የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፲፬ አዲስ አበባ የካቲት ፲፫ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፰ ፲፱፻፲ ዓም የሻይ ምርትና ገበያ ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፮፻፷፭ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፰ ፲፱፻፲ የሻይ ምርትና ገበያ ድርጅትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ዥ፯ አንቀጽ ፭ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፰፬ አንቀጽ ፵፯ ፩ ሀ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የሻይ ምርትና ገበያ ድርጅትማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፫ / ፲፱፻፲ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ መቋቋም ፩ . የሻይ ምርትና ገበያ ድርጅት ( ከዚህ በኋላ “ ድርጅቱ ” እየተባለ የሚጠራ ) የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፱ሺ፩ ገጽ ፮የዝጌ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ ) የካቲት 11 ቀን ፲፱፻፲ ዓም : - ደርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲ሀየሆ፬ መሠረት ይተዳደራል ። ፤ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በመንግሥት የሚሰየም አካል የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የድርጅቱ፡ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ይሆናል ። እንደአስፈላጊ ነቱም በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ድርጅቱ የተቋቋመባቸው ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው : ፩ ሻይ ቅጠልን በፋብሪካ ማዘጋጀት ፡ ፪- በፋብሪካ የተዘጋጀ ሻይ ቅጠልን ለገበያ ማቅረብ ፡ • ዓላማዎቹን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ የሆኑ ሥራዎችን ማካሄድ ። ፮ ካፒታል ለድርጅቱ የተፈቀደው ካፒታል ብር ፳፪ ሚሊዮን ፱፻፳፰ሺ ( ሃያ ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ ስምንት ሺህ ብር ) ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብር ፲፩ ሚሊዮን ፱፻፲፪ሺ ፮፻፭ ( አሥራ አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ስድስት ብር ) በጥሬ ገንዘብና በዓይነት ተከፍሏል ። ድርጅቱ፡ ካለው ጠቅላላ ንብረት በላይ በዕዳ ተጠያቂ አይሆንም ። : ድርጅቱ፡ የሚቆይበት ጊዜ ድርጅቱ፡ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል ። ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ፡ የካቲት ፲ ቀን ፲ሀየን ዓ • ም • መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ