ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ 3 ነጥብሊክ ሕገ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አሥረኛ ዓመት ቁጥር አዲስ አበባህዳር ፫ ቀን ፲፱፻፲፮ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፮ / ፲፱፻፲፮ ዓም የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የወጣ አዋጅ .. ገጽ ፪ሺ፬፻፴፱ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፮ / ፲፱፻፲፮ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የወጣ አዋጅ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር ፳፯ ፲፱፻ጽ፱ አንዳንድ | WHEREAS , it has been necessary to amend some provisions ድንጋጌዎችን ማሻሻል ፣ እና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት | of the commercial Registration and Business licensing አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ተጨማሪ ድንጋጌዎችን ማካተት በማስ | Proclamation No. 67/1997 and to include some additional በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ እንደገና ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ቁጥር ፫፻፸፮ ፲፱፻፲፮ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ማሻሻያ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር ፳፯ ፲፱፻፵፬ / እንደተሻሻለ ከዚህ እንደሚከተለው ተሻሽሏል ። ፩ በአዋጁ አንቀጽ ፭ ላይ የሚከተሉት ንዑስ አንቀጽ ( ፰ ) ፣ ( ፱ ) ፣ ( ፲ ) እና ) ፲፩ ) ተጨምረዋል ። ፰ ) የንግድ ማህበራት መስራቾች ወይም አባላት በተፈ ረሙና በንግድ መዝገብ በገቡ መመስረቻ ጽሑፎቻ ቸውና መተዳደሪያደንቦቻቸውላይ ከሚያደርጓቸው ማናቸውም ማሻሻያዎቻቸው በስተቀር ለንግድ ምዝገባ ከመቅረባቸው በፊት የመመስረቻ ጽሑፎቻ F ውናና የመተዳደሪያ ደንቦቻቸውን አግባብ ያለው ባለሥልጣን ለውልና የሰነዶች ምዝገባ ጽ / ቤት በሚልካቸው ደረጃቸውን የጠበቁ የመመስረቻ ጽሑፍና የመተዳደሪያ ደንብ ናሙናዎች መሠረት መፈራረም አለባቸው ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፪ሺ o የሣ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ኅዳር ፫ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም። የንግድ ማህበር መስራቾች ወይም አባላት የመመስረቻ | 9 ) Before signing their memorandum and Articles of ጽሑፎቻቸውን ወይም መተዳደሪያ ደንቦቻቸውን ከመፈራረ ማቸው በፊት የንግድ ማህበሩን ስም በተመለከተ በቅድሚያ ኣግባብ ያለው ባለሥልጣን ስሙ በሌላ ነጋዴ ያልተያዘ መሆኑን ሊያረጋግጥላቸው ይገባል ። 1. በትራንስፖርት ንግድ ሥራ ተሰማርቶ የነበረ ግለሰብ ነጋዴ ወራሾች በንግድ ስራው ለመቀጠል የንግድ ማህበር ለማቋቋም ያልፈለጉ ከሆነ ካወራሾቹ አንዱ በሌሎቹ በሚሰጠው ውክልና መሠረት በንግድ መዝገብ መመዝገብ ይችላል ። ፲፩ . በንግድ ማህበር ውስጥ በዓይነት የሚደረግ መዋጮን ግምት የንግድማህበሩ መስራቾች ወይም አባላት ባደረጉት ስምምነት የተወሰነ መሆኑ በመመስረቻ ጽሑፉውስጥ መጠቀስ አለበት ። ፪ ) የአዋጁ አንቀጽ ፰ ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፰ ተተክቷል ። የንግድ ማህበራት የሕግ ሰውነት የንግድ ማህበራት በንግድ ሕግ ቁጥር ፳፯ ፡ ፪፻፲፱ ፣ ፪፻፳ ፣ ፪፻፳፫ እና ፪፻፳፬ እንደተደነገገው ስለ መመስረታቸው ወይም በመመስረቻ ጽሑፎቻቸው ላይ ስለሚደረጉ ማሻሻያዎች የጋዜጣ ማስታወቂያ ሳያስፈልጋቸው በንግድ መዝገብ በመመዝገብ የሕግ ሰውነት ያገኛሉ ። ፪ ) የንግድ ማህበራትን የንግድ ምዝገባ ሦስተኛ ወገኖች እንዲያውቁት መዝገቡ ክፍት ይደረጋል ። የአዋጁ አንቀጽ ፬ ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፬ ተተክቷል ። ፱ ) ምዝገባው ስለሚፀናበት ጊዜ ማንኛውም የንግድ ምዝገባ የሚፀናው አመልካቹ በንግድ መዝገብ ከተመዘገበበት ዕለት ጀምሮ ነው ። የአዋጁ አንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ ( ፭ ) ተሰርዟል ። የአዋጁ አንቀጽ ፳፪ ፣ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እና ( ፫ ) ተሰርዘው በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እና ( ፫ ) ተተክ ተዋል ። ፪ ) ፈቃድ ለተጠየቀበት የንግድ ሥራ አግባብ ያለው የመንግሥት መሥሪያ ቤት በመመሪያ የሚወሰነውን መስፈርት ስለማሟላቱ በአመልካቹ የተፈረመ ማረጋገጫ መቅረብ አለበት ። አግባብ ያለው ባለሥል ጣንም ስለመመሪያው አፈፃፀም ለሚመለከተው መሥሪያ ቤት ያሳውቃል ። ፫ ) ከላይ በንዑስ ቁጥር ( ፪ ) የተጠቀሰው ቢኖርም የሙያ ብቃት ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊቀርብ ባቸው የሚገቡ የንግድ ሥራዎችንና ይህንኑ ማረጋገጫ የሚሰጡ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብ ይወስናል ። 6 ) የአዋጁ አንቀጽ ፳፫ላይ የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) ተጨምሯል ። ፫ ) በትራንስፖርት ንግድ ሥራ ተሰማርቶ የነበረ ግለሰብ ነጋዴ ወራሾች በንግድ ስራው ለመቀጠል የንግድ ማህበር ለማቋቋም ያልፈለጉ ከሆነ ከወራሾቹ አንዱ በሌሎቹ ወራሾች በሚሰጠው ውክልና መሠረት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት በንግድ መዝገብ ከተመዘገበ በኋላ በወኪሉ ስም የንግድ ፈቃዱ ይሰጣል ። ፯ ) የአዋጁ አንቀጽ ፳፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) ተሰርዞ በሚከ ተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) ተተክቷል ። ገጸ ፪ሺ፱የ፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ኅዳር ፫ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም ፫ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) በተመለከተው ጊዜ ውስጥ የንግድ ሥራ ፈቃዱን ሳያሳድስ የቀረ ሳለፈቃድ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ ማለትም ከጥር ፩ ቀን እስከ ሰኔ ፴ ቀን ከፈቃድ ማሳደሻው በተጨማሪ ለዘገየበት ለጥር ወር ብር 2,500.00 ( ሁለት ሺህ አምስት መቶ ) እና ለሚቀ ጥለው እያንዳንዱ ወር ብር 1,500.00 ( አንድ ሺህ አምስት መቶ ) ቅጣት በመክፈል የንግድ ፈቃዱን ያሳድሳል ። ፰ ) የአዋጁ ኣንቀጽ ፳፰ ንዑስ አንቀጽ ( ፬ ) እና ( ፮ ) ተሰርዘው በሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፮ ) ተተክ ተዋል ። ፬ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሠ ) ምክንያት ካልሆነ በስተቀር በሌሎች ማናቸውም ምክንያቶች የንግድ ሥራ ፈቃድ የተሰረዘባቸው ነጋዴዎች ያንኑ የንግድ ሥራ ፈቃድ እንደ አዲስ ለማውጣት የሚችሉት ከአንድ ዓመት በኋላ ነው ። ፮ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፭ ) መሠረት አግባብ ላለው ባለሥልጣን የንግድ ፈቃዱን ተመላሽ የሚያ ደርግ ነጋዴ ወይም በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት የተሰረዘበትን ያንኑ የንግድ ሥራ ፈቃድ እንደ አዲስ ለማውጣት ሲመጣ ወይም በዚህ አዋጅ ኣንቀጽ ፳፬ መሠረት ምትክ የንግድ ሥራ ፈቃድ እንዲሰጠው የሚጠይቅ ነጋዴ ተመላሽ በተደረገው ወይም በተሰረዘው ወይም በሚተካው የንግድ ሥራ ፈቃድ ለተጠቀመበት ጊዜ የግብር ክሊራንስ ማቅረብ አለበት ። ፬ ) የአዋጁ አንቀጽ ፳፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) ተተክቷል ። ፫ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ጥያቄው የቀረበለት አግባብ ያለው ባለሥልጣን ኣመልካቹን ለጠፋው የንግድ ፈቃድ የኃላፊነት ግዴታ በማስፈ ረምና በደንቡ የተመለከተውን ክፍያ በማስከፈል ምትክ የንግድ ሥራ ፈቃድ ይሰጠዋል ። ፲ የአዋጁ አንቀጽ ፴፭ ላይ የሚከተለው አዲስ ንዑስ ኣንቀጽ ( ፫ ) ተጨምሯል ። ፫ ) የሚመለከተው የሴክተር መሥሪያ ቤት ነጋዴው ፈቃድ ከተሰጠበት መስፈርት ውጭ ሲሰራ ሲገኝ ወይም ጥፋት ሲፈጽም መወሰድ ስለሚገባው እርምጃ አግባብ ላለው ባለሥልጣን ማሳወቅ አለበት ። ፫ ኣዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከህዳር ፫ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ኅዳር ፫ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት