×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 21439

      Sorry, pritning is not allowed

* መነሻ የሆነው ጉዳይ የአሠሪና ሠራተኛ ሕግን በአዋጅን / ( 4 ° ፋ ነው ፡፡ ክርክሩ የተጀመረው በትግራይ
የሰበር መ / ቁ .21439
ግንቦት 30 ቀን 1998 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ
ሐጉስ ወልዱ ተገኔ ጌታነህ መስፍን ዕቁበዮናስ
ሂሩት መለሰ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ / ቤት ተጠሪ፡- መልአከፀሐይ ዳንኤል ተስፋዬ
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ስጥተናል ፡፡
ለሰበር አቤቱታው መሠረት አድርጎ የቀረበ ክርክር
ብ / ክ / መ / በስሐርቲሳምረ ወረዳ ፍ / ቤት ነው ። ከሣሽ የነበረው የአሁኑ ተጠሪ በአመልካች
ላይ ክስ የመሠረተው ተከሣሽ ከሕግ ውጪ ከስራዬ ያገደኝ ስለሆነ እግዱ ተነስቶ ወደ
ሥራዬ እንዲመልሰኝ ይታዘዝልኝ ፡፡ ውዝፍ ደመወዝንም ይክፈለኝ በማለት ሲሆን ፣
አመልካች ደግሞ
የወሰደው እርምጃ ትክክል
መሆኑን በመግለጽ
ክሱ ውድቅ
እንዲደረግለት ጠይቆአል ፡፡ የወረዳው ፍ / ቤት ክርክሩን ከሰማ በኋላ ፣ ከሣሽ የወሰደው
እርምጃ ከአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁ . 42/85 ውጪ ነው ፡፡ የሚል ምክንያት
በመስጠት ከሣሽ ወደስራው
እንዲመለስ ፤
ያልተከፈለው
/ ውዝፍ ደመወዙንም
እንዲከፈለው ሲል ውሳኔ ሰጥቶአል ፡፡ በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የክልሉ
ከፍተኛ ፍ /
ቤትም እንደዚሁ ክርክሩን የሰማ ሲሆን ፣ በመጨረሻም በወረዳው ፍ / ቤት
ፍራል ጠቅላይ ፍናና በቅ
ትክል ልባዊ
9- ( -3 -ኖሪ
4 ጣለውን ጥያቄ- ለመመለስም ተጠሪ በቤተክርስቲያንዋ ያላቸው
ያ ግ ** ÷ ው ፡፡ ይህ ደግሞ የሚያሳየን የሁለቱ ወገኖች የተሰጠውን ውሳኔ ሽሮአል ። በሌላ በኩል ደግሞ ተጠሪው ለክልሉ ጠ / ፍ / ቤት ይግባኝ በማቅረቡ በዚህ ደረጃም ክርክሩ ከተካሄደ በኋላ ፣ የከፍተኛው ፍ / ቤት ውሳኔ ተሽሮ የወረዳው ፍ / ቤት የሰጠው ውሳኔ ፀንቶአል ፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ የትግራይ ብ / ክ / መ / ጠ / ፍ / ቤት በመ / ቁ .05228 ሐምሌ 27 ቀን 97 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ላይ ነው ፡፡
አቤቱታው በሰበር ችሎት እንዲታይ የተወሰነው ጉዳዩ በመደበኛ ፍ / ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ስር የሚወድቅ ነው ወይስ አይደለም ? የሚለውን የሕግ ጥያቄ ለመመርመር ነው ፡፡
ከስር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር መገንዘብ እንደቻልነው በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ያለው / የነበረው / ግንኙነት በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ሕግ መሠረት ከሚቋቋሙት
ሠራተኛ ግንኙነቶች የተለየ ነው ፡፡ የአመልካች እና የተጠሪ ግንኙነት ምንድነው የስራ ድርሻ ወይም ሃላፊነት ተገቢ ነው ፡፡ እንዳየየነው ተጠሪ የቤተክርስቲያን
መንፈሳዊ አገልጋይ እና አስተዳዳሪ
ግንኙነት የክርስትና ሃይማኖቱን እምነትና ስርዓት መሠረት ካደረገ መንፈሳዊ ግንኙነት
ውጪ መታየት እንደማይችል ነው ፡፡ ይህ የሰበር ችሎት ተመሣሣይ ጉዳይ ቀርቦለት
በሰበር መ / ቁ .18419 ግንቦት 4 ቀን 98 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ ይህን በመሰለ ግንኙነት
በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ
የሚፈጠሩ
አለመግባባቶች የሃይማኖት ተቋማቱ
በሚኖራቸው የአለመግባባት አፈታት ስርዓት የሚታዩ እንጂ በመደበኛ ፍ / ቤቶች የዳኝነት
ስልጣን ስር እንደማይወድቁ
በማስመልከት የሕግ ትርጉም ሰጥቶአል ፡፡ የሰበር ችሎቱ
የሚሰጠው የሕግ ትርጉም በሁሉም ፍ / ቤቶች ላይ / በራሱ ጨምሮ / አስገዳጅነት
እንደሚኖረው የፌዴራል ፍ / ቤቶች አዋጅ ቁ .25 / 88 ን ለማሻሻል በወጣው አዋጅቁ .454 / 97
- ( ታ “ 8
አንቀጽ 2 / 1 / ተደንግጎአል ፡፡ ስለዚህ በዚህ መዝገብ በተያዘው ጉዳይም የተለየ ውሳኔ
ሊሰጥ አይችልም ፡፡
ው ሳ ኔ
1. አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁ .348 / 1 / መሠረት ተሽሮአል ፡፡
2. ግራ ቀኝ ወገኖች በዚህ ክርክር ምክንያት ያወጡት ወጪና የደረሰባቸው
ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
« ብቀላ ርድ ፊት ትክክል ልባጭ
ቀ ፃ – 3 -52

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?