የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አሥራ አንደኛ ዓመት ቁጥር ፯ አዲስ አበባ - ሐምሌ ፲፱ ቀን ፲፱፻፲፯ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፲፰ / ፲፱፻፲፯ “ የጨርቃጨርቅና ስፌት ኢንዱስትሪ ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ... ገጽ ፫ሺ፩፻፵፪ የሚኒስትሮች ም / ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፲፰ / ፲፱፻፲፯ የጨርቃጨርቅና ስፌት ኢንዱስትሪ ኢንስቲቲዩት ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን ባወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፷፯ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ፡፡ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የጨርቃጨርቅና ስፌት ኢንዱስትሪ ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር፩፻፲፰ / ፲፱፻፲፯ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ፡፡ ፪ . ትርጓሜ ፤ በዚህ ደንብ ውስጥ “ ሚኒስቴር ” እና “ ሚኒስትር ” 2. Definitions ማለት እንደቅደም ተከተሉ የንግድና እንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ሚኒስትር ነው ፡፡ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣ.ቁ. ፳ሺ ፩ ገጽ ፫ሺ፩፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ ሐምሌ ፲፱ ቀን ፲፱፻፶፯ ቀን ዓ.ም ፫ . መቋቋም ፩ / የጨርቃጨርቅና ስፌት ኢንዱስትሪ ኢንስቲትዩት / ከዚህ በኋላ “ ኢንስቲትዩት ” እየተባለ የሚጠራ / የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መስሪያ ቤት ሆኖ በዚህ ተቋቁሟል ፡፡ ፪ / የኢንስቲትዩቱ ተጠሪነት ለሚኒስቴሩ ይሆናል ፡፡ ፬ . የኢንስቲትዩቱ ዋና መስሪያ ቤት የኢንስቲትዩት ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በሌሎች ቦታዎች ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ሊኖረው ይችላል ፡፡ ' ፭ የኢንስቲትዩቱ ዓላማ የኢንስቲትዩቱ የጨርቃጨርቅና ኢንዱስትሪዎች አለምአቀፍ የምርት ጥራትና ደረጃ ዕውቅና በማግኘት በሀገር ውስጥና በውጭ ገበያ ተወዳዳሪ መሆን እንዲችሉ በገበያ ልማት እንዲሁም አመራር ፣ የቁጥጥርና ኃይላቸውን ለማዳበር የሚረዳና የሚያስፈልጓቸውን ቴክኒሺያኖች በዘላቂነት ለማሟላት የሚያስችላቸው የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠና በመስጠት ማገዝ ይሆናል ፡፡ ፮ . የኢንስቲትዩቱ ስልጣንና ተግባር የመንግሥት ተለይተው የተሰጡት ሥልጣንና ተግባሮች እንደተጠበቁ ኢንስቲትዩቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ . ለጨርቃጨርቅ ስፌት ኢንዱስትሪዎች የገበያ ልማት ድጋፍ ማድረግ እና የስራ አመራርና የምርት ቁጥጥር የአጭር ጊዜ ስልጠና መስጠት ፤ የጨርቃጨርቅና ሥርዓተ ትምህርት በመቅረጽ በዘርፉ የሙያተኞችን ብዛት ለማሳደግና ሠልጣኞችን ከአዳዲስ ጂዎችና አሰራሮች ጋር ለማስተዋወቅ የቅድመ ሥራ ስምሪት እና የሥራ ላይ የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠና በራሱ ወይም ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር መስጠት ፤ ፫ . የጨርቃጨርቅና ስፌት ውጤቶች ጥራትና ብዛት ለማሳደግ የሚያስችል የምርምርና ተግባራትን በራሱ ወይም ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር ማከናወን ፤ ፬ ዘረፉ ያለበትን መሠረት በማድረግ የሚያደርጋቸውን ጥናቶች በሕትመት ወየም በሌላ ዘዴ ማሰራጨት ፤ ፭ . ከዘርፉ ጋር የተያያዘ የላቦራቶሪ ፍተሻ አገልግሎት መስጠት ፤ የጨርቃጨርቅና ስፌት ውጤቶች ጥራትና ብዛትን ለማሳደግና በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ለሚያጋጥሟቸው ችግሮች የምክር አገልግሎት መስጠት ፤ የሚ e ኣውን ገጽ ፫ሺ፩፻፵፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ ሐምሌ ፲፱ ቀን ፲፱፻፲፯ ቀን ዓ.ም ፯ የዘርፉን ልማት ለማሳደግ የሚያስችል የመረጃ አገልግሎት መስጠት ፰ . ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀትና ዲፕሎማ መስጠት ፤ ፱ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ክፍያ ማስከፈል ፧ ፲ የንብረት ባለቤት መሆን ፣ ውል መዋዋል ፣ በራሱ ስም መከሰስና መክሰስ ፤ ፲፩ . ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ማከናወን ፡፡ ፯ . የኢንስቲትዩቱ አቋም ኢንስቲትዩቱ ፣ ፩ . በሚኒስትሩ አቅራቢነት በመንግሥት የሚሾም አንድ ዲሬክተር ፪ . አካዳሚክ ካውንስል ፣ ፫ . አማካሪ ቦርድ ፣ እና ፬ አስፈላጊ ሠራተኞች ፣ ይኖሩታል ፡፡ ፰ . የአማካሪ ቦርድ አባላት የአማካሪ ቦርዱ አባላት በመንግሥት ይመደባሉ ፡፡ ፱ የአማካሪ ቦርዱ ተግባራት ኣማካሪ ቦርዱ የሚከተሉት ተግባራት ይኖሩታል ፤ በጨርቃጨርቅና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሚኒስቴሩና ለኢንስቲትዩቱ ይሰራል ፤ በጨርቃጨርቅና በኢንስቲትዩቱ በሚዘጋጁ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እንዲሁም ኢንስቲትዩቱ በሚያወጣቸው መመሪያዎች ላይ አስተያየት ያቀርባል ፤ ኢንስቲትዩቱ በማቀድና የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በማድረግ ያግዛል ፤ ኢንስቲትዩቱ የሚያከናወናቸውን የምርምር ሥራዎች ይገመግማል ፣ አስተያየት ይሠጣል 5. የጨርቃጨርቅና ኢንዱስትሪዎችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የበኩሉን ምክር ያከፋፍላል ፡፡ ፲ የአማካሪ ቦርዱ ስብሰባ ፩ . ቦርዱ በወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ይኖረዋል ፤ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል ፡፡ ፪ . በቦርዱ ስብሰባ ላይ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አባላት ከተገኙ ምልዐተ - ጉባዔ ይሆናል ፡፡ እንደተጠበቀ ሆኖ ቦርዱ ውሳኔ የሚሰጠው በድምፅ ብልጫ ይሆናል ፤ ሆኖም ድምፅ እኩል ለእኩል የተከፈለ ከሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምፅ ይኖረዋል ፡፡ ገጽ ፫ሺ፩፻፵፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ ሐምሌ ፲፱ ቀን ፲፱፻፲፯ ቀን ዓ.ም ፬ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ፡፡ ፲፩ . የዲሬክተሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ . ዲሬክተሩ የኢንስቲትዩቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ከሚኒስትሩ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የኢንስቲትዩቱን ሥራዎች ይመራል ፤ ያስተዳድራል ፡፡ ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመሰከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ዲሬክተሩ ፣ ሀ ) በዚህ ደንበ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከቱትን የኢንስቲትዩትን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ሕግና በመንግሥት በሚፈቀድለት የደመወዝ የኢንስቲትዩቱን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፤ ሐ ) የእንስቲትዩቱን የሥራ ፐሮግራምና በጀት አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ፣ ሲፈቀደም ተግባራዊ ያደርጋል ፤ መ ) ለኢንስቲትዩቱ በተፈቀደው በጀትና የሥራ ፕሮግረም ያደርጋል ፤ ከሦስተኛ በሚደረጉ ግንኙነቶች ኢንስቲትዩትን ይወክላል ፤ ረ ) የኢንስቲትዩቱን የሥራ አፈፃፀምና የሂሣብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ፡፡ ፫ ዲሬክተሩ ለኢንስቲትዩቱ ሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ ሥልጣንና ተግባሩን ለእንስቲትዩቱ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል ፡፡ ፲፪ . ስለአካዳሚ ካውንስሉ አባላት የኢንስቲትዩቱ አካዳሚክ ካውንስል የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ፤ ፩ . የኢንስቲትዩቱ ዳሬክተር ...... ሰብሳቢ ፪ . የኢንስቲትዩቱ ሬጅስትራር ፫ . የመምህራን ተወካይ ፬ ከኢንስቲትዩቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች በሚኒስቴሩ የሚሰየሙ ተወካዮች ፲፫ የአካዳሚክ ካውንስሉ ሥልጣንና ተግባር የአካዳሚክ ካውንስሉ የሚከተሉት ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ሥልጣንና ጽ ፫ሺ፩፻፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ ሐምሌ ፲፱ ቀን ፲፱፻፲፯ ቀን ዓ.ም ፩ . የኢንስቲትዩትን ልዩ ልዩ የትምህርት ፕሮ ግራሞችና ካሌንደር ለሚኒስቴሩ የማቅረብ ፤ ፪ . ዲፕሎማ ፣ ሠርተፊኬትና ልዩ ሽልማት የሚሰ ጥበትን ሁኔታ እያጠና ሰሚኒስቴሩ የማቅረብ ፤ ፫ የሠላጣኞች አቀባበልን ፣ የትምህርት ደረጃ አወሳሰንና ምዘናን ፣ የዲስፕሊንና ጉዳዮችን የሚመለከቱ መመዘኛ መስፈርቶችን አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩ የማቅረብ ፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ የማድረግ ፤ በነዚህ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን የመስጠት ፤ ፬ አጠቃላይ የፈተና አሰጣጥ ዘዴና የመወሰን ፤ ፭ ስለአካዳሚክ እድገቶች ጉዳይ አጥንቶ ኒስቴሩ የማቅረብ ፤ ፮ . የራሱን የስብሰባ ሥነ - ሥርዓት የመወሰን ፯ . በሚንስቴሩ የሚሠጡትን ሌሎች ተግባሮች የማከናወን ፡፡ ፲፬ በጀት የኢንስቲትዩቱ ከሚከተሉት የተውጣጣ ይሆናል ፡፡ ፩ . በፌዴራል መንግሥት ከሚመደብለት የገንዘብ ፪ . ከሚሰበስበው የአግልግሎት ክፍያ ፤ ፫ . ከዕርዳታ ፣ ከስጦታና ከማናቸውም ሌሎች ምን ፲፭ . የሂሣብ መዛግብት ፩ . ኢንስቲትዩቱ የተሟሉና ትክክለኛ ግብት ይይዛል ፡፡ ፪ . የኢንስቲትዩቱ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ በሚሰይመው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ፡፡ ፲፮ ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ፡፡ አዲስ አበባ ሐምሌ ፲፱ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር