የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፵፯ አዲስ አበባ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፲ ዓም የጤና አጠባበቅ ትምህርት ማዕከል ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፰፻፪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ ፲፱፻፲ የጤና አጠባበቅ ትምህርት ማዕከልን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፴፯ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የጤና አጠባበቅ ትምህርት ማዕከል ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፲ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ ፤ ፩ . “ የጤና አጠባበቅ ትምህርት ” ማለት የሰዎችን ባሕሪይና አኗኗር ለጤናማነት አመቺ ወደሆነ መልኩ በትምህርት መቀየር ፤ ባሕሪይውም ቀጣይነት እንዲኖረውማድረግ ፤ ሰዎች እራሳቸውንና የአካባቢያቸውን ነዋሪዎች ጤንነት ለመጠበቅ ኃላፊነት እንዲሰማቸው በማድረግ ጠቃሚና ትርጉም ባለው ሥራ የመሳተፍ ብቃታቸውን ማጎልበት ነው ፤ ፪ “ ሚኒስቴር ” ወይም “ ሚኒስትር ” ማለት እንደቅደም ተከተሉ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፰፻፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፲ ዓም • ፫ መቋቋም ፩ : የጤና አጠባበቅ ትምህርት ማዕከል ( ከዚህ በኋላ “ ማዕከሉ ” እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ የማዕከሉ ተጠሪነት ለሚኒስቴሩ ይሆናል ። ፬ . ዋና መሥሪያ ቤት የማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ይሆናል ። እንደ ኣስፈላጊነቱም በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ሊኖረው ይችላል ። ፭ ዓላማ ማዕከሉ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል በአገር አቀፍ ደረጃ የጤና አጠባበቅ ትምህርት እንቅስ ቃሴንማስተባበር ፤ ፪ በአገሪቱ የጤና ፖሊሲ መሠረት የኅብረተሰቡን የጤና ግንዛቤና አመለካከት በማሳደግ ኅብረተሰቡ በፈቃደ ኝነት ላይ የተመሠረተ የባህሪይ ለውጥ አምጥቶ ራሱን ከበሽታ ጠንቆች እንዲከላከል ፤ ጤናውን እንዲያዳብር በተዘረጉለት የጤና አገልግሎቶችና ፕሮግራሞች እንዲ ሳተፍና ተጠቃሚ እንዲሆን ማገዝ ። ፮ ሥልጣንና ተግባር ማዕከሉ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ ፩ በአገሪቱ የጤና ፖሊሲ ላይ በመመሥረት የጤና አጠባበቅ ትምህርት ሀገር አቀፍ መመዘኛ የማዘጋጀትና ተግባራዊነቱን የመከታተል ፪ በአገሪቱ ዋና ዋና የጤናና ተዛማጅችግሮች ላይ ያተኮሩ ትምህርታዊ መልእክቶችን አግባብ ባላቸው የመገናኛ ብዙሃን እንዲሰራጩ የማድረግ ፤ የጤና አጠባበቅ ትምህርትን በተመለከተ ለፌዴራልና ለክልል መንግሥታዊ እንዲሁም መንግሥታዊ ላልሆኑ አካላት እገዛ የመስጠት ፤ • አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ለትምህርት ቤቶችና ለማሠልጠኛ ተቋማት መሠረታዊ የጤና አጠባበቅ ትምህርት እንዲሰጥና እንዳስፈላጊነቱም በሥርዓተ ትምህርት እንዲካተት የማድረግ ፤ የጤና አጠባበቅ ትምህርትን በተመለከተ ጥናትና ምርምር የማካሄድ ፤ በጥናትና ምርምር ውጤቶች ላይ በመመስረት የማስተማሪያ መሣሪያዎችን የማዘጋጀትና የማሠራጨት ፤ ቀጣይ ጥናቶችና ግምገማዎች በማድረግ የማሻሻል ፤ • እንደአስፈላጊነቱ የሙያ ምክር የመስጠት ፣ አጫጭር ሥልጠናዎች አውደጥናቶችና ሲምፖዚየሞች የማካሄድ ፤ ፯ ለሚሰጠው አገልግሎት መንግሥት በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ተመጣጣኝ ዋጋ የማስከፈል ፤ ፰ የንብረት ባለቤት የመሆን ፤ ውል የመዋዋል ፤ በስሙ የመክሰስና የመከሰስ ፤ ፱ ለሚሰጠው የጤና አጠባበቅ ትምህርት አጫጭር ሥል ጠናዎች የምስክር ወረቀት የመስጠት ፤ ዓላማውን ለማስፈጸም የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን የማከናወን ። " ነው ቦርዱ ገጽ ፰፻፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፲ ዓ.ም ፮ : የማዕከሉ አቋም ማዕከሉ ፤ ፩ : ቦርድ ፣ ጅ በሚኒስትሩ አቅራቢነት በመንግሥት የሚሾሙ አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና አሳድ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፤ እና ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ፣ ይኖሩታል ። የቦርዱ አባላት ቦርዱ በመንግሥት የሚሰየሙ ሰባት አባላት ይኖሩታል ። ፩ . ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ • የማዕከሉን ሥራዎች በበላይነት ይመራል ፤ ይቆጣጠራል ፤ ጅ የማዕከሉን የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅድ እንዲሁም ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት መርምሮ ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፤ ሲፀድቅም ተግባራዊነቱን ያረጋግጣል ፤ ፫ • የማዕከሉን የሥራፕሮግራም መርምሮ ያፀድቃል ፤ በሥራ መተርጎሙንም ይከታተላል ፤ በዋናው ሥራ አስኪያጅ በሚቀርቡ የማዕከሉን አስተዳ ደርና አመራር በሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ይወስናል ። የቦርዱ ስብሰባ ፩ ቦርዱ በዓመት ሦስት ጊዜ ይሰበሰባል ፤ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሰብሳቢውጥሪ በማናቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል ። ፪ . በቦርዱ ስብሰባ ላይ ከግማሽ በላይ አባላት ከተገኙ ምልአተ ጉባኤ ይሆናል ። ፫ የቦርዱ ውሣኔ የሚተላለፈው በስብሰባው በተገኙ አባላት በአብዛኛው ድምጽ ሲደገፍ ይሆናል ፤ ሆኖም ድምጽ እኩል ለእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሣኝድምጽ ይኖረዋል ። የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። የዋናው ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር ፩ . ዋናው ሥራ አስኪያጅ የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የማዕከሉን ሥራዎች ይመራል ፤ ያስተዳድራል ። ፪ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ፤ ሀ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፮ የተመለከተውን የማዕከሉን ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ የማዕከሉን ዓመታዊ ዕቅድ ፤ የሥራ ፕሮግራም እና በጀት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፤ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ ሐ ለማዕከሉ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ መ ) የማዕከሉን የሥራ እንቅስቃሴና የሂሣብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፤ ሠ ) በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት የማዕከሉን ሠራተኞች ይቀጥራል ያስተዳድራል ፤ ረ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ማዕከሉን ይወክላል ። ገጽ ፰፻፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፲ ዓም • ዋናው ሥራ አስኪያጅ ለማዕከሉ ሥራቅልጥፍና በሚያ ስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለምክትል ዋና አስኪያጁ ወይም ለሌሎች የማዕከሉ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ፲፪ የምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ ሥልጣንና ተግባር ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ ፤ ዋናው ሥራ አስኪያጅ በማይኖርበት ጊዜ ለዋናው ሥራ አስኪያጅ የተሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል በዋናው ሥራ አስኪያጅ የሚሰጡትን ሥራዎች ያከና ፲፫ በጀት ፩ • የማዕከሉ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል ፤ ሀ ) በፌዴራል መንግሥት ከሚመደብለት በጀት ለ ) ከሚሰበስበው የአገልግሎት ክፍያ ፣ እና ሐ ) ከሌሎች ምንጮች፡ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው ገንዘብ በማዕከሉ ስም በሚከፈት የባንክ ሂሣብ ተቀማጭ ሆኖ የማዕከሉን ሥራዎች ለማስፈጸም ወጪ ይሆናል ። የሂሣብ መዛግብት ፩ . ማዕከሉ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ፡፡ ፪ . የማዕከሉ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይመው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ፡፡ አዲስ አበባ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፲ ዓም : መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት