የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አንደኛ ዓመት ቁጥር ፲፩ አዲስ ኣበባ – – ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፷፯ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፲፩ / ፲፱፻፷፯ ዓም : የቱሪዝም ኮሚሽን ማቋቋሚያ ገጽ ፻፰ አዋጅቁጥር ፲፩ / ፲፱፻፯ የቱሪዝም ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የቱሪዝም ኮሚሽንን ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤ | በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፲፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ኣዋጅ “ የቱሪዝም ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፲፩ | ፲፱፻፷፯ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ መቋቋም ፩• የቱሪዝም ኮሚሽን ( ከዚህ በኋላ “ ኮሚሽኑ ” እየተባለ | 2 . Establishment የሚጠራ ) ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ይሆናል ። ፫ : ዋና መሥሪያ ቤት የኮሚሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ይሆናል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ | ገጽ ሮ፱ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፫፯ ዓም : Negarit Gazeta – No . 11 – 24 August 1995 – Page 79 ፬ . የኮሚሽኑ ዓላማ የኮሚሽኑ ዓላማ ቱሪዝም እንዲስፋፋና እንዲዳብር ማድረግ ይሆናል ። ፭ የኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባር ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ . ፩ የሀገሪቱን የቱሪዝም ፖሊሲና ሕጐች ያዘጋጃል ፤ ሲፈቀድም በሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል ፤ የሀገሪቱ የቱሪስት መስህቦች በጐብኚዎች እንዲታወቁ ያደርጋል ፤ የቱሪስት አገልግሎት እንዲስፋፋ ያበረታታል ፣ ከኣንድ በላይ በሆኑ ክልሎች ውስጥ አገልግሎት ለሚሰጡ ወይም በውጭ ባለሀብቶች ለሚካሄዱ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋሞች ሥልጣኑ በግልጽ ለሌላ አካል በሕግ ካልተሰጠ በስተቀር ፈቃድ ይሰጣል ፣ ይቆጣጠራል ፤ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋሞችን ደረጃ ይመድባል ፤ ፭ ስለሀገሪቱ ቱሪዝም መረጃዎችን ይሰበስባል ፣ ያጠና ቅራል ፣ ያሰራጫል ፤ ቱሪዝም ነክ በሆኑ ጉዳዮች ለክልል መስተዳድሮች ምክርና ድጋፍ ይሰጣል ፤ ፯ የሀገሪቱን የቱሪዝም ዕድገት ለማፋጠን የሚረዱ ጥናቶችን ያካሂዳል ፣ እንደአስፈላጊነቱ ማሠልጠኛ ተቋሞችን ያቋቁማል ፤ የንብረት ባለቤት ይሆናል ፣ ውል ይዋዋላል ፣ በስሙ ይከሳል ፣ ይከሰሳል ፤ ፀ• ዓላማውን ለማስፈጸም የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን ያከና ፮ . የኮሚሽኑ አቋም ኮሚሽኑ ፤ ፩ : በመንግሥት የሚሾሙ አንድ ኮሚሽነርና አንድ ምክትል ኮሚሽነር ፤ እና ፪ አስፈላጊው ሠራተኞች ፤ ይኖሩታል ። ፯ ስለ ኮሚሽነሩ ሥልጣንና ተግባር ኮሚሽነሩ የኮሚሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን የኮሚ ሽኑን ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል ። ፪ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ኣጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽነሩ ፣ ሀ ) በዚህ አዋጅ ኣንቀጽ ፭ የተመለከተውን የኮሚሽኑን ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) በፌዴራሉ የሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት የኮሚ ሽኑን ሠራተኞች ይቀጥራል ፤ ያስተዳድራል ፤ ሐ ) የኮሚሽኑን የሥራ ፕሮግራምና በጀት ያዘጋጃል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ መ ) ለኮሚሽኑ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ ሠ ) ኮሚሽኑ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ሁሉ ኮሚሽኑን ይወክላል ፤ ረ ) ስለኮሚሽኑ የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ያቀርባል ። ኮሚሽነሩ ለኮሚሽኑ የሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለኮሚሽኑ ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ፰ በጀት የኮሚሽኑ በጀት በመንግሥት ይመደባል ። ገጽ ፯ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻T፯ ዓ•ም• Negarit Gazeta – No . 11 – 24 August 1995 - Page 80 ፱• የሂሣብ መዛግብት ፩ ኮሚሽኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። • የኮሚሽኑ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው | ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲ . የተሻረ ሕግ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፩፻T፪ ፲፱፻፸፪ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ፲፩ . መብትና ግዴታ ስለማስተላለፍ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኮሚሽን መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለኮሚሽኑ ተላልፈዋል ። ፲፪ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻ዥ፯ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ . ም ዶ ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ ።