×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፳፬/፲፱፻፹፰

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፲፪ አዲስ አበባ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፲፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፳፰ ዓም የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ማቋቋሚያ አዋጅ . . . . . ገጽ ፻፳፭ አዋጅቁጥር ፳፬ / ፲፱፻፳፰ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤማቋቋሚያ አዋጅ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ነጻ የዳኝነት አካል የተቋቋመ በመሆኑ ፤ ይህንኑ በሕገመንግሥት የተረጋገጠውን የዳኝነት ነጻነት | under the Constitution of the Federal Democratic Republic of ለማረጋገጥ ከሚያስችሉት መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው | Ethiopia : የዳኞች አስተዳደርን ማናቸውም የመንግሥት አካል ወይም ባለሥልጣን ተጽዕኖ ነጻ በሆነ ሁኔታ እንዲመራማድረግ በመሆኑ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | tration directed in a way free from the influence of Govern መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ማቋቋሚያ አዋጅቁጥር ፳፬ / ፲፱፻፳፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ . “ የዲሲፕሊን ጥፋት ” ማለት በዲሲፕሊንና በሥነ ምግባር ደንብ የተመለከተው ጥፋት ሲሆን በወንጀል ተከሶ ጥፋተ ኝነቱ የተረጋገጠበትን ፣ በጉቦና በኣማላጅ የሚሠራን ፣ በዘር ፣ በሃይማኖት ፣ በፆታና በፖለቲካ አመለካከት አድልዎ የሚያደርግን ወይም ባለጉዳይ የሚያጉላላን ይጨምራል ፤ ያንዱ ዋጋ 1160 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ተሺ፩ ገጽ ፻፳፮ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓም : Negarit Gazeta – No . 12 15 February 1996 Page 126 ነ ተ . . . . . . . . . . . . . . . . ፪ . “ ጉልህ የሆነ የሥራችሎታናቅልጥፍናማነስ ” ማለት በዲሲፕ | 2 ) “ Manifest Incompetence and Inefficiency ” means ሊንና በሥነ ምግባር ደንብ የተመለከተው ሲሆን በዳኝነት ሥራው ላይ ሙያው ከሚጠይቀው የትምህርትና የልምድ ችሎታ በታች የሆነ የሕግና የፍሬ ነገር ስሕተት የሚፈጽምን ወይም ከሚገባው ጊዜ በላይ ክርክር የሚያራዝምን ይጨምራል ። ፫ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ መቋቋም የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ( ከዚህ በኋላ “ ጉባዔው ” | እየተባሉ የሚበልራ ) በዚህ ፡ ኣ°ጅ ተቋቁሟል ። ፩ የጉባዔው አባላት ፩ ጉባዔው የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ፤ ሀ ) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት . ሰብሳቢ ለ ) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት . . . . . . . አባል ሐ ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሦስት አባላት . . . . . . . . . . . . . . . . . መ ) ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በሥራ ቀደምትነት ያለው አንድ ዳኛ . . ዘሠ ) የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት . . . ረ ) ከፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በሥራ ቀደምትነት ያለው አንድ ዳኛ . . . ሲ ) የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት # ጉባዔው የራሱን ፀሐፊ ከኣባላቱ መካከል ይመርጣል ። ፫ ሰብሳቢው በማይኖርበት ጊዜ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሰብሳቢውን ተክቶ ይሰራል ። ፭ የጉባዔው ሥልጣንና ተግባር ጉባዔው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ . በጉባዔው አባላት ከተጠቆሙ ዕጩዎች መካከል በዚህ | ኣዋጅ ኣንቀጽ ፰ መሠረት ለዳኝነት ብቁ የሆኑትን ዕጩ ዳኞች ይመርጣል ፤ ፪ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ ተ፩ ( ፪ ) መሠረት የክልል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በሚያቀርብላት የክልል ጠቅላይና ከፍተኛ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞች ላይ አስተያየቱን ይሰጣል ፣ ፫ የፌዴራል ዳኞች የሚመሩበትን የዲሲፕሊንና የሥነ ምግባር ደንብ ያወጣል ፤ ፬• ስለፌዴራል ዳኞች ዝውውር ፣ ደመወዝ ፣ አበል ፣ የደረጃ ዕድገት ፣ ህክምናና ምደባ ይወስናል ፤ ፭ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ መሠረት የሚቀርቡ ጉዳዮችን መርምሮ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ጅ፱ ( ፩ ) መሠረት ይወስናል ፤ ውሳኔው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እስከሚጸድቅ ድረስ ዳኛውን ከሥራ ለማገድ ይችላል ። ዝርዝሩ በዳኞች የዲሲፕሊንና የሥነ ምግባር ደንብ ይወሰናል ። ፮ . የጉባዔው ስብሰባ ፩ ጉባዔው በወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል ፣ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል ። ፪ ከጉባዔው አባላት ኣብዛኛዎቹ ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ የጉባዔው ውሣኔዎች በድምፅ ብልጫ ያልፋሉ ፣ ሆኖም ድምጽ እኩል በኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሣኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ፬• የዲሲፕሊን ክስ የቀረበበት ማንኛውም የጉባኤ ኣባል ዳኛ ጕዳዩ በሚታይበት ጊዜ በጉባዔው ስብሰባ ላይ በአባልነት መቀመጥ አይችልም ። | ገጽ ፻፳፯ ነጋሪት ጋዜጣ ፲፪ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓም - Negarit Gazeta No . 12 15 February 1996 Page 127 ፭ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ፣ ( ፪ ) ፡ ( ፫ ) እና ( ፱ ) | _ 5 ) Without prejudice to the other provisions of this ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፡ ጉባዔው የራሱን | የስብሰባ ሥነሥርዓት ደንብ ማውጣት ይችላል ። • የጉባዔው ሰብሳቢ ሥልጣንና ተግባር የጉባዔው ሰብሳቢ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ . የጉባዔውን ጽሕፈት ቤት በበላይነት ይመራል ፣ ይቆጣ ፪ . የጉባዔውን ስብሰባ ይጠራል ፡ ፫ የጉባዔውን ስብሰባ በሊቀ መንበርነት ይመራል ፤ ፩ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ( ፩ ) መሠረት በጉባዔው አባላት የተጠቆሙትን ግለሰቦች አጭር የሕይወት ታሪክ መግለጫ አዘጋጅቶ ለጉባዔው ያቀርባል ፣ በጉባዔው የተመረጡትን ዕጩ ዳኞች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀርባል ። ፰ ለዳኝነት ለመመረጥ የሚያበቁ ሁኔታዎች ፩ . የሚከተሉትን ሁኔታዎች የሚያሟላ ማንኛውም ኢትዮ ጵያዊ የፌዴራል ዳኛ ሆኖ ሊሾም ይችላል ፣ ህ ) ለሕገ መንግሥቱ ታማኝ የሆነ ፡ ለ ) በሕግ ትምህርት የሰለጠነ ወይም በልምድ በቂ የሆነ የሕግ ዕውቀት ያለው ፡ ሐ ) በታታሪነቱ ፡ በፍትሐዊነቱና በሥነ ምግባሩ መልካም ስም ያተረፈ ፡ መ ) በዳኝነት ሙያ ለመሰማራት ፈቃደኛ የሆነ ፡ እና ሠ ) ዕድሜው ከ፳፭ ዓመት ያላነሰ ። ማንኛውም ሰው በመንግሥት ሕግ አውጭ ወይም አስፈጻሚ ውስጥ ወይም በማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት በአባልነት በሚያገለግልበት ጊዜ አጣምሮ የዳኝነት ሥራ ሊሠራ አይችልም ። ፱• የዳኞች ከሥራ መሰናበት ማንኛውም የፌዴራል ዳኛ ከሥራ የሚሰናበተው በሚከተሉት ምክንያቶች ይሆናል ፤ ፩ ሥራውን ለመልቀቅ ሲፈልግ የሁለት ወር የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ፤ ፪• ዕድሜው ስድሣ ( ፰ ) ዓመት ሲሞላው ፤ ፫ በሕመም ምክንያት ተግባሩን በተገቢው ሁኔታ ማከናወን ኣይችልም ተብሎ ሲወሰን ፤ ፬ የዲሲፕሊን ጥፋት ፈጽሞ ሲገኝ ፤ ፭ ጉልህ የሆነ የሥራ ችሎታና ቅልጥፍና አንሶታል ተብሎ ሲወሰን ፤ ፮• የዳኞች የዲሲፕሊንና የሥነ ምግባር ደንብን ተላልፎ ፲ አቤቱታ ስለማቅረብ ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ የተመለከቱትን ተላልፎ በሚገኝ የፌዴራል ዳኛ ላይ ለጉባዔው አቤቱታ | ማቅረብ ይችላል ። ፲፩ ቃለ መሐላ ዳኞች ሥራቸውን ከመጀመራቸው በፊት የሚከተለውን ቃለ መሐላ ይፈጽማሉ ፤ እኔ . . . . . . . . . . . . . . . . በዛሬው ዕለት . . . . . . . . . . . . . ፍርድ ቤት ዳኛ በመሆን ተሹሜ ሥራዬን ስጀምር የተጣለብኝን ከፍተኛ ኃላፊነት በታማኝነት ለመፈጸም ቃል እገባለሁ ። ገጽ ፻፳፯ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ የካቲት ፯ ቀን ፲ሀየዝ፷ ዓ•ም• Negarit Gazeta No . 12 15 February 1996 Page 128 ፲፪ የተሻሩ ሕጎች አዋጅ ቁጥር ፳፫ ፲፱፻፳፬ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ፲፫ መብትና ግዴታ ስለማስተላለፍ በአዋጅ ቁጥር ፳፫ ፲፱፻፴፬ የተቋቋመው የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ መብትና ግዴታ በዚህ አዋጅ ለተቋቋመው ጉባዔ ተላልፋል ። አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ኣዋጅ ከየካቲት ፯ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓ . ም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓ•ም• ዶ ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?