የሰበር መ / ቁ . 17712
ጥቅምት 16 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
3. ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
4. ኣቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- የኦዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጽ / ቤት
መልስ ሰጭ፡- የወ / ሮ ሳድያ እስማዔል ወራሾች
ስለባለሀብትነት ማስረጃ- የባለሀብትነት የርስት የምስክር ወረቀት
ተቃራኒ ማስረጃ፡- የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1195 / 1 / ፣
መ / ሰጭ በስር ፍ / ቤት በቀረበባቸው ክስ በአዲስ አበባ ከተማ
ወረዳ 5 ፣ ቀበሌ ዐ 9 የሚገኘውን የቤት ቁጥር 797 እና 798
የሆኑትን እንዲያስረክቡ
ከተወሰነባቸው በኋላ ኣመልካች በክርክሩ ገብቶ ፍ / ቤቱ
ውሣኔውን እንዲሽር ያቀረበውን ጥያቄ ንብረቶቹ ለመወረሳቸው
ማስረጃ አልቀረበም በሚል ውድቅ በማድረጉና የተሰጠውንም
ብይን የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት በማጽናቱ የቀረበ አቤቱታ ፡፡
ው ሣ ኔ፡- የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት የሰጠውና የፌዴራል
ከፍተኛ ፍ / ቤት ያጸናው ብይን ሰኣብላጫ ድምፅ ተሽሯል ፡፡
1. የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነትን በማወቅ በአስተዳደር ክፍል
ለአንድ ሰው የተሰጠ የባለህብትነት የምስክር ወረቀት ማስረጃ
የተሰጠው ሰው የዚሁ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብት እንደሆነ
ይቆጠራል ፡፡
2. ማስረጃው የተሰጠው ከደንብ
ውጭ በሆነ አሰራር መሆን
ሰተረጋገጠ ጊዜ ከፍ / ብ / ህ / ቁ .1195 የተመለከተው የሕሊና ግምት
ፈራሽ ይሆናል ፡፡
3. በተሰረዘ የባለሃብትነት ምስክር ወረቀት የሚገኝ የባለሀብትነት
መብት አይኖርም ፡፡
ጥቅምት 16 ቀን 1998
የመ / ቁ 17712
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2 አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
3. ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
4. ኔቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጽ / ቤት
ፈጅ ተስፋዬ
ዘመድኩን ቀረበ
ተጠሪ፡- የወ / ሮ ሳድያ እስማኤል ወራሾች እነ ወ / ሮ ሣባህ እብዶ /
ወራሽ አህመድ አብዶ ቀረበ
መዝገቡ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፡፡
ፍ ር ድ
በሰበር ችሎቱ ለቀረበው ክስ መነሻ የሆነው ጉዳይ የተጀመረው
በፌ / መ / ደ / ፍ / ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች በስር በመቃወም አመልካች
በመሆን የሥር ፍ / ቢት ታህሣስ 6 ቀን 1995 ዓ.ም በዋለው ችሎት
በሰጠው ውሣኔ ላይ የተቃውሞ አቤቱታ በማቅረቡ ነው ፡፡ ይዘቱም
ተቃውሞ በቀረበበት ፍርድ ተከሣሽ የሆኑት አቶ አማን መሐመድ
ከመቃወም አመልካች በውል ተከራይተው የሚነግዱበትን በወ . 5 ቀበሌ
9 የቤት ቁ . 797 እና 798 የሆኑትን ንግድ ቤቶች ተቃውሞ በቀረበበት
ፍርድ ከሣሽ የሆኑት ወ / ሮ ሳዲያ የግል ንብረቶች ናቸው በሚል ተከሣሽ
ቤቶቹን ለቀው ለከሣሽ እንዲያስረክቡ እንዲሁም ከየካቲት 7 ቀን 1994
ጀምሮ ያለውን ከራይ እንዲከፍል በማለት ውሣኔ በመስጠቱ
በመቃወም አመልካች ሴቶቹ በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተወረሱ ላለፉት
28 ዓመታት ለአቶ አማን መሐመድ ኣከራይቶ ሊጠቀም መቆየቱንና
ለከሣሽ ተሰጥቶ የነበረው ቁጥር 5127386 የሆነ የባለቤትነት ደብተር
በአ / አበባ አስተዳደር ሥራና ከተማ ልማት ቢሮ የቤቶች ጉዳይ መምሪያ
የተሰረዘ መሆኑን በመግለጽ ተከራክሮ የቆየ ቢሆንም ፍ / ቤቱ ሴቶቹ ስለ
መወረሳቸው የሚያረጋግጥ የመረካከቢያ
አልቀረበም በማለት
የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ አድርጐታል ፡፡
ጉዳዩ በይግባኝ በፌ / ከ / ፍ / ቤት ቀርቦ የነበረ ቢሆንም በተመሣሣይ ሁኔታ የሥር ፍ / ቤትን ውሣኔ አጽንቶታል ፡፡
የአሁን አመልካች በሰበር
በሰበር አቤቱታው የፌ / ከፍ / ቤት በተሰረዘና
ተቀባይነት በሌላው ማስረጃ ላይ ተንተርሶ የሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ
የሕግ ስህተት ያለበት ነው ብሎ ያቀረበው ማመልከቻ የሕግ ትርጉም
የሚያስነሳ ነጥብ ያለው መሆኑን በማመን ጉዳዩ ለሰበር እንዲቀርብ
ተደርጓል ፡፡ የተጠሪ መልስና የአመልካች የመልስ መልስ እንዲቀርብ
ተደርጓል ፡፡
ይህ የሰበር ችሎት ጉዳዩን መርምሯል ፡፡ በዚህ ጉዳይ የሕግ
ትርጉም የሚያስፈልገው ነጥብ ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነትን
በማወቅ በአስተዳደር ክፍል የተሰጠ የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት
በተሰረዘ ጊዜ ውጤቱ ምን ይሆናል ? የሚለው ነው ፡፡
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1195 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ በግልጽ
እንደተመለከተው
የማይንቀሳቀስ
ባለሀብትነትን
በአስተዳደር ክፍል ለአንድ ሰው የተሰጠ የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት
ማስረጃ ለተሰጠው
ሰው ለዚሁ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብት
እንደሆነ
እንደሚያስቆጥረው
ተመልክቷል ፡፡
በአንፃሩ
ማስረጃው
የተሰጠው ከደንብ ውጭ በሆነ አሰራር መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ከፍ ብሎ
በፍትሐብሔር ቁጥር 1195 ላይ የተመለከተው የሕሊና ግምት ፈራሽ
እንደሚሆን የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1196 / 1 / ይደነግጋል ፡፡ በያዝነው
ጉዳይ በሕግ አግባብ ሥልጣን ተሰጠቶት ይህን መሰሉን የባለሀብትነት
ማስረጃ የሚሰጠው ክፍል ቁጥር 5127386 የሆነውን የባለቤትነት
ደብተር የሰረዘው መሆኑ ተረጋግጧል ፡፡ በተሰረዘ የባለሀብትነት ምስክር
ወረቀት ደግሞ የሚገኝ
የባለሀብትነት መብት አይኖርም ፡፡ የተጠሪ
ወራሾችም አውራሻቸው ያልነበራቸውን መብት ሊወርሱ አይችሉም ፡፡
የሥር ፍ / ቤት ከፍ
ሲል በተጠቀሱት የሕግ ቁጥሮች መሠረት
የባለሀብትነት የምስክር ወረቀቱ የተሰረዘ መሆኑን የተረዳው ቢሆንም
የባለቤትነት ደብተሩ መሰረዝ ለአሁኑ አመልካች የሚሰጠው መብት
የለም በማለት የደረሰበት መደምደሚያ መሠረታዊ የሕግ ሥህተት ነው
በማለት ይህንን ፍርድ በድምፅ ብልጫ ሰጥተዋል ፡፡
ው ሣ ኔ
የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ጥቅምት 10 ቀን 1997 ዓ.ም.
ሰመ / ቁ . 15563 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል ፡፡
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ ፡፡ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት
ይመለስ ፡፡
የሐሳብ ልዩነት
ክርክር ውስጥ ተካፋይ መሆን የሚገባው ወይም
በክርክሩ ለመግባት የሚችል እና በክርክሩ ላይካፈልበት የተሰጠው
ፍርድ መብቱን የሚነካበት ማናቸውም ሰው ፍርዱ ከመፈፀሙ በፊት
መቃወሚያ ሊያቀርብበት እንደሚችል በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ ቁ .358 ላይ
ተደንግጓል ፡፡ ከዚህ ድንጋጌ አግባብ አንድ አመልካች ፍርድ ከመስጠቱ
በፊት በነበረው
በነበረው ክርክር ተካፋይ ሊደረግ ይገባው ነበር ፤
ሳይሟገትበት የተሰጠው ፍርድ የእርሱን መብት የሚጎዳ ሆኖ ተገኝቷል
ይሰኝለት
ለአቤቱታው
የቀረበው
የሚያረጋግጥለት እንዲሆን ያስፈልጋል ፡፡
በዚህ በተያዘው ጉዳይ አመልካች በወረዳ 5 ቀበሌ 19 ውስጥ
የሚገኙትን ቁጥር 797 እና 798 የሆኑ የንግድ ቤቶች የተጠሪዎች
አውራሽ እንድትረከብ ሰፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት የተሰጠው
ፍርድ መብቴን የሚጎዳው ነውና ገብቼ ተከራክሬ ፍርዱን እንዳሽር
ይፈቀድልኝ ሲል ይህን የፍ / ብ / ሥ ' “ 58 በመጥቀስ
አቤቱታው ለተጠቀሰው ፍ / ቤት አቅርቧል ፡፡ በቤቶቹ
በቤቶቹ ላይ መብት አለኝ
የሚለው ደግሞ በመንግስት የተወረሱ ናቸው በሚል መሆኑን መዝገቡ
ያስረዳል ። ይሁን
እንጂ ቤቶቹ
በመንግስት
የተወረሱ መሆናቸውን
የሚያሳይለት ማስረጃ አላቀረበም ፡፡ የአቀረበው ሙግትም ይህ ማስረጃ
አለኝ ወይም ነበረኝ በሚል አይነት ፍሬ
ነገር ላይ
የተመሰረተ
አይደለም ፡፡ በሌላም በኩል ንብረቱ ባለቤት የሌለው ጠፍ የሆነ ንብረት
ነው የሚል ክርክርና ማስረጃ የሌለው በመሆኑ ጉዳዩ ከፍ / ብ / ሕ / ቁ .1194
አግባብ ሊታይና የሴቶቹ ባለቤት መንግስት ነው ሊባል
አይደለም ፡፡ ለተጠሪዎች አውራሽ ተሰጥቶ የነበረው የባለቤትነት ደብተር
ተሰርዟል ማለቱ ብቻውንም ለእርሱ መብት የሚሰጠውና አቤቱታውም
ስፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ .358 አግባብ እንዲስተናገድለት ለማድረግ የሚያስችል
አይደለም ፡፡
በኔ እምነት የስር ፍርድ ቤቶች ወደ ዋናው ጉዳይ ተመልሰው
ክርክሩን እንደገና መመርመር ሳያስፈልጋቸው አመልካቹን ወደ ክርክሩ
ለመግባት የሚያስችልህ መብት መኖሩን አላስረዳህም በሚል ከወዲሁ
ጥያቄውን ውድቅ በማድረጋቸው የፈፀሙት የሕግ ስህተት
የለም ፡፡ ስለሆነም ውሣኔያቸው ሊፀና
የሚገባው ነው በማለት ስሜ
በሦስተኛ ተራ የተጠቀሰው ዳኛ አብዛኛው ድምፅ በተሰጠው ውሣኔ
ባለመስማማት በሐሳብ ተለይቻለሁ ፡፡
You must login to view the entire document.