የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ
ሃያ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፷፰ አዲስ አበባ ሐምሌ ፲፫ ቀን ፪ሺ፱ ዓ.ም
ደንብ ቁጥር ፬፻፮ / ፪ሺ፱ ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ………………… ገጽ
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬፻፮ / ፪ሺ፱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ
ያንዱ ዋጋ
ማቋቋሚያ
፱ሺ፯፻፴፫
፩. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬፻፮ / ፪ሺ፱ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል::
፪. ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ የተለየ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር
ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፩ሺ፱፻፹፬ አንቀጽ ፵፯ (፩) () መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል ።
፩ / “ የአየር ማመላለሻ አገልግሎት ” ማለት መደበኛ ፖስታን የማመላለስ ተግባር ነው፡
፪ / “ ጠቅላላ የአውሮፕላን አገልግሎት ” ማለት መደበኛ ያልሆነ የአየር ማመላለሻ አገልግሎት እና የዚሁ አስፈላጊ ተጓዳኝ ወይም ተያያዥየሆነ በአየር ሊሰጥ የሚችል ሌላ አገልግሎት ነው '
ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣ.ቀ. ፹ሺ፩