የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፲፮ አዲስ አበባ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፴፪ / ፲፱፻፲፩ ዓ.ም ከጅቡቲ አዲስ አበባ ስለተዘረጋው የምድር ባቡር ከጅቡቲ ሪፐብሊክ መንግሥት ጋር የተደረገውን ስምምነት ለማሻሻል የተደረገው ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ ገጽ ፬፻፲፩ አዋጅ ቁጥር ፩፻፴፱ / ፲፱፻፲፩ ከጅቡቲ አዲስ አበባ ስለተዘረጋው የምድር ባቡር የተደረገውን ስምምነት ለማሻሻል በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በጅቡቲ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት እና በጅቡቲ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል ከጅቡቲ አዲስ አበባ ስለተዘረጋው የምድር ባቡር መጋቢት ፲፪ ቀን ፲፱፻፸፫ ዓም የተደረገውን ስምምነት ለማሻሻል የሚያስችል ስምምነት የካቲት ፲፮ ቀን ፲፱፻፳፬ ዓም ጅቡቲ ላይ የተፈረመ በመሆኑ ፤ ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፲፪ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ ከጅቡቲ አዲስ አበባ ስለተዘረጋው የምድር ባቡር ከጅቡቲ ሪፐብሊክ መንግሥት ጋር የተደረገውን ስምምነት ለማሻሻል የተደረገው ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፴፱ ፲፱፻፲፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ 2.30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ • ዥሺ፩ ገጽ ፬፻፲፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ኅዳር ፳፬ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ፪ የስምምነቱ መጽደቅ መጋቢት ፲፪ ቀን ፲፱፻፻፫ዓም ከጅቡቲ አዲስ አበባ ስለተዘረጋው የምድር ባቡር የተደረገውን ስምምነት ለማሻሻል በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በጅቡቲ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የካቲት ፲፯ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ጅቡቲ ላይ የተፈረመው ስምምነት ጸድቋል ። ፫ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር ሥልጣን የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር ስምምነቱ በሥራ ላይ እንዲውል አስፈላጊውን እርምጃ የመውሰድ ሥልጣን በዚህ ኣዋጅ ተሰጥቶታል ። ፬ • አዋጁየሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከህዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ህዳር፱ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ