×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 274/1994 የኅብረት ሥራ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፳፩ አዲስ አበባ ግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፲፬ ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፻፬ / ፲፱፻፲፬ ዓም የሕብረት ሥራ ኮሚሽን ማቋቋሚያ ገጽ ፩ሺ፯፻፵፰ አዋጅ ቁጥር ፪፻፸፬ / ፲፱፻፶፬ የሕብረት ሥራ ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ በገጠርና በከተማ የሚኖረው ሕዝብ በአካባቢው ሀብት ላይ በመመስረት የተለያዩ ዓይነቶችና ደረጃዎች ባላቸው የኅብረት ሥራ | and urban working people to solve the economic and social ማህበራት በመደራጀት የሚገጥመውን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ | problems they face by themselves depending on local ችግር በጋራ እንዲፈታና በራሱም እንዲተማመን ማድረግ አስፈላጊ | resources and become self - reliant by being organized in በመሆኑ፡ ይህንን ዓላማ ለማስፈጸም በፌዴራል ደረጃ የሚደራጁ የኅብረት ሥራ ማሕበራትን የሚዘግብና በአገሪቱ ውስጥ ላሉ ሕብረት ሥራ ማህበራት እገዛ የሚያደርግ ፣ ሥልጠና የሚሰጥ ፣ | cooperative societies organized at federal level , conducting ምርምር የሚያደርግና ሌሎች ቴክኒካዊ ድጋፎችን የሚሰጥ | research , rendering training and other technical support to የፌዴራል መንግሥት አካል ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ / ፩ / እና በሕብረት ሥራ ማህበራት | of the Constitution of the Federal Democratic Republic of ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፵፯ / ፲፱፻፲፩ አንቀጽ ፲፭ መሠረት | Ethiopia and Article 55 of the Cooperatives Societies የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የሕብረት ሥራ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር | 1. Shor Title ፪፻፻፬ / ፲፱፻፲፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ መቋቋም ፩ . የሕብረት ሥራ ኮሚሽን / ከዚህ በኋላ “ ኮሚሽኑ ” እየተባለ የሚጠራ የሕግ ሰውነት ያለው እራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለገጠር ልማት ሚኒስቴር ይሆናል ። ያንዱ ዋጋ [ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጸ ፩ሺ፯፻፵፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፩ ግንቦት ፯ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም : ፫ : ዋና መሥሪያ ቤት የኮሚሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ይሆናል ። ፬ . የኮሚሽኑ ዓላማ የኮሚሽኑ ዓላማ በገጠርና በከተማ የሚኖረው ሕዝብ በአካ | 4 Objective of the Commission ባቢው ሀብት ላይ በመመሥረት የተለያዩ ዓይነቶችና ደረጃዎች ባላቸው የኅብረት ሥራ ማኅበራት እየተደራጀ የሚገጥመውን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮች በጋራ እንዲፈታ እና በራሱም ላይ እንዲተማመን ማድረግ ይሆናል ። ፭ የኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባራት ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ ፩ . ለሕብረት ሥራ ማኅበራት እንቅስቃሴና ዕድገት የሚበጁ የፖሊሲ ሃሣቦችንና የሕግ ረቂቆችን አዘጋጅቶ ለመን ግሥት ያቀርባል ፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል ፣ ፪ የሕብረት ሥራ ማኅበራት አደረጃጀት በኅብረት ሥራ ማኅበራት አዋጅ ቁጥር ፩፻፵፯ ፲፩ መሠረትና በዓለም አቀፍ የሕብረት ሥራ መርሆዎች መሠረት እንዲደራጁ ያበረታታል ፣ ፫ . በፌዴራል ደረጃ የሚቋቋመውን የሕብረት ሥራ ማሠልጠኛ ተቋም ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ፬ • ባሕላዊና ሀገር በቀል የራስ አገዝ ማኅበራት ወደ ዘመናዊ የሕብረት ሥራማኅበራት የሚያድጉበት ጥናትና ምርምር ያደርጋል ፣ የጥናቱንም ያስተዋውቃል ፣ ያሰራጫል ፣ በተግባር መተርጐሙንም ይከታተላል ፣ ፭ የሕብረት ሥራ ዕሴቶች ፣ መርሆዎች ፣ አደረጃጀት እና ጠቀሜታ በኅብረተሰቡና በትምህርት ተቋማት ይበልጥ እንዲታወቁ ያደርጋል ፣ በፌዴራል ደረጃ የሚቋቋሙ ፣ ሀ ) በልዩ ባህርያቸው ምክንያት በክልላዊ ማህበር መደራጀት የማይችሉና በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ መሠረታዊ ማኅበራት የሚያቋቁሙትን ሕብረት ሥራ ማህበር ፣ ለ ) ሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ክልሎች የሚገኙ ክልላዊ የሕብረት ሥራ ማኅበራት የሚያቋቁሙትን ሕብረት ሥራ ማኅበር ፣ ሐ ) በዚሁ ንዑስ አንቀጽ / ሀ / እና / ለ / መሠረት የተደራጁ ማኅበራት በጋራ የሚያቋቁሙትን የሕብረት ሥራ ማህበር ወይም በዚህ ንዑስ አንቀጽ [ ለ መሠረት የተደራጁ የተለያዩ ማኅበራት በጋራ የሚያቋቁሙትን ሕብረት ሥራ ማኅበር ይመዘ ግባል ፣ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል ፣ ፯ በፌዴራል ደረጃ የሚደራጁ የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ሂሣብ ይመረምራል ፣ ሂሣብ አጣሪም ይመድባል ፣ ሲፈርሱም ከመዝገብ ይሰርዛል ፣ በመላ ሀገሪቱ አንድ ወጥ የሆነ የሕብረት ሥራ ማኅበራት የሂሳብ አያያዝና ምርመራ ሥርዓት እንዲኖር ያደርጋል ፣ ፰ የሕብረት ሥራ ማኅበራት ምርቶች ገበያ እንዲያገኙ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል ፣ በሀገር ውስጥ ሸማቹና አምራቹ በቀጥታ የሚገናኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል ፣ ፬ . የሕብረት ሥራ ማኅበራት ምርቶች ተጨማሪ እሴት ወይም ዋጋ እንዲኖራቸው ፣ ወደ ኢንዱስትሪ ምርትነት እንዲለወጡ እና የእጅ ጥበብ ምርቶች እንዲያድጉ የሙያና የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል ፣ ፲ የአርብቶ አደሩን ሕይወት ለማሻሻል የሚያስችል በባሕሉና በልምዱ ላይ የተመሠረተ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አደረጃጀት እንዲኖር የሙያ እገዛ ያደርጋል ፣ ገጽ ፩ሺ፯፻፲ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፩ ግንቦት፮ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ፲፩ ለሕብረት ሥራ ማኅበራት ዕድገት የሚበጁ ፕሮጀክ ቶችን በማጥናትና በማዘጋጀት እንደአስፈላጊነቱ ከክልሎች ጋር በመተጋገዝ ማኅበራት ድጋፍ የሚያገኙ በትን መንገድ ያመቻቻል ፣ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የሕብረት ሥራ ማኅበራት የምርት ፣ የገበያ ኢንፎርሜሽንና የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል ፣ ፲፫ በክልል ለሚደራጁ ቢሮዎችና የሕብረት ሥራ ማኅበራት የቴክኒክና የሙያ እገዛ ያደርጋል ፣ የሕብረት ሥራ ማኅበራት እንቅስቃሴን እና ዕድገትን ለማፋጠን ከሕብረት ሥራ ማኅበራት ጋር ግንኙነት ካላቸው የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ያደርጋል ፣ ፲፭ እንደየኅብረት ማኅበራቱ ዓይነትና ደረጃ ሊለዋወጥ የሚችል የማህበራት ሞዴል የመተዳደሪያ ደንብ ያዘጋጃል ፣ ያሰራጫል ፣ ፲፮ : ስለሥራው ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያቀርባል ፣ ፲፯ የንብረት ባለቤት ይሆናል ፣ ውል ይዋዋላል ' በራሱ ስም ይከስሳል ፣ ይከሰሳል ፣ ዓላማውን ለማስፈጸም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል ። ፮ . የኮሚሽኑ አቋም ፩ ኮሚሽኑ በመንግሥት የሚሾሙ አንድ ኮሚሽነርና አንድ ምክትል ኮሚሽነር ፣ እና ፪ አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፯ ስለኮሚሽነሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ ኮሚሽነሩ የኮሚሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን የኮሚ ሽኑን ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል ። ፪ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽነሩ ፣ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ የተመለከተውን የኮሚሽኑን ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ ያውላል ፣ ለ ) በፌዴራሉ የሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት የኮሚ ሽኑን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ሐ ) የኮሚሽኑን የሥራ ፕሮግራሞችና በጀት ያዘጋጃል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፣ መ ) ለኮሚሽኑ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፣ ሠ ) ኮሚሽኑ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ሁሉ ኮሚሽኑን ይወክላል ፣ ረ ) ስለኮሚሽኑ የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ያቀርባል ። ፫ ኮሚሽነሩ ለኮሚሽኑ የሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለኮሚሽኑ ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍይችላል ። ፰ ስለምክትል ኮሚሽነሩ ሥልጣንና ተግባር ምክትል ኮሚሽነሩ ፣ ፩ ኮሚሽነሩ በማይገኝበት ጊዜ ኮሚሽነሩን ተክቶ የኮሚ ሽኑን ሥራ ይሠራል ፣ ፪ . በተጨማሪ ከኮሚሽነሩ የሚሰጠውን ሥራ ያከናውናል ። ፬ . በጀት የኮሚሽኑ ገቢ ፣ ሀ ) በመንግሥት ከሚመደብ በጀት ፣ ለ ) ከሀገር ውስጥና ከውጭ ከሚገኝ እርዳታና ከሌሎች ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል ። ፲ የሂሣብ መዛግብት ፩ ኮሚሽኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። ገጽ ፩ሺ፯፻፶፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፩ ግንቦት ፯ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ፪ የኮሚሽኑ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማናቸውም ሕግ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። 15 መብትና ግዴታ ስለማስተላለፍ በዚህ አዋጅ የተሸፈኑጉዳዮችን በተመለከተ የሌሉች የመን ግሥት አካላትመብቶችና ግዴታዎች በዚህ አዋጅለኮሚሽኑ ተላልፈዋል ። አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከግንቦት ፳ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። . " አዲስ አበባ ግንቦት ፯ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?