ሀያ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፳፰ "
ነጋሪት ፡ ፡ ጋዜጣ ።
የጋዜጣው ፡ ዋጋ ባገር'ውስጥ ' ባመት
ያንዱ '
ጭ'አገር እጥፍ ' ይሆናል "
ማ ው ጫ "
፲፱፻፷፩ ዓ. ም.
በኢትዮጵያ ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ መንግሥት በጽሕፈት ▪ ሚኒስቴር ፡ ተጠባባቂነት ▪ የቆመ ።
የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቍጥር I ፻፸፫ / ፷፩ ዓ. ም. የቡና ተጨማሪ ታክስ (ሱር ታክስ) ቅናሽ ደንብ.
ቍጥር ፫፻፸፫ ፲፱፻፷፩ ዓ. ም. የሕግ ክፍል ማስታወቂያ
ገጽ ፪፻፴
ስለ ገቢና የወጭ ዕቃ የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ በ፲፱፻፴፭ ዓ.ም. በወጣው አዋጅ መሠረት የወጣ ደንብ ።
፩- የገንዘብ ሚኒስትር ስለገቢና ወጭ ዕቃ የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ በ፲፱፻፴፭ ዓ.ም. በቊጥር ፴፱ በወጣው አዋጅ በአንቀጽ ፭ (ሀ) በተሰ ሥልጣን መሠረት ይህን
ደንብ አውጥቷል ።
፫ ፪ ይህ ደንብ « የ፲፱፻፷፩ ዓ.ም. የቡና ተጨማሪ ታክስ (ሱር ታክስ) ቅናሽ » ደንብ ተብሎ ሊጠቀስ ይቻላል " ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ አገር በሚወጣው ቡና ላይ በ፲፱ ፻፶፮ ዓ.ም. በወጣው የሱር ታክስ ደንብ መሠረት ከሚ ከፈለው ተጨማሪ ታክስ (ሱር ታክስ) በመቶ ሃምሳ (50%) እየተቀነሰ ይከፈላል " ይህም ቅናሽ ተጨማሪ ታክሱ (ሱር ታክስ) በሚከፈልበት ጊዜ ይደረጋል ።
፬- ይህ ደንብ የሚጸናው በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መ ስከረም ፳ (ሃያ) ቀን ፲፱፻፷፪ ዓ.ም እኩለ ሌሊት ድረስ ብቻ ነው ።
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ ፯ ቀን ፲፱፻፷፩ ዓ. ም.
ማሞ ታደሰ የገንዘብ ሚኒስትር
አዲስ አበባ ነሐሴ ፯ ቀን ፲፱፻፷፩ ዓ. ም.
ቢያንስ ▪ በወር ▪ አንድ ' ጊዜ ▪ ይታተማል
የፖስታ ሣጥን: ❖r ር • ፩ሺ፫፻ 2 ፬ (1364)
ብርሃንና ሰላም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ማተሚያ ቤት ታተመ