አምሳ ሦስተኛ ዓመት ቍጥር ፲፬
ነ ጋ ሪ ት
የአንዱ ዋጋ
ማ ው ጫ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፴፫ ፲፱፻፹፮ ሰሜን ኦሞ የእርሻ ልማት ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስት ሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፴፩
በ ኢ ት ዮ ጵ ያ የ ሽ ግ ግ ር መ ን ግ ሥ ት የተወካዮች ምክር ቤት ተጠባባቂነት የወጣ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፴፫ ፲፱፻፹፮ ሰሜን ኦሞ የእርሻ ልማት ድርጅትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክርቤት ደንብ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጠቅላይ ሚኒስትርንና የሚኒስ ትሮች ምክር ቤትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፪ ፲፱፻፹፫ አንቀጽ ፬፪ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፹፬ በአንቀጽ ፵፯ ፩ ሀ መሠ ረት ይህን ደንብ አውጥቷል ።
፩. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ « ሰሜን ኦሞ የእርሻ ልማት ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፴፫ ፲፱፻፹፮ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ።
መ ቋ ቋ ም
፩. ሰሜን ኦሞ የእርሻ ልማት ድርጅት (ከዚህ በኋላ « ድርጅት » እየተባለ የሚጠራ) የመንግሥት የል ማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ።
፪. ድርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፹፬ መሠረት ይተዳደራል ።
ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን
በመንግሥት የሚሰየም አካል የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለ ሥልጣን ይሆናል ።
አዲስ አበባ ኅዳር ፲ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ. ም
መ ን ግ ሥ ት
ጋ ዜ ጣ
የፖስታ ሣጥን ቍ፹ሺ፩ (80,001)