የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፵፰ አዲስ አበባ ሰኔ ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፵፩ ዓ.ም. የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፩ሺ ፻፬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፲፩ የትምህርትመሣሪያዎችማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ ኣካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፴፬ ኣንቀጽ ፵፯ ፩ ( ሀ ) መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፯ / ፲፱፻፲፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። በዚህ ደንብ ውስጥ፡ “ የትምህርት መሣሪያዎች ” ማለት ለትምህርት መስጫ አገል ግሎት የሚውሉ መጻሕፍት : ሥዕላዊ መግለጫዎች ፣ ቻርቶች፡ ካርታዎች : የሳይንስ ፡ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት መሣሪያዎች : የትምህርት ተቋማት ቁሳቁሶች ፈርኒቸር ፤ የኦዶቪዥዋል መሣሪያዎች የሕፃናት መጫወቻዎች ፣ ልዩ ልዩ ፎርሞችና ሌሎችም ለትምህርቱ ዘርፍ የሚያስፈልጉ መሣሪያዎች ናቸው ። ያንዱ ዋጋ 2:30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፩ሺ፰፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፰ ሰኔ ፲፭ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ፩ የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ( ከዚህ በኋላ “ ድርጅቱ ” እየተባለ የሚጠራ ) የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ ድርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፳፬ መሠረት ይተዳደራል ። ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በመንግሥት የሚሰየም አካል የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥ ልጣን ይሆናል ። ፭ ዋና መሥሪያ ቤት የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ይሆናል ። እንደአስፈላጊነቱም በማንኛውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ፩ የትምህርት መሣሪያዎችን ማምረት : ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ገዝቶ ማቅረብ ፡ ፪ የሥልጠናና የሙያ ምክር አገልግሎት መስጠት ፤ ፫ ትርፋማነትን ማሳደግና አስተማማኝገበያ መፍጠር ፤ ፬ ዓላማዎችን ከግቡ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን ማካሄድ ። ፯ . ካፒታል ለድርጅቱ የተፈቀደው ካፒታል ብር ፩፻፵ ሚሊዮን ( አንድ | 7 . Capital መቶ ሃምሣ ሚሊዮን ብር ) ሲሆን ከዚህም ውስጥ ብር ፩፻፲ ሚሊዮን ፮፻፷፰ ሺ፯፻፪ ብርከ፪፬ ሣንቲም ( አንድ መቶ አሥር ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ስምንት ሺ ሰባት መቶ ሁለት ብር ከሰባ አራት ሣንቲም ) በጥሬ ገንዘብና በዓይነት ተከፍሏል ። ፰ ኃላፊነት ድርጅቱ ካለው ጠቅላላ ንብረት በዕዳ ተጠያቂ አይሆንም ። ፬ : ድርጅቱ የሚቆይበት ጊዜ ድርጅቱ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል ። ፲ መብትና ግዴታ ከአሁን ቀደም የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ይባል የነበረው ድርጅት መብትና ግዴታ በዚህ ደንብ ለድርጅቱ ተላልፋል ። ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ