×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 16,3/ 1991 ከሕዝባዊ ቻይና ሪፐብሊክ መንግሥት ጋር ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና ዋስትና ለመስጠት የተደረጎው ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፵፬ አዲስ አበባ - የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፫ / ፲፱፻፵፩ ዓም ከሕዝባዊ ቻይና ሪፐብሊክ መንግሥት ጋር ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና ዋስትና ለመስጠት የተደረገው ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ ገጽ ፩ሺህ፲ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፫ / ፲፱፻፲፩ ከሕዝባዊ ቻይና ሪፐብሊክ መንግሥት ጋር ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና ዋስትና ለመስጠት የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ በሕዝባዊ ቻይና ሪፐብሊክ መንግሥትና በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል ኢንቨስትመንትን ለማስ ፋፋት እና ዋስትና ለመስጠት በግንቦት ወር ፲፱፻፲ ዓ.ም በቤጂንግ ከተማ ስምምነት የተፈረመ ስለሆነ ፡ ስምምነቱ በሚገባ ሥራ ላይ የሚውለው በተዋዋዮቹ ሀገሮች ህጐች መሠረት ስምምነቱ መፅደቁን የሚያረጋግጡ ሰነዶች ልውውጥ ከተደረገበት ዕለት በኋላ ባለው ወር የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ እንደ ሚሆን በስምምነቱ ስለተገለጸ፡ ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓ • ም • ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ ፡ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ ከሕዝባዊቻይና ሪፐብሊክ መንግሥት ጋርኢንቨስት መንትን ለማስፋፋትና ዋስትና ለመስጠት የተደረገው ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅቁጥር ፩፻፲፫ / ፲፱፻፲፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ ብር 230 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ፩ሺህ፲፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፬ የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፵፩ ዓም ፪ ስምምነቱ ስለመጽደቁ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክእናበሕዝባዊ ቻይና ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል ኢንቨስትመንትን ለማስ ፋፋትና ዋስትና ለመስጠት ፤ በግንቦት ወር ፲፱፻፶ ዓም • በቤጂንግ ከተማ የተፈረመው ስምምነት ጸድቋል ። ፫ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን ኃላፊነት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን ስምምነቱ በሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ በዚህ አዋጅ ሥልጣን ተሰጥቶታል ። ፬ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?