የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ
ሃያ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፺፬ አዲስ አበባ ነሐሴ ፳፭ ቀን ፪ሺ፱ ዓ.ም
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፵፯ / ፪ሺ፱ ዓ.ም
የ፪ሺ፲ በጀት ዓመት የፌደራል መንግሥት በጀት አዋጅ. ገጽ ፱ሺ፱፻፴፰
አንቀጽ ፩ አጭር ርዕስ
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ
በ፪ሺ፲ በጀት ዓመት በፌደራል መንግሥት ለሚከናወኑ ሥራዎችና አገልግሎቶች የሚያስፈልገውን በጀት አዕድቆ በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ወቅት ሥራ ላይ ማዋል አስፈላጊ በመኑ ፣
የፌደሬሽን ምክር ቤት በወሰነው ቀመር መሠረት የፌደራሉ መንግሥት ለክልሎች የሚሰጠው የድጋፍ በጀት መጠን መወሰን ስለሚኖርበት ፣
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፵፯ / ፪ሺ፱
የፌደራል መንግሥት የበጀት አዋጅ
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ (፩) እና (፲፩) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ፦
ክፍል አንድ
ይህ አዋጅ " የ፪ሺ፲ በጀት ዓመት የፌደራል መንግሥት የበጀት
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፵፯ / ፪ሺ፱ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ።
_ አንቀጽ ፪ ጠቅላላ የተፈቀደ በጀት
ከሐምሌ ፩ ቀን ፪ሺ፱ ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ ፴ ቀን ፪ሺ፲ ዓ.ም በሚፈጸመው በአንድ በጀት ዓመት ጊዜ ውስጥ የፌደራል መንግሥት ከሚያገኘው ገቢ እና ከሌላ ገንዘብ i ይ ከዚህ ጋር በተያያዘው ሠንጠረዥ ውስጥ ለሚጠቀሱት ሥራዎችና __ አገልግሎቶች ቀጥሎ እንደተመለከተው ፦ ሀ / ለመደበኛ ወጪዎች
ለ / ለካፒታል ወጪዎች
ብር 81,839,528,570 ብር 114,703,641,453 ብር 117,260,432,137
h / ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ መ / ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ ድጋፍ
ጠቅላላ ድምር
ብር 320,803,602,160 / ሶስት መቶ ሃያ ቢሊዮን ስምንት መቶ ሶስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሁለት ሺ አንድ መቶ ስድሳ ብር / ለፌደራል መንግሥት ወጪ ሆኖ እንዲከፈል በዚህ አዋጅ ተፈቅዷ ።
ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሢ.ቀ. ፹ሺ፩