ስለውል አፃፃፍ / ፎር ዓይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ስለሚመለከቱ ውሎች - የማይንቀሳቀሱ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
የመ / ቁ .15992 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
ወ / ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት መልስ ሰጪ፡- ወ / ት ሶስና አስፋው
ስለ ውል አፃፃፍ ነፃነት ስለ ውል አጻጻፍ ፎርም / የተሰጠ ደንብ
አለመፈጸም የሚያስከትለው
ንብረቶችን ስለሚመለከቱ ውሎች - በስምምነት ስለሚሆን ያጻጻፍ አይነት
የውል ጽሁፍ አኳኋን / ፎርም /
- የግዴታዎች ቀሪ መሆን - ስለ ይርጋ
የፍትሐብሔር ህግ ቁጥሮች 1719፣1720 / 1 / 1723 ፣ 1726 ፣
በአመልካችና መ /
ሰጭ መካከል የተደረገው የኪራይ ውል በሁለት ምስክሮች
ያልተረጋገጠ በመሆኑ በፍትሐብሔር ህግ ቁጥሮች 1726 / 1 / እና 1727 / 1 / መሰረት
የውል ረቂቅ እንጅ አስገዳጅነት የለውም ፧ አመልካች ከጠየቀው ኪራይ ውስጥ እስከ
8/2/89 ያለው መጠየቅ ከሚችልበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት አመት ያለፈው በመሆኑ በይርጋ
ይታገዳል በማለት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት የሰጠውን ውሳኔ የፌዴራል
ከፍተኛ ፍ / ቤት በማጽናቱ የቀረበ አቤቱታ
ው ሳ ኔ፡- የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት የሰጠውና የፌዴሪል ከፍተኛ ፍ / ቤት
ያፀናው ውሳኔ ተሽሯል ፡፡
1- በኢትዮጵያ የውል ህግ ውል አመሰራረት ደንቦች መሰረት በህግ ወይም በተዋዋዮች
በራሳቸው የተለየ ፎርም ካልተፈለገ በቀር ለውል መመስረት በሁለት ተዋዋዮች
መካከል የስምምነት መኖር ብቻ በቂ ነው ፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሚመለከት የሚደረግ ውል ባለቤትነትን / Ownership /
የአላባ ጥቅምን / usufruct / ፣
መያዥን / mortgage / ወይም ሌላ አገልግሎትን
/ servitude / ለማቋቋም ወይም ለማስተላለፍ የተደረገ ካለሆነ በቀር የግድ በህግ
በተመለከተው አጻጻፍ / ፎርም / መከናወን የለበትም ፡፡ የኪራይ ውል ከነዚህ ውሎች
ውጭ በመሆኑ ከተዋዋዮች ስምምነት ካልሆነ በቀር በህጉ የተለየ አጻጻፍ / ፎርም /
የሚጠይቁት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ አይሆኑበትም ፡፡
የህግ ግምት ድንጋጌዎች ከይርጋ ድንጋጌዎች የተለዩ ናቸው ፡፡
የመዝገብ ቁ .15992 ሐምሌ 19 ቀን 1997
ዝገብ የቀረበውን ጉዳይ መርምሮ ችሎቱ የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥቷል ፡፡
ሰውሣኔ የተሰጠው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ መንበረፀሐይ ታደሰ
ፍሥሐ ወርቅነህ አብድልቃድር መሐመድ ስንዱ ዓለሙ
ሂሩት መለሰ አመልካች ኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት መልስ ሰጪ -- ወ / ት ሶስና አስፋው
ለሰበር ለቀረበው ጉዳይ መነሻ የሆነው ፍርድ ቤት ሲሆን የውሣኔውም ይዘት የኪራይ ውል የቤት ) በሁለት ምስክሮች ፊት ካልተረጋገጠ በፍትሐብሄር ህግ ቁጥር 1727 ( 2 ) እና 1726 ( 1 ) መሠረት የውል ረቂቅ እንጂ አስገዳጅነት አይኖረውም ፣ በመሆኑም ከሣሽ ማስረጃዬ ነው ብሎ ያቀረበው ሰነድ ይህን ስለማያሟላና በአመልካችና በተጠሪ መካከል የኪራይ ውል አለ ሊባል ስለማይችል ከሣሹ ኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት የአሁን መልስ ሰጭ ከ 23 / 5 / 70 እስከ 3 ዐ / 1 / 91 ያልተከፈለ ኪራይ ሂሣብ ብር 65,790.67 እና ወለድ ብር 168,785.90 በድምሩ ብር 234,576.57 እንድትከፍል ያቀረበው ክስ ፍ / ቤቱ አልተቀበለውም የሚል ነው :: ይኸው ፍ /
ቤት ተከሣሽ ያቀረበችውን ይርጋን የሚመለከት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መሠረት በማድረግ ከሣሽ ከጠየቀው ክፍያ ውስጥ እስከ 8/2/89 ድረስ ያለው በይርጋ ይታገዳል በማለት ቀደም ሲል በ 23 / 10 / 92 ብይን ሰጥቷል ፡፡
ኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ይህን ውሣኔ በመቃወም ለከፍተኛው ፍ / ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ለሰበር ችሎቱ የሰበር ማመልከቻ አቅርቧል ፡፡
መመስረት ሕጉ የሚጠይቀውን መስፈርት በተመለከተ ፤ የሰበር ችሎት በዚህ የክርክር ሂደት
1 ኛ . ይርጋን አስመልክቶ የተሰጠው ትዕዛዝ
2 ኛ . የኪራይ ውል በሁለት ምስክር ፊት ካልተረጋገጠ አይፀናም በማለት የሰጠው ውሣኔ የህግ ትርጉም የሚያስነሱ በመሆናቸው ጉዳዩ በሰበር ቀርቦ እንዲታይ አድርጓል ፤ በዚህም መሠረት መልስ ሰጪ መልሱን ፣ አመልካች ደግሞ የመልስ መልሱን እንዲያቀርቡ አድርጓል ::
የሰበር ችሎት በቀረበለት ጉዳይ የህግ ትርጉም የሚሹትን ነጥቦች ከፍሬ ነገር ጉዳዮች በመለየት ተመልክቷል ፡፡ በዚህም መሠረት ፣ 1 ኛ . የሚፀና የኪራይ ውል ለመመስረት መሟላት ያለበት የህግ መስፈርት ምንድነው ? 2 ኛ . በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2024 የተመለከተው የሕግ ግምት ክስን በይርጋ
ከሚያግደው ድንጋጌ ( 1845 ) ያለው ግንኙነት ምንድነው ? የሚሉትን የሕግ ነጥቦች
መርምሮአል :: የሚፀና የኪራይ ውል
ከላይ እንደተገለፀው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት ከሣሽ ያቀረበውን ክስ ውድቅ ያደረገው በከሣሽ በኩል የቀረበው ሰነድ በሁለት ምስክሮች አልተፈረመም በማለት ነው ::
የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1719 ( 1 ) “ በጠቅላላው ሥርዓት በሁለት ወገን ተዋዋዮች በማናቸውም ሁኔታ የተደረገ ስምምነት ውል ለማድረግ በቂ ነው » በማለት ይደነግጋል ፡፡ ከዚህ ድንጋጌ በግልጽ ለመገንዘብ እንደሚቻለው በሁለት ተዋዋዮች መካከል በህግ የሚፀና ሕጋዊ ውጤት ያለው ውል ለመመስረት በሁለቱም መካከል ስምምነት መኖሩ ብቻ በቂ ነው :: ስለዚህ በኢትዮጵያ የውል ሕግ ውል አመሰራረት መሠረታዊ መርህ ወይም በተዋዋዮች በራሳቸው የተለየ ፎርም ካልተፈለገ በስተቀር ለውል መመስረት በሁለት ተዋዋዮች መካከል የስምምነት መኖር ብቻ በቂ ነው የሚለው ነው :: በመሆኑም አንድ ውል ህጉ ያስቀመጠውን የፎርም መስፈርት አያሟላም ተብሎ ወድቅ ሊደረግ የሚችለው ይህን ውል የሚመለከት በግልጽ የተቀመጠና የተለየ የአጻጻፍ ሥርዓት ( ፎርም ) መኖሩ ሲረጋገጥ ብቻ ነው :: ህጉ የተለየ ጽሁፍ የሚጠይቅ በሆነ ጊዜ ይኸው ሥርዓት እስካልተሟላ ድረስ ውሉ እንደረቂቅ ከሚቆጠር በቀር በተዋዋዮች መካከል የሚፀናና አስገዳጅነት ያለው ህጋዊ ግኑኝነት ሊመሰረት አይችልም ( 1720 ) ፡፡ ለመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት ውሣኔ መሠረት የሆነው ይኸው የሕግ ድንጋጌ አስገዳጅ የሕግ ድንጋጌ ነው :: ሆኖም ይህ ድንጋጌ ተፈጻሚነት የሚኖረው ሕጉ የተለየ ፎርም የግድ
በሚልባቸው ውሎች ብቻ ነው :: በመሆኑም መጀመሪያ መታየት ያለበት ነጥብ የኢትዮጵያ ህግ ቤትን አስመልክቶ የሚደረግ የኪራይ ውል በተለየ ፎርም እንዲከናወን ይጠይቃል ወይስ አይጠይቅም የሚለው ነው ?
ስለ ውል አጻጻፍ ( ፎርም ) የሚመለከተው የፍትሐብሔር ሕግ ክፍል ( አንቀጽ 1719 173 ዐ ) የኪራይ ውል የተለየ ፎርም መከተል እንዳለበት የሚያስገድድ ድንጋጌ የለውም :: በፍርድ ቤቱ በቀጥታ ባይጠቀስም ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ያለው ድንጋጌ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ስለሚመለከቱ ውሎች የሚደነግገው አንቀጽ 1723 ነው :: ሆኖም ይህም በማይንቀሳቀስ ንብረት አስመልክቶ የሚደረጉ እንዲኖራቸው የሚጠይቅ ቢሆንም የኪራይ ውልን ግን የሚያጠቃልል አይደለም :: ከሕጉ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለው በዚሁ ድንጋጌ መሠረት የተለየ ፎርም እንዲከተሉ የሚፈለጉት ውሎች የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከቱ ሁሉም ውሎች ሳይሆኑ በድንጋጌው ውስጥ ተለይተው የተቀመጡ ውሱን የውል ዓይነቶች ናቸው :: አግባብነት ያለው የቁጥር 1723 ድንጋጌ የሚከተለውን ይዘት የያዘ ነው ::
1723 ( 1 ) “ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ባለቤትነት ወይም ባንድ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ
የአለን ጥቅም መብት ወይም የመያዣ ወይም የሌላ አገልግሎት መብት ለማቋቋም ወይም ለማስተላለፍ የሚደነግጉት ውሎች ሁሉ በጽሁፍና በሚገባ አኳኋን በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ፊት
መሆን አለባቸው » :: ከዚህ ድንጋጌ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚደረግ ውል በተለየ ፎርም እንዲፈጸም ግድ የሚሆነው ውሉ -
1. ባለቤትነትን ( ownership ) 2. የአላባ ጥቅምን ( usufruct ) 3. መያዣን ወይም ( mortgage ) 4. ሌላ አገልግሎትን ( servitude ) ለማቋቋም ወይም ለማስተላለፍ የተደረገ እንደሆነ ብቻ ነው :: አንድ ውል የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከትም ቢሆን ከእነዚህ ውሎች በአንዱ ውስጥ የሚካተት እስካልሆነ ድረስ በተለየ ፎርም መከናወን ለበትም :: ከእነዚህ ውሎች በአንዱም ውስጥ ከማይካተቱና በዚህም ምክንያት የተለየ ፎርም ከማያስፈልጋቸው ውሎች መካከል የኪራይ ውል አንዱ ነው :: የኪራይ ውል የባለቤትነት ማስተላለፍን የሚመለከት አይደለም :: የአላባ ጥቅምን ፣ መያዣን ወይም ሌላ አገልግሎት ( servitude ) ለማቋቋም ወይም ለማስተላለፍ የሚደረግም አይደለም ፡፡ በመሆኑም የተለየ ፎርም የሚጠይቀው የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1723 ( 1 ) የቤት ኪራይን ለሚመለከቱ ውሎች አግባብነት የለውም ::
ተዋዋዮች ጠ ... 4 በሌላ በኩል ሕጉ ከሚያስቀምጠው አስገዳጅ ፎርም ውጪ ተዋዋይ ወገኖች የውላቸው አፈጻጸም ሊወስኑት እንደሚችሉ የፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 1719 ( 3 ) ይደነግጋል ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ተዋዋዮቹ ሕጉ የማያስገድደውን ፎርም ለመፈፀም የተስማሙ እንደሆነ ውሉ ፍጹም የሚሆነው የተስማሙበትን የውላቸውን አፈጻጸም ሞልተው ሲዋዋሉ ብቻ እንደሆነ የሕጉ ቁጥር 1721 ይደነግጋል :: በዚህ ህግ መሠረት የፎርሙን ዓይነትና ይዘት የሚወስኑት ተዋዋዮቹ ራሳቸው በመሆናቸው ሊከተሉ ስለፈለጉት ፎርም በመካከላቸው ግልጽ የሆነ ስምምነት መኖር ይገባዋል ፡፡ በቁጥር 1719 እንደተገለፀው በመርህ ደረጃ ውል ለመዋዋል የስምምነት መኖር ብቻ በቂ በመሆኑ ውሉን እንዲፀና ተዋዋዮቹ እንዲፈፀም የፈለጉት ተጨማሪ ፎርማሊቲ ምን እንደሆነ ማወቅ የሚቻለው ተዋዋዮቹ ባደረጉት ውል ብቻ ነው :: ስለዚህ የፎርሙን አይነት የምስክሮቹን ብዛት ፣ የመዝገብ አስፈላጊነት ፣ አዋዋይ ፊት ስለመቅረብ ወ.ዘ.ተ ተዋዋዮች በፍላጎት የጨመሩት ፎርም ስለመኖሩ በተዋዋዮቹ መካከል ከተደረገው ስምምነት መገንዘብ መቻል አለበት ::
በጽሁፍ ካሰፈሩ የጽሁፉን ፎርማሊቲ እንደፈለጉ መገመት ቢቻልም ይህ በጽሁፍ የሰፈረው ስምምነት በምስክሮች እንዲረጋገጥ ወይም እንዲመዘገብ ፣ ወይም አዋዋይ ፊት እንዲቀርብ መፈለጋቸውን የሚያሳይ አይሆንም ፡፡ በጽሁፍ ከመሆኑ በተጨማሪ ሌሎቹንም ፎርማሊቲዎች እንዲሟላ መፈለጋቸው በጽሁፍ በራሱ ወይም በሌላ መልክ ስምምነት መኖሩን የሚያሳይ ነገር መኖር አለበት ::
በመሆኑም ተዋዋዮች በጽሁፍ መዋዋላቸውን ብቻ መሠረት በማድረግ ውሉ በምስክሮች ካልተረጋገጠ አይፀናም ተዋዋዮቹ ያልፈለጉትንና ያልተስማሙበትን ፎርም ከፍላጎታቸው ውጪ እንዲጫንባቸው ማድረግ ስለሚሆን ትክክለኛ ሕጉን የተከተለ አተረጓጎም አይደለም :: ውሉ በሁለት ምስክሮች ፊት ካልተረጋገጠ አይፀናም የሚለው የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1727 ( 2 ) ተፈጻሚ የሚሆነው ውሉ በጽሁፍ እንዲሆን ግዴታ የጣለ እንደሆነ ወይም ተዋዋዮቹ በስምምነት በሁለት ምስክር ፊት እንዲረጋገጥ ሲፈልጉ መሆን አለበት :: ከዚሁ ውጪ ተዋዋዮች የፈረሙት ሰነድ በመካከላቸው የውል ግንኙነት ለመመሥረት በቂና ብቸኛ ፎርም አድርገው ከተቀበሉት ፍርድ ቤቶች ፍላጎታቸውን ከማስፈፀም ውጪ ሌላ ተጨማሪ ፎርም ሊጠይቁ አይገባም ::
የማይንቀሳቀስ ንብረት ኪራይ የሚመለከተው የፍትሐብሔር ህጉ ሌላው ክፍልም ቤትን የሚመለከት የኪራይ ውል የተለየ ፎርም እንዲከተል የሚያስገድድ ድንጋጌ የለውም :: ( ቁጥር 2896 -3 ዐ 18 ) :: ይልቁንም የዚሁ ክፍል አካል የሆነው አንቀጽ 2898 የሚደነግገው የኪራይ ውልን ለማረጋገጥ ስለሚያስፈልገው የማስረጃ አይነት እንጂ የሚፀና የኪራይ ውል ለመመሥረት መኖር ስለሚገባው ጽሁፍ ( ፎርም ) አይደለም :: የዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 « ቢሆንም የኪራዩ ውል የመከናወኑን ጊዜ ጀምሮ እንደሆነ ይህ ውል መኖሩን ምስክሮች ማቅረብ ወይም በግምት አስተያየት ለማስረዳት ይቻላል ” በማለት ስለሚደነግግ የኪራይ ውል መኖሩን ለማረጋገጥ ምስክሮች ማቅረብ የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለ ያመለክታል ፡፡ ይህም ቀድሞውኑ የሚፀና የኪራይ ውል ለመመስረት የተለየ ፎርም መኖር አስፈላጊ አለመሆኑን ይበልጥ የሚያረጋግጥ ነው :: በመሆኑም የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ህጉ የማይጠይቀውን የፎርም መስፈርት መሠረት በማድረግ አመልካች ያቀረበው ሰነድ ረቂቅ እንጂ የሚፀና ውል አይደለም ማለቱ የውል ህጉን በተሣሣተ መንገድ መተርጎሙን የሚያመለክት ነው :: ከላይ እንደተብራራው የኪራይ ውል ልዩ ፎርም የሚጠይቅ ባለመሆኑ በአመልካች በኩል ቀረበ የተባለው ሰነድ በሁለት ምስክር አለመፈረሙ ብቻውን ውል የለም ወደሚል መደምደሚያ የሚወስድ አይደለም :: የፍትሐብሔር ሕጉ አንቀጽ ጽ 2898 ( 0 የኪራይ ውል ለማስረዳት የጽሁፍ ማስረጃ እንደሚጠይቅ ግልጽ ነው ፡፡ ሆኖም ለማስረጃነት የሚፈለገው ጽሁፍ ለውሉ መጽናት ( validity ) ከሚፈለገው ጋር ተመሳሳይ ፎርማሊቲ እንዲኖረው ሕጉ አይጠይቅም :: በመሆኑም ለማስረጃነት የሚፈለግ ሰነድ የግድ በሁለት ምስክሮች መፈረም አለበት ሊባል አይችልም :: ለማስረጃነት የሚፈለግ ሰነድ ያስረዳል የተባለውን ፍሬነገር ለማረጋገጥ የሚያስችል ተአማኒነት እስከአገኘ ድረስ ፍርድ ቤቱ የግድ በምስክሮች ፊት አልተፈረመም ወይም ለውል መጽናት የሚፈለጉትን ሌሎች መስፈርቶች አላሟላም በማለት ዋጋ እንዲያጣ ለማድረግ የሚያስችለው የህግ ድጋፍ የለውም ::
ስለዚህ 1 ኛ . የኪራይ ውል በጽሁፍ መሆን እንዳለበት የሚያስገድድ ህግ ስለሌለ
2 ኛ.ተዋዋዮች በጽሁፍ መዋዋላቸው ብቻውን ምስክርም እንዲኖር መፈለጋቸውን
ስለማያሳይ ፣
3 ኛ . ለማስረጃነት የሚፈለግ በምስክር መረጋገጥ ስለሌለበት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት አመልካች ያቀረበውንና ማስረጃዬ ነው ያለውን የውል ሰነድ የፍትሐብሔር ሕጉን አንቀጽ 1720 ( 1 ) እና 1727 ( 2 ) በመጥቀስ ረቂቅ እንጂ አስገዳጅነት ያለው ውል አይደለም ማለቱ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት አተረጓጎም በመሆኑ ይህ ፍርድ ቤት አልተቀበለውም ::
የሚያደርግ ሥርዓት ነው ::
► 2020-2024 ባሉት ድንጋጌዎች የተለያዩ በሕግ ግምትና በይርጋ ድንጋጌዎች መካከል ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ከዚህ ሌላ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት የቀረበለትን ጉዳይ ሲመለከት አመልካች ከጠየቀው ክፍያ እስከ 8/2/89 ድረስ ያለው በይርጋ ታግዷል በማለት ብይን ሰጥቷል ፡፡ በዚህም ረገድ ፍርድ ቤቱ በፍትሐብሔር ሕግ 2024 የተቀመጠውን የሕግ ግምት ( presumption of payment ) የተለየ ይዘትና ዓላማ ካለው የይርጋ ሕግ ያ eriod of limitation ) ጋር በማምታታት መሠረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀሙን ያመለክታል ፡፡ የይርጋ ሕግ አንድ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ጉዳይ ፍሬ ነገር መመርመር ሳያስፈልገው አንድን ክስ ውድቅ የሚያደርግበት ሥርዓት ሲሆን የሕግ ግምት ግን ጉዳዩ ፍርድ ቤት ቀርቦ በተከራካሪዎች መካከል የቀረበው ማስረጃ ሲመዘን ተፈጻሚ የሚሆን ደንብ ነው :: በመሆኑም አልፎ አልፎ የውጤት መመሳሰል የሚያጋጥም ቢሆንም የሕግ ግምትን ተፈጻሚ ለማድረግ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ፍሬ ነገርና አግባብነት ያለውን ሕግ መመርመር የግድ የሚል ሲሆን ይርጋ ግን ጊዜውን በመቁጠር ብቻ ክሱ በፍሬ ነገር ደረጃ እንዳይሰማ የፍትሐብሔር ሕጉ
የህግ ግምቶች አስቀምጧል ፡፡ እነዚህ የሕግ ግምቶች እንደብዙዎቹ የህግ ግምቶች አንድ ክስ ለችሎት ቀርቦ በሚታይበት ወቅት የማስረዳት ሸክም ያለው ማነው ? በሕግ የሰፈረውን ግምት ማፍረስ የሚቻለው እንዴት ነው ? ወ.ዘ.ተ. የሚሉትን ማስረጃን የሚመለከቱ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች እንጂ አንድ ጉዳይ በጊዜ ማለፍ ምክንያት ክስ እንዳይቀርብበት የሚከለክሉ የይርጋ ደንቦች አይደሉም :: በመሆኑም ሁለት ዓመት ያለፈው ዕዳ እንደተከፈለ የሚቆጥረው አንቀጽ 2 ዐ 24 ሁለት ዓመት ካለፈው በጉዳዩ ላይ የሚቀርበውን ክስ በይርጋ የማገድ ውጤት የለውም :: አንድ ክስ በይርጋ ተቋርጧል ወይስ አይቋረጥም የሚለውን በሚመለከት ( ተከሣሹ በ 2024 በተቀመጠው ድንጋጌ ተጠቃሚ በሆነባቸው ጉዳዮችም ጭምር ) ተፈጻሚ የሚሆነው የውልን ግንኙነት የሚመለከተው አጠቃላይ የይርጋ ሕግ ነው :: አጠቃላይ የይርጋ ገደብ ደግሞ በ 1845 እንደተደነገገው 1 ዐ ዓመት ነው :: በዚህ መሠረት አንድ ክስ በይርጋ የሚታገደው ክሱ ከመቅረቡ ከአስር ዓመት በላይ ሲሆን እንጂ ሁለት ዓመት የሞላው እንደሆነ አይደለም :: ከሁለት ዓመት በላይ እና ከአስር አመት በታች ባለው ጊዜ ውስጥ የሚገኘውና በክሱ የተጠቃለለው ክፍያ በቁጥር 2024 በተቀመጠው የሕግ ግምት የሚሸፈን በመሆኑ ከሣሹ የማስረዳት ሸክሙን መወጣት አለመወጣቱን በመርመር ፍርድ ቤቱ በፍሬነገሩ ውሣኔ የሚሰጥበት እንጂ ከወዲሁ በይርጋ ታግዷል በማለት ወደ ሥረ ነገሩ ሳይገባ ከክርክር ውጪ የሚያደርገው አይደለም ::
በመሆኑም በዚህም ረገድ ፍርድ ቤቱ ክስ የቀረበበትን ጊዜ መሠረት በማድረግ እስከ 8/2/89 ድረስ ያለው ሂሣብ በይርጋ ይታገዳል ማለቱ ትክክል አይደለም :: ክሱ የቀረበው በ 4 / 2 / 91 በመሆኑ በይርጋ የሚታገደው ከ 4 / 2 / 81 በፊት ያለው ሂሣብ ብቻ ነው ::
1. የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት በመቁ .3993 በ 9 / 10 / 95 እና ከፍተኛ ፍ / ቤት በዝገብ
ቁ .23335 የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል :: 2. ፍ / ቤቱ ፍሬ ነገሩን መርምሮ የመሰለውን ውሣኔ እንዲሰጥ ጉዳዩ ወደ ፌዴራል
መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ይመለስ :: 3. ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
You must login to view the entire document.