×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፮/፲፱፻፶፮ ዓ•ም• የጉምሩክ አስተላላፊዎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አሥርኛ ዓመት ቁጥር፳፭ አዲስ አበባ -ሐምሌ ፬ ቀን ፲፱፻፶፮ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፮ / ፲፱፻፶፰ ዓም • የጉምሩክ አስተላላፊዎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ገጽ ፪ሺ፰፻፷፮ የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፮ / ፲፱፻፶፮ የጉምሩክ አስተላላፊዎች የሚኒሰቴሮች ምክር ቤት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን 1 pursuant to article 5 of the Definition of powers and duties of በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ እና የጉምሩክ | the executive organs of the Federal Democratic Republic of ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋምና ኣሰራሩን ለመወሰን የወጣውን | Ethiopia Proclamation No. 4/1995 and Article 90 ( 1 ) of አዋጅ ቁጥር ፩ / ፲፱፻፶፬ እንደተሻሻለ በአንቀጽ ፯ ( ፩ ) መሠረት | establishment and modernization of customs Authority ይህንን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የጉምሩክ አስተላላፊዎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፳ / ፲፱፻፲፮ ” ተብሉ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ “ ባለሥልጣን ” ማለት የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥ ልጣን ነው ። “ የፀናንግድ ሥራ ፈቃድ ” ማለት በጉምሩክ አስተላ ላፊነት ሥራ ለመስራት ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚሰጥ ፈቃድ ነው ። “ የብቃት ማረጋገጫ ” ማለት የጉምሩክ አስተላላ ፊነት ሥራ ለማከናወን የሚያበቃ የሰው ኃይል እና የቢሮ አደረጃጀት መሟላቱን ለማረጋገጥ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ነው ። “ የሙያ ማረጋገጫ ” ማለት በጉምሩክ አስተላላ ፊነት ሥራለመሰማራትየሚያስችል በባለሥልጣኑ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ነው ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ • ፰ሺ፩ ገጽ ፪ሺ፰፻፳፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፭ ሐምሌ ፬ ቀን ፲፱፻፶፰ ዓም “ የጉምሩክ አስተላላፊ ” ማለት በኢትዮጵያ የጉምሩክ ክልል ተወስኖ ዕቃዎችን ወደ አገር ከማስገባት ከአገር ከማስወጣት በአጠቃላይ ዕቃዎች በጉምሩክ ክልል ውስጥ ከሚኖራቸው እንቅስቃሴና መጋዘን ከሚከማቹበት ሁኔታ ጋር የጉምሩክ ስነሥርዓት ስለሌላ ሰው ሆኖ የማስፈጸም ተግባር ለማከናወን የሚያስችል የውክልና ሥልጣን የተሰጠው ሰው ነው ። ረ “ የጉምሩክ ስነሥርዓት ” ማለት ወደ አገር የሚገባ ወደ ውጭ አገር የሚላክ ወይም ተላላፊ ዕቃ ከጉምሩክ ወደብ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እንደአግባብነቱ አስመጪው እስከሚረከበው ወይም ከኢትዮጵያ እስ ከሚወጣ ድረስ የሚከናወን ማናቸውም የጉምሩክ አፈፃፀም ሂደት ነው ። ሰ “ የመታወቂያማስረጃ ” ማለትየጉምሩክ አስተላላፊ በባለሥልጣኑና በጣቢያዎች የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት መፈጸም እንዲችል ወደ ግቢ ለመግባት የሚያስችለው ማስረጃ ነው ። ሸ . “ ሰው ” ማለት የሕግ ወይም የተፈጥሮ ሰው ነው ። ቀ . “ ሚኒስቴር ” ወይም “ ሚኒስትር ” ማለት የገቢዎች ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው ። በ • “ አዋጅ ” ማለት የጉምሩክ ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋምና አሰራሩን ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር፳ / ፲፱፻፳፱ እንደተሻሻለ ነው ። ፫ • የተፈጻሚነት ወሰን ይህ ደንብ በማንኛውም የጉምሩክ አስተላላፊ ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ። ክፍል አንድ ሥልጠና ፣ የሙያ ፣ የብቃት ማረጋገጫ ፣ የመታወቂያ ማስረጃ አሰጣጥ ፣ እገዳ እና ስረዛ ፬ . ሥልጠና ፩ . ባለሥልጣኑ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ ለ ዕድሜው ከ 21 ዓመት ያላነሰ በማንኛውም የጉምሩክ ያልተቀጣ ሰው ፣ በየጊዜው በሚያወጣው የሥልጠና ፕሮግራም መሠረት እየመለመለ በጉምሩክ አስተላላፊነት ሥልጠና ይሰጣል ። ፪ ለጉምሩክ አስተላፈነት ሥልጠና የሚያበቃው የትም ህርት ደረጃ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል ። ፫ ባለስልጣኑ እንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠናዎችን ይሰጣል ። ፬ . ባለሥልጣኑ እንደአስፈላጊነቱ የጉምሩክ አስተላላ ፊነት ሙያ ሥልጠና ብቃቱ በተረጋገጠ ተቋም ሥልጠና እንዲሰጥ ማድረግ ይችላል ። ፭ የሙያ ማረጋገጫ ባለሥልጣኑ የጉምሩክ አስተላላፊነት ሥልጠናውን በብቃት ላጠናቀቀ ሰልጣኝ የሙያ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል ። ፮ የብቃት ማረጋገጫ ባለ ' ልጣኑ በዚህ ደንብ በአንቀጽ ፲ ላይ የተመለከቱትን መስፈርቶች ማሟላቱ ለተረጋገጠ ማንኛውም ሰው በጉምሩክ አስተላላፊነት ሥራ ለመሰማራት የሚያስችለውን የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል ። ገጽ ቪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፭ ሐምሌ ፬ ቀን ፲፱፻ ዓም : ፯ የንግድ ሥራ ፈቃድ የሙያ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያለው ማንኛውም ሰው በጉምሩክ አስተላላፊነት ለመስራት የፀና የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው መሆን አለበት ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ ፩ ላይ የተደነገገው ቢኖርም በአዋጁ አንቀጽ ፳፮ ) መሰረት ዕቃዎችን ወደ አገር የሚያስገቡ ወይም ከአገር ውጭ የሚልኩ ድርጅቶች ላይ ተፈጻሚ አይሆንም ። ፰ የሙያ እና የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ስለማገድ እና ስለመሰረዝ ባለሥልጣኑ ለማንኛውም ሰው የሰጠውን የጉምሩክ አስተላላ ፊነት የሙያ እና የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት በዚህ ደንብ በአንቀጽ ፬እና፮ላይየተደነገጉትን ተፃርሮ ማግኘቱ ከተረጋገጠ ለ • ከሙያው ጋር የተዛመዱ ህጎችን መተላለፉ ከተረጋገጠ በዚህ ደንብ ፣ በአዋጁ እና ባለሥልጣኑ በሚያስፈፅ ማቸው ህጎቸ መሰረት የተጣለበትን ግዴታ ወይም ያለበትን ኃላፊነት ካልተወጣ እንደሁኔታው ለጊዜው ለማገድ ወይም ለመሰረዝ ይችላል ። የጉምሩክ አስተላላፊነት መታወቂያ በባለስልጣኑ የሙያ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጠው ማንኛውም የጉምሩክ አስተላላፊየንግድሥራ ፈቃድሲያወጣ ወይም ከቀጠረው የጉምሩክ አስተላላፊ ድርጅት ሲጠየቅ ወይም በዚህ ደንብ በአንቀጽ ፮ ( ፪ ) መሰረት የሚሰራበት ድርጅት ሰራተኛ መሆኑን ሲያረጋግጥ የመታወቂያ ማስረጃ ይሰጠዋል ። ክፍል ሁለት የብቃት ማረጋገጫ አሰጣጥ መስፈርት የብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት የሚያበቁ መስፈሮች በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር ፳፯ / ፲፱፻፳፱ የተደነ ገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የጉምሩክ አስተላላፊነት ስራየንግድ ሥራ ፈቃድ ለማግኘት የሚፈልግማንኛውም ሰው በተጨማሪ የሚከተሉትን ማሟላት አለበት፡ ለሚያከናውነው ሥራቋሚቢሮከበቂየቴሌፎን የፋክስ የኮምፒዩተር እና ተዛማጅ የመገናኛ መሣሪያዎች ፣ ለ . ማናቸውንም መጻጻፎች የሂሣብና የጉምሩክ ሠነዶችን የሚያስቀምጥበት ሥፍራ ፣ የጉምሩክ ሥነ - ሥርዓት የሚያስፈጽሙ የሙያ ማረጋገጫ ማስረጃ ያላቸው ቢያንስ ሁለት ሠራተኞች ባለስልጣኑ በየጊዜው እንደአስፈላጊነቱ በባንክ ሂሳብ ውስጥ እንዲቀመጥ የሚወስነው የገንዘብ መጠን ወይም ተቀባይነት ያለው ዋስትና፡ ፲፩ . የባለስልጣኑ ሥልጣን ባለስልጣኑ የመታወቂያ ማስረጃ አጠቃቀም ፣ እድሳት ፣ እገዳ እና ስረዛ አስመልክቶ በሚያ ወጣው መመሪያ ይወስናል ። ክፍል ሦስት የጉምሩክ አስተላላፊ ኃላፊነትና ግዴታ የጉምሩክ አስተላላፊ ኃላፊነት ማንኛውም የጉምሩክ አስተላላፊ የወከለው ደንበኛ ስለሰጠው ሥልጣን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ሲጠይቅ ለባለስልጣኑ ወዲያውኑ የማቅረብ ግዴታ አለበት ። ገጽ ፪ሺ፰፻፷፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፭ ሐምሌ ፬ ቀን ፲፱፻፶፰ ዓም ለ ደንበኛው በሠነዶች ላይ ማንኛውም ስህተት ወይም ግድፈት በመፈጸም ሕግን አለማክበሩን ካወቀ ሕግ በሚያዘው መሠረት እንዲፈጽም ወዲያውኑ የማማከር ግዴታ አለበት ። የጉምሩክን አስመልክቶ ለደንበኛው የሚሰጠው መረጃ ትክክለኛነት ላይ አስፈላጊውን ትጋት የማድረግ ግዴታ አለበት ። በጉምሩክ በኩል የሚጠየቀውን የቀረጥ ፣ የታክስ እና ሌሎች ክፍያዎችን ወዲያውኑ ለጉምሩክ ይከፍላል ለቀረጥና ታክስ ክፍያውም ከደንበኛው ጋር በተናጠል እና በአንድነት ተጠያቂ ይሆናል ። በማንኛውም የጉምሩክ ጣቢያ ላይ የሚሰራን የጉምሩክ ሹም ወይም ፖሊስ ከማስፈራራት ፣ ከሐሰት ክስ ፣ ከመግባባት ስጦታ ፡ ውለታዎችን ወይም ጥቅም ከመስጠት ወይም ለመስጠት ከመሞከር የመታቀብ ግዴታ አለበት ። አግባብነት ያላቸውን የጉምሩክ መረጃዎችን ከትክክ ለኛው ሥርዓት ውጭ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ማግኘት ፣ ወይም ለማግኘት ከመሞከር የመታቀብ ግዴታ አለበት ። ፲፫ ማስረጃዎችን መያዝ ፩ ማንኛውም የጉምሩክ አስተላላፊ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ስላስፈፀመባቸው ጉዳዮች በሙሉ ፣ ስላከናወ ናቸው የገንዘብ እንቅስቃሴዎች ፣ ስላደረጋቸው የደብዳቤ ልውውጥ እና በአጠቃላይከጉምሩክ አስተላላ ፊነት ሥራ ጋር የተዛመዱ የተሟሉ ሰነዶችን የመያዝ ግዴታ አለበት ። ፪ . ማንኛውም የጉምሩክ አስተላላፊ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ ላይ የተመለከቱትን ሠነዶች በማናቸውም ጊዜ በባለሥልጣኑ የጉምሩክ ሹም እንዲታይና እንዲመ ረመሩ አስፈላጊ ሲሆንም ቅጂዎችን እንዲወሰድ የመፍቀድ ግዴታ አለበት ። ፫ . ማንኛውም የጉምሩክ አስተላላፊ ከስራው ጋር የተዛመዱ ሠነዶችን ለጉምሩክ ስራ አፈጻጸም እስከ አምስት ዓመታት ድረስ ይዞ የማቆየት ግዴታ አለበት ። ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፬ ስለ ክፍያዎች ፩ ባለስልጣኑ ለጉምሩክ አስተላላፊዎች ለሚሰጠው የምስክር ወረቀት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወ ስነው መሰረት ያስከፍላል ። ባለስልጣኑ ለጉምሩክ አስተላላፊዎች ለሚሰጠው ቋሚ ያልሆነ ስልጠና ሚኒስቴሩ በመመሪያ በሚወስነው መጠን ያስከፍላል ። ፲፭ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ የሙያ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ከባለስልጣኑ ኣስቀድሞ አግኝቶ በስራ ላይ በሚገኝ የጉምሩክ አስተላላፊ የዚህ ደንብ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ ። ፲፮ የተሻረ ደንብ የጉምሩክ አስተላላፊነት ሥራ ፈቃድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፲፭ / ፲፱፻፷፮ በዚህ ደንብ ተሽሯል ። ፲፯ መመሪያ ስለማውጣት የገቢዎች ሚኒስቴር ይህንን ደንብ ለማስፈጸም መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ተሰጥቶታል ። ገጽ ፪ሺ፰፻፲ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፭ ሐምሌ ፬ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓም • ፲፰ ቅጣት ይህንን ደንብ የተላለፈ ማንኛውም ሰው ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ አግባብ ባለው የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት ይቀጣል ። ፲፬ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሐምሌ ፬ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?