የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነጋሪት ጋዜጣ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፴፭ አዲስ አበባ ጥር ፳፬ ቀን ፲፱፻፲፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፯ ፲፱፻፲፭ ዓ.ም የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ . ገጽ ፪ሺ፲፰ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፫ / ፲፱፻፲፭ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፈንድ ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የገጠሩን አካባቢ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማሻሻል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማቅረብ አስፈላጊ በመሆኑ ፣ በብድር ላይ የተመሠረተ የቴክኒክ አገልግሎትና የፋይናንስ ድጋፍ በመሥጠት በገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ተግባር የሚሠማሩ የግል ባለሀብቶችን እና የኅብረት ሥራ ማህበራትን ማበረታታት | cooperative engagement in rural electrification activities አስፈላጊ በመሆኑ ፣ ለዚህ ተግባራዊነት የፋይናንስ ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል ፈንድ ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ አጭር ርዕሰ ይህ አዋጅ “ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፯ ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጥ ካልሆነ በስተቀር በዚህ ኣዋጅ ውስጥ ፤ ፩ . “ ኤጀንሲ ” ማለት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኤጀንሲ ነው ፣ ያንዱ ዋጋ 3.40 ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ • ፰ሺ፩ ገጽ ፪ሺ፲፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፭ ጥር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ፪ . “ ማዕከል ” ማለት በአዋጅ ቁጥር ፪፻፳፱ / ፲፱፻፲፬ የተቋ ቋመው የኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማትና ማስፋፊያ ማዕከል ነው ፣ ፫ “ ኮርፖሬሽን ” ማለት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ነው ፣ ፬ “ ዳይሬክተር ” ማለት የኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማትና ማስፋፊያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ነው ፣ ፭ “ አስፈጸሚ ሴክሬታሪያት ” ማለት የኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማትና ማስፋፊያ ማዕከል ነው ፣ ፮ “ ከግሪድ ውጭ ” ማለት በኮርፖሬሽን ያልተሸፈነ የኤሌ ክትሪክ አቅርቦት ነው ፣ ፯ . “ የገጠር አካባቢ ” ማለት ከግሪድውጭ ያለአካባቢ ነው ፣ ፰ “ መንግሥት ” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ነው ፣ ፱ . “ ሚኒስቴር ” እና “ ሚኒስትር ” ማለት እንደ ቅደም ተከተላቸው የገጠር ልማት ሚኒስቴርእናሚኒስትርነው ፣ ፲ “ ኦፕሬተር ” ማለት ከግሪድ ውጭ ለንግድ ዓላማ ኤሌክ ትሪክ የማመንጨት ፣ የማከፋፈልና የመሸጥ ሥራ የሚሠራ ሰው ነው ፣ ፲፩ . “ ኦፕሬሽን ” ማለት ከግሪድ ውጭ ለንግድ ዓላማ ኤሌክ ትሪክ የማመንጨት ፣ የማከፋፈልና የመሸጥ ሥራ ነው ፣ ፲፪ . “ የገንዘብ ባለአደራ ተቋም ” ማለት ከፈንዱ ልዩ ልዩ ምንጮች የሚሰበሰበውን ገንዘብ የሚያስቀምጥና በቦርዱ ትዕዛዝ ብድር የሚሰጥና ብድሩንም ተቀብሎ በፈንዱ የባንክ ሂሳብ የሚያስቀምጥ ማንኛውም የፋይናንስ ተቋም ፲፫ “ ክልል ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፯ ፩ / የተገለጸ ክልል ሲሆን ፤ ለዚህ አዋጅ ዓላማ አፈጻጸም አዲስ አበባና ድሬዳዋን ይጨምራል ፣ ፲፬ • “ ታዳሽ የኃይል ምንጭ ” ማለት ከተፈጥሮ የሚገኝ በራሱ ወይም በሰው አማካይነት በማያቋርጥ ዑደት ሂደቱን ጠብቆና እንደአስፈላጊነቱ ተተኪም በመሆን ለሰዎች አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውል እንደ የፀሐይ ፣ የነፋስ ፣ የውሃ ፣ የባዮማስና የመሳሰሉት የኃይል ምንጭ ነው ፣ ፲፭ “ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ” ማለት ከግሪድ ውጭ ኤሌክ ትሪክ ማመንጨት ፣ ማስተላለፍ ፣ ማከፋፈል ፣ መሸጥና እነዚህን ለማስፈጸምና ለማስፋፋት የሚከናወኑ ተጓዳኝ ተግባሮች ናቸው ፣ ፲፮ “ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን መርሐ ግብር ” ማለት በገጠር አካባቢ ለፈንዱ ከተቀመጡት ዓላማዎች አንፃር በፈንዱ እየታገዘ የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ለማስፋፋት በቦርዱ የሚጸድቅ የእንቅስቃሴ አቅጣጫ ነው ፣ ፲፯ “ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮጀክት ” ማለት ከግሪድ ውጭ የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ለማዳረስ የሚከናወን የዲዛይን ፣ የግንባታ ፣ የማመንጨት ፣ የማስተላለፍና ሌሎች ተጓዳኝ ሥራዎች ናቸው ፣ ፲፰ “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ፣ ፲፬ “ የአሠራር ወጥነት መመሪያ ” ማለት በፈንዱ ልዩ ልዩ አካላትና ፈንዱን በሚያስፈጽሙ የክልል አስፈጻሚ ጽሕፈት ቤቶች የሚከናወኑ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ተግባራት ወጥነትና ቅንጅት ባለው አኳኋን እንዲሠሩ የሚመራ መመሪያ ነው ። • መቋቋም የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፈንድ ( ከዚህ በኋላ “ ፈንዱ ” እየተባለ የሚጠራው ) ቋሚ የፋይናንስ ምንጭ ሆኖ የገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በሚከፍተው ልዩ የባንክ ሂሳብ ውስጥ ተቀማጭ እንዲሆን በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ወናቸውን ይከታተል ገጽ ሺ፩ደ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፭ ጥር፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም የፈንዱ ዓላማዎች ፈንዱ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፣ በግል ፣ በህብረት ሥራማህበራትና በአካባቢኅብረተሰብ ለሚካሄዱና በተለይም በዋነኝነት ታዳሽ የኃይል ምንጮችን ለሚጠቀሙ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮጀ ክቶች የብድርና የቴክኒክ አገልግሎት መስጠት ፣ በገጠሩ አካባቢ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለምርትና ለማህበራዊ አገልግሎት እንዲውል ማበረታታት ። ፭ የፈንዱ ምንጮች የፈንዱ ምንጮች የሚከተሉት ይሆናሉ ፣ ፩ ከመንግሥት የሚመደብ በጀት ፣ ፪ ከሌሎች መንግሥታት የሚገኝ ብድርና ዕርዳታ ፣ • ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅቶች የሚገኝ ብድርና ፩ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ከሚገኝ ዕርዳታ ፣ ፭ ከሌሎች ልዩ ልዩ ምንጮች የሚገኝ ገቢ ። ክፍል ሁለት የፌዴራል የፈንዱ አካላት ፲ የፈንዱ አካላት ፩ : ፈንዱ በፌዴራል ደረጃ ፤ ሀ ) በገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) ፣ ለ ) አስፈጻሚ ሴክሬታሪያት ፣ ይኖረዋል ቦርዱ ተጠሪነቱ ለሚኒስትሩ ይሆናል፡ ፫ ክልሎች የራሳቸውን የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን አስፈጻሚ ሴክሬታሪያት ሊያቋቁሙ ይችላሉ ፣ ፬ የክልል ኤሌክትሪፊኬሽን ሴክሬታሪያት ጽሕፈት ቤቶች ፣ የየክልሎቻቸው የገጠር ኤሌክትሪፊ ኬሽን ፕሮጀክቶች በዚህ ሕግና ቦርዱ በሚያወጣቸው ልዩ ልዩ መርሐ ግብሮችና መመሪያዎች መሠረት መከና የቦርዱ አባላት ፩ ቦርዱ በመንግሥት የሚሰየሙ አባላት ይኖሩታል ። የቦርዱ አባላት የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ይሆናል ። ሆኖም ማንኛውም አባል ለተጨማሪ የሥራ ዘመናት . እንደገና ሊመደብ ይችላል ። ፫ አንድን የቦርድ አባል መንግሥት በማናቸውም ጊዜ እና ምክንያት ሊያነሳው እና በሌላ ሊተካው ይችላል ። የቦርዱ አባላት ቁጥር በሞት ፣ ሥራን በፈቃድ በመልቀቅ ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት ቢቀንስ ፤ ክፍት ቦታው በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ይሞላል ። ፭ ማንኛውምየቦርድ አባል በቦርዱ ውስጥ ካለው ሥራጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በጥቅም የሚጋጭ ማንኛውንም ተግባር ማከናወን የለበትም ፡፡ በቦርዱ ውስጥ ካለ ሥራ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የጥቅም ግጭት ሲያጋጥመው ይህንኑ ለቦርዱ በማሳወቅ ጉዳዩ ከሚታይባቸው የቦርዱ ስብሰባዎች እራሱን ማግለል ኣለበት ። የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ተግባራት ይኖሩታል ፣ ፩ ሚኒስቴሩን በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ያማክራል ፣ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን መርሐ ግብርን ሥራ ላይ ለማዋል የሚያገለግሉ የአሠራር ሥርዓቶችን ፣ መመሪያ ዎችን ፣ ደረጃዎችንና የፕሮጀክት አፈጻጸም መመሪያ ዎችን ያፀድቃል ። እነዚህኑ በየጊዜው እየመረመረ ተገቢውን ማስተካከያ ያደርጋል ፣ ገጽ ፪ሺ፩፻፩ ፌዴራል ቁጥር ፴፭ ጥር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም ብድር ለመስጠት የሚያስችሉ ግልዕ መመሪያዎች፡ መስፈርቶችና አግባብ ያላቸውን የአሠራር ሥርዓቶች ያፀድቃል፡ ፬ . በዚህ አዋጅ ኣንቀጽ ፲፮ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት ኦፕሬሽናቸውን በኮርፖሬሽኑ አማካይነት ለለቀቁ ኦፕሬ ተሮች ካሳ የሚከፈልበትን መስፈርት አውጥቶ በሚኒ ስቴሩ ያስፀድቃል ፣ ፭ ሪፖርቶችን ይቀበላል፡ ይመረምራል፡ እንደ አስፈላጊነ ታቸው ያፀድቃል ፤ ፈንዱን ያስተዳድራል ፣ ጊ ከልዩ ልዩ የፈንዱ ምንጮች ገቢ የሚደረገውን ገንዘብ በኃላፊነት የሚያስቀምጥ የገንዘብ ባለአደራ ተቋም በሴክሬታሪያቱ ሲቀርብለት ያጸድቃል፡ ስለ ገንዘብ ባለአደራ ተቋሙ ዝርዝር አሠራር መመሪያ ያወጣል ፣ ፬ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ሥልጣንና ተግባሩን ለክልል የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ሴክሬታሪያት ጽሕፈት ቤቶች በውክልና ሊሠጥ ይችላል ፤ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽንን የሚያጠናክሩ ሌሎች ሥራዎች ያከናውናል፡ የቦርዱ ውሳኔዎች፡ መርሐግብሮች እና ለሕዝብ ግልፅ እንዲሆኑ ያደርጋል ፣ በዚህ አዋጅ ኣንቀጽ ፭ ካተጠቀሱት የፈንዱ ምንጮች የሚገኘው ገቢ በሚመለከተው አካል ከጊዜው መሰብ ሰቡን ያረጋግጣል ። የቦርዱ ስብሰባዎች ቦርዱ በየሦስት ወሩ ይሰበሰባል ። ሊቀመንበሩ ሲጠራ በማናቸውም ጊዜ ሌሎች አስቸኳይ ስብሰባዎችን ያደርጋል ። ፪ • ከቦርዱ አባላት ከግማሽ በላይ በስብሰባው ላይ ከተገኙ ምልዐተ ጉባኤ ይሆናል ። ፫ የቦርዱ ውሳኔ ሆኖ የሚፀናው በስብሰባው ከተገኙት ከግማሽ በላይ ድምዕ የሰጡበት ውሳኔ ነው ። እኩሌታ ድምዕ ሲገኝ ሊቀመንበሩ ድምፁን የሰጠበት ወገን አብላጫ ድምዕ ይሆናል ። ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። የአስፈጻሚ ሴክሬታሪያቱ ሥልጣንና ተግባር ኣስፈጻሚ ሴክሬታሪያቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል፡ ፩ . ዓመታዊና አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሪፖርትን በማዘጋጀት በቦርዱ ያስፀድቃል፡ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮጀክት ኦፕሬተሮችን ማመልከቻ ይመረምራል ፣ ቦርዱ ባፀደቃቸው መስፈ ርቶች መሠረት ይወስናል ፣ ፫ . መስፈርቶችን አውጥቶ በውድድር ላይ በተመሠረተ አሠራር ባለአደራ የፋይናንስ ተቋምን ይመርጣል ፤ ይህንኑ እንዲያፀድቀው ለቦርዱ ያቀርባል ፣ ብድር የሚሰጥባቸውን ግልፅ መመሪያዎችና አግባብ ያለውን የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮጀክት ለመምረጥ የሚያስችሉ የምርጫ መስፈርቶችና ሥርዓቶችን አዘጋጅቶ ለቦርዱ በማቅረብ ያስፀድቃል ፣ ፭ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን መርሐ ግብርከሌሎች የገጠር ልማት ተግባራት ጋር እንዲቀናጅ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል ፣ ፮ • በገጠር ውስጥ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲስፋፋ ፣ ለምርትና ማህበራዊ ጥቅም እንዲውል ያደርጋል ፣ ፯ • የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ጣቢያዎችን ለመትከል ፣ ለማን ቀሳቀስና ለማስተዳደር በሚያስችሉ የአቅም ግንባታ ተግባሮች ላይ ከሚመለከታቸው ጋር ይተባበራል ፣ ገጽ ፪ሺ፩፻፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፭ ጥር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ቿ ተቀባይነት ያላቸውንና የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን የደህ ንነት ደረጃና ኢኮኖሚያዊ አቅም ያገናዘቡ ቁሳቁሶችን ፣ መሣሪያዎችንና ቴክኖሎጂን ያዘጋጃል ፣ ይይዛል ። እንዲሁም በመረጃነት እንዲሠራጩ ያደርጋል ፣ ፱ ለፈንዱ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታ ዎችን ያጠናል ፣ ፲ . የቦርዱን የሥራ መዛግብት ፣ ዘገባዎችና የስብሰባ ቃለ ጉባኤዎች ይይዛል ፣ እንዲሁም የቦርዱ ውሳኔዎችና መመ ሪያዎች በትክክል መፈጸማቸውን ተከታትሎ ያረጋ ፲፩ . በዚህ አዋጅከተጠቀሱት የፈንዱ ምንጮች የሚገኘው ገንዘብ በጊዜው መሰብሰቡንና በፈንዱ ሂሳብ ገቢ መደረጉን ያረጋግጣል ፣ ሌሎች ከተግባርና ኃላፊነቱ ጋር የሚገናኙ ሥራዎችን ይሠራል ፣ ፈንዱ በየጊዜው ለሚወጠነው የገጠር ኤሌክትሪፊ ኬሽን ፕሮግራም የበለጠ ውጤታማ በሆነ መንገድ ሥራ ላይ የሚውልበትን እያጠና ለቦርዱ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል ። ፲፩ . የዲሬክተሩ ሥልጣንና ተግባር ዲሬክተሩ ፈንዱን በሚመለከቱ ጉዳዮች ተጠሪነቱ ለቦርዱ ሆኖ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲ የተመለከቱትን የአስፈጻሚ ሴክሬታሪያቱን ሥልጣንና ተግባሮች በሥራ ላይ ያውላል ። ክፍል ሦስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፪ . የአሠራር ወጥነት ፩ የአሠራር ወጥነት እንዲኖር ሁሉም የፈንዱ አሠራሮችና ተግባሮች በአሠራር መመሪያ ይመራሉ ። ቦርዱ የአሠራር መመሪያ ያወጣል ። ፲፫ • የገንዘብ ባለአደራው ተቋም ኃላፊነት ፩ የገንዘብ ባለአደራው ተቋም በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ከተጠቀሱት የፈንዱ ምንጮች የሚገኘውን ገንዘብ በኃላ ፊነት ይይዛል ። ፪ . በቦርዱ ትዕዛዝ ለገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮጀክቶች የሚሰጠውን ብድር ይሰጣል ፣ በብድር የተሰጠ ገንዘብ ሲመለስ ይቀበላል ። ፫ • ተበዳሪዎች የወሰዱት ገንዘብ በጊዜው መመለሱን ይከታ የፈንዱን ገቢና ወጪ የሚያሳይ የሂሳብ መዝገብ ያዘጋጃል ። ይህንኑ ቦርዱ በመመሪያ በሚወስነው ጊዜ ለቦርዱ ያቀርባል ። ፭ ሌሎች ከኃላፊነቱ ጋር አግባብ ያላቸውን ሥራዎች ይሠራል ። ፲፬ . ለገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮጀክቶች ፈቃድ ስለመስጠት ኤጀንሲው አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ለገጠር ኤሌክትሪፊ ኬሽን ፕሮጀክቶች ፈቃድ ይሰጣል ፣ ያድሳል ፣ ያቋርጣል ፣ ይሰርዛል ። ፲፭ ለብድር ብቁ ስለመሆን ከፈንዱ ለመበደር የሚፈልግ ሰው በገጠር ኤሌክትሪክሽን ሥራ ለመሠማራት ብቁ መሆንና ብድር ለማግኘት የሚያ ስችሉ መስፈርቶችን ማሟላት አለበት ። ፲፮ : የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን አልሚዎች ዋስትና ፩ . የኮርፖሬሽኑ የኤሌክትሪክ አቅርቦት በየ፲ ዓመት ምን ያህል የአገሪቱን ክፍል እንደሚሸፍን የሚያሳይ ጠቋሚ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ማስተር ፕላን ማውጣት አለበት ። ገጽ ፪ሺ፩፻፫ ፌዴራል ቁጥር ፴፭ ጥር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም : በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተጠቀሰው የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ማስተር ፕላን ለሕዝብ ግልፅና የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽንን ፕሮግራም በማስፈጸም ረገድ ተገቢ ትኩረት የሚሰጠው መሆን አለበት ። ፫ ኮርፖሬሽኑና ሴክሬታሪያቱ በየዓመቱ እየተገናኙ ለሚኒ ስቴሩና ለኤጀንሲው ከሚያቀርቡት ዓመታዊ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ጠቋሚ ዕቅድ አኳያ ዕቅዳቸውን ያቀናጃሉ ። ፬ የኮርፖሬሽኑ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ሂደት በገጠር ኤሌክ ትሪፊኬሽን ተግባር የተሠማራውን ባለሀብት፡ የኅብረት ሥራ ማህበር ወይም የአካባቢ ኅብረተሰብ ያስለቀቀ እንደሆነ ለአልሚው ፈጣንናትክክለኛካሣይከፈለዋል ። ፲፯ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ደንበኞች መብት ፩ ኦፕሬተሩ ኤጀንሲው በሕግ በተሰጠው ሥልጣን አማካ ይነት ከሚወስነው ኤሌክትሪክ ታሪፍ በላይ አያስከ ፪ የኤሌክትሪክ አገልግሎቱን ከማቋረጡ በፊት ኦፕሬተሩ አግባብ ባለው መንገድ ለደንበኛው ማሳወቅ አለበት ። ፫ ኦፕሬተሩ የኤሌክትሪክ አገልግሎቱን ከማቆሙ ከ፫ ወር በፊት ለኤጀንሲው ማሳወቅ አለበት ። ፬ አግባብ ባለው ሕግ ስለ ኤሌክትሪክ ደንበኞች መብት የተደነገጉት ድንጋጌዎች፡ ለገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ደን በኞችም ተፈጻሚ ይሆናል ። ፲፰ ከብሔራዊ ግሪድ ጋር መያያዝ አስፈጻሚ ሴክሬታሪያቱ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮጀ | 18. Integration to National Grid ክቶች ወደፊት ከብሔራዊ ግሪድ ጋር በሚገናኙበት አቅጣጫ እንዲንቀሳቀሰ ፕላን ያወጣል ፣ ይህንኑ ይመክራል ። ፲፱ የፀደቁ ፕሮጀክቶች ቁጥጥርና ክትትል የአስፈጻሚ ሴክሬታሪያቱእንደአስፈላጊነቱ የገጠር ኤሌክትሪ ፊኬሽን ፕሮጀክቶች ለፕሮጀክቶቹ ክንዋኔ በፀደቀው መርሐ ግብር መሠረት መከናወናቸውን ይቆጣጠራል ፣ ያረጋግጣል ፣ ለፕሮጀክቱ በተገባው ውል መሠረትም አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል ። የመንገድና የመሬት አጠቃቀም የኤሌክትሪክ አዋጅቁጥር፷፮ / ፲፱፻፶፬ ስለመንገድና መሬት አጠቃቀም የሚደነግገው ለገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮጀክ ቶችም ተፈጸሚ ይሆናል ። ፳፩ . የአካባቢ ጥበቃ የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮጀክቶች ዕቅድ ፣ ግንባታ ፣ ሥራና ጥገና የአካባቢ ጥበቃ ሕጐችን ያከበሩ መሆን ኣለባቸው ። ፳፪ ደህንነት ፩ ኦፕሬተሮች ሠራተኞቻቸውን ፣ ሕዝቡንና ንብረቱን ከአደጋ ለመጠበቅ ተገቢ የሆነውን ቅድመ ደህንነት እርምጃ ይወስዳሉ ። ፪ የኤሌክትሪክ አዋጅ ቁጥር ፳፮ / ፲፱፻፫፱ ፣ ደንብ ቁጥር | 2 ) Relevant provisions of safety standards and conditions in ፱ / ፲፱፻፲፩ እና የደህንነት መመሪያዎች በገጠር ኤሌክት ሪፊኬሽን ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ ። ፳፫ • የሂሣብ መዛግብት አስፈጻሚ ሴክሬታሪያቱ የፈንዱን ትክክለኛና የተሟሉ የሂሣብ መዛግብትና አስረጅ ሰነዶችን ይይዛል ። ገጽ ፪ሺ፩፻፬ ፌዴራል ቁጥር ፴፭ ጥር ፳፱ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም. ፳፬ • ኦዲት ፩ . ለዋናው ኦዲተር በሕግ የተሰጠው ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ የፈንዱ ሂሣብ ቦርዱ በሚሰይመው የውጭ ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራል ። ፪ : ሂሣቡ የሚመረመረው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ባለው የሂሣብ ምርመራ መርሆዎችና ሥርዓት መሠረት ሆኖ የኦዲት ሪፖርቱ ቦርዱና የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር አስተያየት እንዲሰጡበት ይቀርብላቸዋል ። ፫ የቴክኒክ ምርመራ ፣ በተመረጡት ተግባራት ላይ በየዓመቱ ይከናወናል ። ፳፭ የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ሰው ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም የመተባበር ግዴታ አለበት ። ፳፮ : ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ፩ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ደንቦችን የሚኒስ ትሮች ምክር ቤት ሊያወጣ ይችላል ። ፪ • ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን በደንቡ በሚወሰነው መሠረት ሚኒስቴሩ ወይም ቦርዱ ሊያወጡ ይችላሉ ። ፳፯ ተፈጻሚ የማይሆኑ ሕጐች ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማናቸውም ሕግ በዚህ አዋጅ በተደነገጉት ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። ፳፰ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ቁጥር ፳፬ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥር ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ