የሰ / መ / ቁ . 21684
ሰኔ 7 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ
4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ
አመልካች፡- የኢትዮጵያ ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት
ተጠሪዎች፡- እነ ወ / ገብርኤል ተፈሪ / 25 ሰዎች /
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፡፡
ፍ ር ድ
መዝገቡ ለሰበር ችሎት
የቻለው የአሁኑ አመልካች ጳጉሜ 4 ቀን 1997
ዓ.ም. ጽፎ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ ቅሬታ መነሻነት ነው ፡፡ የአሁኑ አመልካች
በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት መስርቶት በነበረው የፍትሐብሔር ክስ ፣ የድርጅቱ
ሠራተኞች የነበሩት የአሁኖቹ ተጠሪዎች እንደሥራቸው ባህሪይ የሥራ ውሉ ፀንቶ
እስከሚቆይ ድረስ የመኖሪያ ቤቶች ተሰጥቶዋቸው የነበረ መሆኑን ገልጾ የሥራ
ውላቸው በተለያየ ምክንያት ሲቆረጥ ቤቶቹን በነበሩበት ሁኔታ ለድርጅቱ የመመለስ
ግዴታ በህብረት ስምምነቱ ላይ የተመለከተ ቢሆንም ቤቶቹ እስከዛሬ ያልተመለሱለት
መሆኑን ገልጾ በእያንዳንዱ ቤት ላይ የሚኖረውን የቤት ኪራይ አስቦ ክስ የመመስረት
መብቱ እንዲጠበቅለት እና በሕብረት ሥምምነቱና በሕጉ መሠረት ቤቶቹን እንዲረከብ
ውሣኔ እንዲሰጥላት ጠይቋል ፡፡ የሥር ፍ / ቤት ተጠሪዎች ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ
ያ አመመ O S ' A
ል ፡፡ የመዝገብ ቁጥር 21683 ም በአንድነት መቃሚያ እና በፍሬ ነገሩ ላይ የሰጡትን መልስ ተቀብሎ ሰኔ 27 ቀን 1993 ብይን ሰጥቷል ፡፡ ፍ / ቤቱ በሰጠው ብይን ከሣሽ ማለትም የአሁኑ አመልካች ለክሱ መነሻ ለሆኑት ቤቶች ባለቤት ስለመሆኑ ስልጣን ከተሰጠው አካል በፍ / ሕ / ቁ . 1195 መሠረት ያቀረበው የምስክር ወረቀት የለም፡ በተጨማሪ ከሣሽ በፍ / ሕ / ቁ . 1168 መሠረት ቤቶቹን በመያዝ ለአሥራ አምስት አመታት ግብር የከፈለ ለመሆኑ ማስረጃ ያላቀረበ በመሆኑ ለክርክሩ መነሻ በሆኑት ቤቶች ላይ መብት ወይም ጥቅም ያለው መሆኑን ስላላስረዳ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ . 33 / 2 / መሠረት ክስ ሊያቀርብ አይፈቀድለትም የሚል
ይህ ችሎት የአመልካችን የሰበር ቅሬታ ማመልከቻ መርምሮ ታህሣስ 25 ቀን 1998 በዋለው ችሎት ፣ የግል ያልሆኑና ለሕዝብ አገልግሉት የሚሰጡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ የባለሀብትነት መብት ማረጋገጫ መንገዱ ምዝገባ ነው ወይስ አይደለም ? የሚለውን
ሲባል መዝገቡ ለሰበር ይቀርባል ብሎ ወስኖ ግራ
ቀኙ ያደረጉትን የቃል ክርክር
እንዲታይ ወስኗል ፡፡
በመሠረቱ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለን የባለሀብትነት መብት ለማወቅ
ወይም ለማስተላለፍ ወይም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት በግልጽ ወይም በግል
የሚደረጉ ማናቸውም ጽሁፎች በባለሀብትነት ልዩ መዝገብ ውስጥ ሊፃፉ እንደሚገባ
የፍት . ሕግ ቁ . 1567 እና የሚቀጥሉት ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ ፡፡ ሆኖም ከነዚህ
የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ውስጥ
ያልሆኑና ለሕዝብ አገልግሎት
የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ( public Immovables ) በሕጉ ውስጥ የተመለከተው ልዩ
ሁኔታ ከሌለ በስተቀር በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ውስጥ መመዝገብ የሌለባቸው
ስለመሆኑ በቁጥር 1578 / 4 / ላይ ተደንግጓል ፡፡ በዚህ ረገድ የግል ያልሆኑና ለሕዝብ
አላስረዳም በማለት
ነበር 277/87 በ 27 / 1 O / 93 አገልግሎት የተመደቡ የሚያስተዳድሯቸው የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች እንደሌሎች የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች መዝገብ ውስጥ አልገቡም ተብሎ ንብረቶቹን በእውነተኛነት የሚያዙባቸው አካላት የባለቤትነት መብቶቻቸውን ሊያጡ እንደማይገባ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል ፡፡ በያዝነው ጉዳይም ቢሆን የአሁኑ አመልካች ድርጅት ተቋም በሁለት ሉዐላይ አገሮች ስምምነት ተቋቁሞ ላለፉት አንድ መቶ ዓመታት ከላይ የተጠቀሱትን ንብረቶች ጨምሮ ለሕዝብ አገልግሎት ተግባር አውሏቸው የነበረ መሆኑ አከራካሪ አይደለም ፡፡ የአሁኖቹ ተጠሪዎችም ቢሆኑ እነዚህን ቤቶች ከዚሁ ተቋም ጋር ባደረጉት የሥራ ውል መነሻነት ያገኙዋቸው ስለመሆኑ ከክርክሩ ሂደት ለመረዳት ችለናል ፡፡ ይህ ሁኔታ በዚህ መልኩ የተረጋገጠ ሆኖ ሳለ የሥር ፍ / ቤት የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1195 ን በመጥቀስ የአሁኑ አመልካች በቤቶቹ ላይ መብት ያለው መሆኑን
የሰጠውን ብይን ይህ ችሎት አልተቀበለውም ፡፡
ው ሣ ኔ ፣
የፌ / መ / ደ / ፍ / ቤት
በመ / ቁ .
የፌ / ከ / ፍ / ቤት በመ / ቁ . 00491 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል ፡፡
አመልካች ለክርክሩ መነሻ በሆኑት ቤቶች ላይ መብት ያለው መሆኑ ስለተረጋገጠ
በጉዳዩ ላይ የሚቀርበውን ክርክር አድምጦ የመሰለውን እንዲወስን በፍ / ሕ / ሥ /
ሥ / ቁ . 343 / 1 / መሠረት መዝገቡ ለፌ / መ / ደ / ፍ / ቤት ተላልፏል ፣
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻሉ ። መዝገቡ ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
ፍራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክል ግልባጭ
You must login to view the entire document.