የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፵፮ አዲስ አበባ ሰኔ ፲፪ ቀን ፲፱የኝ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፯ ፲፱፻፲ ዓ.ም የዕቃ አስተላላፊነት እና የመርከብ ውክልና ሥራ ፈቃድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፯፻፳፮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፯ ፲፱የኝ የዕቃ አስተላላፊነት እና የመርከብ ውክልና ሥራ ፈቃድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ ፲ሀየዝ፯ አንቀጽ ፭ እና በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር ፳፯ ፲፱፻፳፬ አንቀጽ ፵፯ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የዕቃ አስተላላፊነት እና የመርከብ ውክልና ሥራ ፈቃድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፯ ፲፱፻ኝ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ ፡ ፩ . “ ዕቃ አስተላላፊነት ” ማለት በአገር ውስጥ ወይም | 2. Definitions በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕቃ ተቀባይን ወይም ዕቃ ላኪን በመወከል የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ፡ የወደብ ሥነ ሥርዐት እና ሌሎች ሥነ ሥርዓቶችን አስፈጽሞ የገቢ ወይም የወጪ ዕቃዎች በወደብ እንዲገቡ ወይም እንዲወጡ ማድረግ ሲሆን ዕቃን የማጓጓዝንና የማስረከብን ሥራ ይጨምራል ፡ ፪ . “ ዕቃ አስተላላፊ ” ማለት በዚህ ደንብ መሠረት የዕቃ አስተላላፊነት ለመሥራት የንግድ የተሰጠው ሰው ነው ፡ ያንዱ ዋጋ 3:40 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ዝሺዕ ገጽ ፯፻፳፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፮ ሰኔ ፲፪ ቀን ፲፱፻፲ ዓ • ም • ፫ “ ወደብ ” ማለት የፌዴራል ገቢዎች ቦርድ የሚወስነው ክልል ወይም ቦታ ነው : ፬ . “ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ማስፈጸም ” ማለት ዕቃ ላኪዎችን ወይም አስመጪዎችን በመወከል በጉምሩክ ጣቢያ ውስጥ ለወጪ ወይም ለገቢ ዕቃዎች የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ማስፈጸም ነው ፡ ፭ “ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ” ማለት ወደ ሀገርየሚገባ ፤ ወደ ውጭ ሀገር የሚላክ ወይም ተላላፊ ዕቃ ጉምሩክ ወደብ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እንደአግባብነቱ አስመጪው እስከሚረከበው ወይም ከኢትዮጵያ እስከሚወጣ ድረስ የሚከናወን ማናቸውም ሂደት ነው ፣ ፮ “ የወደብ ሥነ ሥርዓት ማስፈጸም ” ማለት የወጪ ዕቃን በተመለከተ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ በወደብ ዕቃው በመርከብ ላይ እስከሚጫንበት ወይም ገቢ ዕቃን በተመለከተ ዕቃው ከተራገፈ በኋላ ከወደብ እስከሚወጣበት ጊዜ ድረስ ለወጪ ወይም ለገቢ ዕቃ ማናቸውንም ሥነ ሥርዓት ማስፈጸም ነው : ፯ . “ ዕቃዎችን በአንድ ላይ ማቀናጀት ” ማለት በአንድ ላይ ሊሆኑ የሚችሉ የተለያዩ ባለንብረቶች ዕቃዎችን በአንድ ሙሉ ኮንቴይነር አንድ ላይ የማሰባሰብ ተግባር ነው ፣ ፰ . “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ፣ ፱ . “ የተቆጣጣሪ ውክልና ” ማለት ወደብ ውስጥ ያለ መርከብ ባለንብረትን በመወከል የባለመርከቡን ጥቅም ለመጠበቅ የመርከብ ወኪሉን ሥራ የመቆጣጠር ተግባር ፲ . “ መርከብ ” ማለት ማናቸውም ለማሪታይም ትራንስ ፖርት አገልግሎት የሚውል ተንሳፋፊ የጭነት ወይም የሰው ማጓጓዣ መሣሪያ ሲሆን ጀልባን ይጨምራል ፡ ፲፩ . “ የመርከብ ውክልና ” ማለት የመርከብ ባለንብረትን ፣ ተከራይን ፡ ወይም ኦፕሬተርን በመወከል ፡ መርከቡ የሚያጓጉዘውን ዕቃ ወይም መንገደኛ ማግኘትንና መመ ዝገብን ፡ በባህር ወደብ ላይእና በአገር ውስጥእንደአስፈላ ጊነቱ ለመርከቦች አገልግሎት መስጠትን ፡ የመጫንና የማራገፍን ፡ እንዲሁም ዕቃን አጓጉዞ የማከማ ቸትን ሥራ ማስተባበርን ይጨምራል ፣ ፲፪ . “ የመርከብ ወኪል ” ማለት በዚህ ደንብ መሠረት የመርከብ ውክልና ለመሥራት የንግድ ሥራ ፈቃድ የተሰጠው ሰው ነው ፡ ፲፫ “ የንግድ ሥራ ፈቃድ ” ማለት በዕቃ አስተላላፊነት ወይም በመርከብ ውክልና አገልግሎት ሥራ ለመሠ ማራት ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚሰጥ ፈቃድ ፲፬ . “ የውጭ ንግድ ረዳት ” ማለት በንግድ ሕግ ከአንቀጽ ፴፬ እስከ ፳፪ እንደተተረጎመው የንግድ ወኪል ፣ የንግድ ደላላ እና የኮሚሽን ወኪል ነው ። ፫ : የዕቃ አስተላላፊነት ሥራ የዕቃ አስተላላፊነት ሥራ የሚከተሉትን ይጨምራል ፣ ፩ የወደብ ሥነ ሥርዓት ማስፈጸም ፣ ፪ • የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ማስፈጸም ፤ ፫ • ዕቃዎችን በአንድ ላይ አቀናጅቶ የመላክ አገልግሎት መስጠት ፣ የመጋዘን አገልግሎት መስጠትና ዕቃ የማድረስ ፣ የዕቃ ማስተናገጃ መሣሪያዎች አገልግሎት መስጠት ፣ ገጽ ፯፻፳፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ ሰኔ ፲፪ ቀን ፲፱፻፲ ዓም የራሱ ትራንስፖርት ካለው እንደአጓጓዥ ሆኖ የትራንስ ፖርት አገልግሎት መስጠት ፡ ባለዕቃው ራሱ ማጓጓዣ ካላቀረበ በስተቀር ፡ የራሱ ትራንስፖርት የሌለው እንደሆነ የትራንስፖርት አገል ግሎት ተከራይቶ ዕቃውን ማጓጓዝ ፣ ፰ የዕቃዎች ማጠን አገልግሎት መስጠት ፡ ፬ ዕቃዎችን ማሸግ ፣ ፲ ሠነዶችን ማዘጋጀትና መስጠት ፡ ፲፩ የውጭ ንግድ ደንብና የሌተር ኦፍ ክሬዲት ትእዛዞችን ተግባር ላይ ማዋል ፡ ፲፪ አመቺ ማጓጓዣ መምረጥ : የዕቃ ማጓጓዝ ስምምነት መዋዋል ፡ ፲፫ የዕቃዎችን እንቅስቃሴ መከታተል ፡ ፲፬ . የዕቃ መተላለፍን በተመለከተ ምክር መስጠት ። የመርከብ ውክልና ሥራ የመርከብ ውክልና ሥራ የሚከተሉትን ይጨምራል ፤ ፩ ከተለያዩ የመርከብ ባለንብረቶች ጋር ግንኙነቶች በማድረግ ለመጫንና ለማራገፍ ስለሚመጡ መርከቦች አስፈላጊ መረጃዎችን በቅድሚያ ማጠናቀር ፡ ፪ • መርከቦች በየቀኑ ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ ማውጣትና ለላኪዎችና ላስመጪዎች መላክ ፡ ፫ • ለመርከብ ዕቃ የመፈለግ ፡ የመደልደልና የማስተባበር አገልግሎት መስጠት ፡ ፬ . የመርከቦችን አመጣጥና አካሔድ ሁኔታ የማቀናጀትና የአገሪቱ የወጭ ንግድ ዕቃዎች ብቃት ባላቸው አጓጓዦች መስተናገዱን ማረጋገጥ ፡ ፭ የወጭ ዕቃዎች መርከቡ ወደብ ከመድረሱ በፊት ወደብ ለመድረሳቸው መከታተል ፡ ዕቃዎች በመርከብ ላይ በአግባቡ መጫናቸውን ማረጋገጥ ፡ ፮ ዕቃ አስመጪዎች ዕቃቸውን እንዲወስዱ ማስታወቅ ፣ የወደብ መጨናነቅን እንዲሁም የአገልግሎት መዘግየትን ለማስወገድ ወይም ለመቀነስ አግባብ ያላቸውን ኣካላት መርዳት ፣ ፰ የመርከብ መከራየትን በተመለከተ ብቃት ያላቸውን መርከቦች ለመከራየት እንዲቻል ድጋፍ መስጠት ፡ ፬ . የመርከብ ዕቃ ማጓጓዣ ኪራይ መሰብሰብና የሒሳብ መግለጫ ሠነድ እንዲሁም የገቢና ወጪ መግለጫ ዝግጅት አገልግሎት መስጠት ፡ ፲ የዕቃ መጫንና ማራገፍ አገልግሎት እና የዕቃ ተቆጣጣ ሪነት ተግባር ማስተባበር ፡ ፲፩ ወደብ ውስጥ ለመርከቡ አስፈላጊ የሆኑ የተለያዩ አገልግ ሎቶችን ማለት ለመርከቡ ሠራተኞች ምግብ ውሃ የመሳሰ ሉትን መስጠት ወይም የሚሰጥበትን ሁኔታ ማቀናጀት ፲፪ • ባሕረኞችን የማቀያየርና ወደ መጡበት የመመለስ አገል ግሎት መስጠት ፡ ፲፫ • የመርከብ ዕቃ መጫኛ ሠነድ ፡ የዕቃ ማስረከቢያ ሠነድ ማዘጋጀትና መስጠት እንዲሁም ሌሎች የመርከብ ሠነዶችን ማዘጋጀት ፡ ፲፬ • ባለዕቃዎች የሚያቀርቡት የክፍያ ጥያቄ እንዲፈጸም ሁኔታዎችን ማመቻቸት ፡ ፲፭ የተቆጣጣሪ ውክልና አገልግሎት መስጠት ፡ ፲፮ የኮንቴይነር እንቅስቃሴ መከታተል ። ገጽ ፯፻፳፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፮ ሰኔ ፲፪ ቀን ፲፱፻፲ ዓም : ስለፈቃድ ኣስፈላጊነት ፩ . ማንኛውም ሰው የዕቃ አስተላላፊነት ወይም የመርከብ ውክልና አገልግሎት ሥራ ለመሥራት በዚህ ደንብ መሠረት ፈቃድ ማውጣት ይኖርበታል ። ፪ . ማንኛውም ሰው በውጭ ንግድረዳትነት ፈቃድየመርከብ ውክልናና የዕቃ አስተላላፊነት ሥራ ለመሥራት በዚህ ደንብ መሠረት ፈቃድ ማውጣት ይኖርበታል ። በዚህ ደንብ መሠረት የዕቃ አስተላላፊነት ሥራ ፈቃድ የተሰጠው ሰው የጉምሩክ አስተላላፊነት ሥራ ፈቃድ እንደተሰጠው ይቆጠራል ። ፮ ፈቃድ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ለዕቃ አስተላላፊነት ሥራ ወይም ለመርከብ ውክልና ሥራ ፈቃድ ለማግኘት አመልካቹ : ሀ ) ኢትዮጵያዊ ዜጋ ወይም አንደኛው ወገን ለሚሰጠው ጥቅም ሌላኛው ወገን በተመሳሳይ አጸፋውን የሚሰ ጥበት ስምምነት ኢትዮጵያ የተፈራረመችበት አገር ለ ) ለዕቃ አስተላላፊነት ከብር ፩ ሚሊዮን ፭፻ ሺህ : ለመርከብ ወኪልነት ከብር ፩ሚሊዮን ወይም ሁለቱንም ሥራዎች ለማካሄድ ከብር ፪ሚሊዮን ፪፻ ሺህ ያላነሰ መነሻ ካፒታል ያለው ፡ ሐ ) እራሱ ወይም የቀጠረው ሰው በኢንተርናሽናል ትራንስ ፖርት በተለይም በባሕር ትራንስፖርት ሥራ አስፈ ላጊው የሙያ ዕውቀትና ልምድ ያለው ፡ ለዚህም ከትራንስፖርትና ሚኒስቴር ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የሚያቀርብ ፡ መ ) በቴሌፎን ፡ በፋክስ ፡ በቴሌክስ እና በሌሎች ለሥራው አስፈላጊ በሆኑ ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎች የተደራጀ ቢሮ ያለው ፡ እና ሠ ) የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩን መመሥረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ የሚያቀርብ ፤ መሆን አለበት ። ፪ • ለዕቃ አስተላላፊነት ሥራ የሚያመለክት አመልካች በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሐ ) የተመለከተውንና ከጉምሩክ ባለሥልጣን በጉምሩክ አስተላላፊነት መሥራት የሚያስችለው የችሎታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት ። ፫ • የጉምሩክ አስተላላፊነት ሥራ ፈቃድ ያለው አመልካች የችሎታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አያስፈል ገውም ። ፯ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር ሥልጣን የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር ከዚህ በአንቀጽ ፮ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሐ ) ለተጠቀሱት መስፈ ርቶች መመሪያ ያወጣል ። ሚኒስቴሩ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሐ ) የተጠቀሱትን መስፈርቶች ላሟላ አመልካች የችሎታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል ። ፰ . የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሥልጣን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በአንቀጽ ፭ የተዘረዘሩት ተሟልተው ሲቀርቡለት የዕቃ አስተላላፊነት ወይም የመርከብ ውክልና የንግድ ሥራ ፈቃድ ይሰጣል ። ገጽ ፯፻፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፮ ሰኔ ፲፪ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ፬ የጉምሩክ ባለሥልጣን ሥልጣን የጉምሩክ ባለሥልጣን በዕቃ አስተላላፊነት ሥራ ለሚሠራ ሰውየጉምሩክ አስተላላፊነትን በተመለከተ በጉምሩክ አስተላ ላፊነት ሥራ ፈቃድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፵፭ / ፲፱፻፳፮ በአንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሐ ) መሠረት የችሎታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል ። ፲ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሥልጣን ፩ የመርከብ ዕቃ ማስጫኛ ሰነድ ፣ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ፲፫ እንደተመለከተው ፣ የመርከብ ወኪሉ የሚያዘጋጀውና የሚሰጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይሆናል ። ፪ • በዕቃ አስተላላፊነትና በመርከብ ውክልና ሥራ የሚገኘ ውንና የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ ቁጥጥር የኢትዮጵያ ባንክ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይፈጸማል ። የችሎታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀትን ስለማገድና ስለመ አንድ ዕቃ አስተላላፊ ወይም የመርከብ ወኪል ሥራው የሚጠይቀውን የሙያ ግዴታና ሥነ ምግባር ካላከበረ የችሎታ የምስክር ወረቀቱ ምስክር ወረቀቱን በሰጠው አካል ሊታገድበት ወይም ሊሠረዝበት ይችላል ። ምስክር ወረቀቱም መታገዱን ወይም መሠረዙን የንግድና ኢንዱ ስትሪ ሚኒስቴር እንዲያውቀው ይደረጋል ። የዕቃ አስተላላፊ ወይም የመርከብ ወኪል ተጠያቂነት ዕቃ አስተላላፊ ወይም የመርከብ ወኪል ተግባሩን በጥንቃቄ ማከናወን አለበት ። • ዕቃ አስተላላፊው ወይም የመርከብ ወኪሉ ተግባሩን ባለማከናወኑ ጥፋት በተለይም ዕቃው ቢጠፋበት ፣ ቢጎድልበት ወይም ዕቃውን በወቅቱ ባያስ ረክብ ተጠያቂ ይሆናል ። ፲፫፡ የሌሎች ሕጎች ተፈጻሚነት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ የጉምሩክ ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋምና አሠራሩንም ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር ፰ ፲፱፻ T ፬ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ሕጎች በዚህ ደንብ ላይ እንደአግባቡ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል ። ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ ከሰኔ ፲፪ ቀን ፲፱፻፯ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፲፪ ቀን ፲፱፻፲ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር