ምክር ቤት ደንብ . … ............. ' s የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፯ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲስ አበባ ጥቅምት ፳ ቀን ፲ሀየ ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፩ ፲፱የ 3 ዓ • ም • ዕለት ደራሽ የእርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ገጽ ፮የሃ፩ ነጋሪት ጋዜጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፩ ፲፱፻ 1 ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ ፲ህየ፳፯ አንቀጽ ፭ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፳፬ አንቀጽ ፵፯ ፩ ሀ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርእስ ይህ ደንብ “ ዕለት ደራሽ የእርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፩ ሀየን ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ መቋቋም ፩ ዕለት ደራሽ የእርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት ( ከዚህ በኋላ “ ድርጅቱ ” እየተባለ የሚጠራ ) የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ ድርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፳፬ መሠረት ይተዳደራል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፮፻፶፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ ጥቅምት ፳ ቀን ፲፱፻፲ ዓ.ም ፫ . ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በመንግሥት የሚሰየም አካል የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ይሆናል ። የድርጅቱ ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው ፤ ፩ የዕርዳታ ቁሳቁስ ማጓጓዝ ኣገልግሎት በክፍያ መስጠት ፣ ፪ . የዕርዳታ ቁሳቁስ ማጓጓዝ ሥራ በማይኖርበት ጊዜ ማንኛውንም የልማትና የንግድ ጭነትን በክፍያ ማጓ ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተውን ዓላማ በማያደናቅፍ ሁኔታ ማንኛውንም የማጓጓዝ አገልግሎት በመስጠት ተግባር መሠማራት ፣ ዓላማዎቹን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎ ችን ማካሄድ ። ለድርጅቱ የተፈቀደው ካፒታል ብር ፵፮ ሚሊዮን ፶፩ሺ ፵ ( አርባ ስድስት ሚሊዮን ሃምሣ አንድ ሺ አርባ ብር ) ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብር ፵ ሚሊዮን ፱፻፳፭ሺ ፲፯ ( አርባ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ አምስት ሺ አሥራ ሰባት ብር ) በዓይነት ተከፍሏል ። ፮ : ዋና መሥሪያ ቤት የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ይሆናል ። እንደአስፈላ ጊነቱም በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ፯ ኃላፊነት ድርጅቱ ካለው ጠቅላላ ንብረት በላይ በዕዳ ተጠያቂ አይሆንም ። ፰ ድርጅቱ የሚቆይበት ጊዜ ድርጅቱ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል ። ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥቅምት ፳ ቀን ፲፱፻፮ ዓ.ም. መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰላም ማተሚያ ቤት ታተመ