሰባ ፩ ቦርዱ በሦስት ወር አንድ ጊዜ ይሰበሰባል ፤ ሆኖም አስፈላጊ • ሆኖ ሲገኝ በሰብሳቢው ጥሪ በማናቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል ። ፪ . በቦርዱ ስብሰባ ላይ አብዛኞቹ አባላት ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ የቦርዱ ውሳኔ የሚተላለፈው በስብሰባው በተገኙ አባሎች በአብዛኛው ድምጽ ሲደገፍ ይሆናል ፡ ሆኖም ድምጹ እኩል ለእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ፬ . የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ቦርዱ የራሱን | 11 . Powers and Duties of the Head of the Agency የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲፩ : የኃላፊው ሥልጣንና ተግባር ፩ ኃላፊው የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ከቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የኤጀንሲውን ሥራ ይመራል ፡ ያስተዳድራል ። ፪ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ኃላፊው ፣ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ የተመለከተውን የኤጀንሲውን ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ ያውላል ፤ ገጽ ፪፻ሮ፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፫ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፲፱፻፴፬ ዓ ም - Federal Negarit Gazeta No . 31October 1996 - page 271 ለ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ ዓላማዎች ተከትሎ ቦርዱ በሚያጸድቀው መመሪያ መሠረት የኤጀን ሲውን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፤ ሐ ) የኤጀንሲውን የሥራ ፕሮግራምና በጀት ያዘጋጃል ፥ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ መ ) ለኤጀንሲው በተፈቀደው በጀት መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረግ ግንኙነት ሁሉ ኤጀን ሲውን ይወክላል ፣ 3 ረ ) የኤጀንሲውን የሥራ እንቅስቃሴና የሂሣብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ። ፫ ኃላፊው ለኤጀንሲው የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ከሥል ጣንና ተግባሩ በከፊል ለኤጀንሲው ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል ። ፲፪• በጀት የኤጀንሲው በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል ፤ | 12 . Budget 3 ፩ በመንግሥት ከሚመደብ በጀት ፤ ፪ : ከሚሰበሰበው የአገልግሎት ክፍያ ፣ እና 3 ፫• ከሌሎች ምንጮች ከሚገኝ ገቢ ። . . . s፲፫ የሂሣብ መዝገብ ስለመያዝ ፥ ፩ ኤጀንሲው የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት | 13 . Books of Accounts _ ይይዛል ። 3 ፪• የኤጀንሲው የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው አዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራል ። ፲፬ . የተሻረ ሕግ ውዳቂ ብረታ ብረቶችና ብረት ያልሆኑ ሌሎች ሜታሎችንም | ለመቆጣጠር የተቋቋመው ቦርድ ቻርተር ( የመንግሥት ማስታ ወቂያ ቁጥር ፩፻፷፮ / ፲፱፻፵፯ ) በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። - ፲፭ መብትና ግዴታ ስለማስተላለፍ ቀደም ሲል የመከላከያ ኢንዱስትሪ ኮሚሽን በኋላም የኢንጂነ ሪንግ ኢንዱስትሪ ኮሚሽን በመባል ይታወቅ የነበረው መሥሪያ ቤት መብትና ግዴታ በዚህ አዋጅ ለኤጀንሲው ተላልፈዋል ። ፲፮ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከጥቅምት ፳፩ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ ።

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?