×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 67492 የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት አስተዳደር ማቋቋሚያ ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፵፱ አዲስ አበባ ጳገሜ ፩ ቀን ፲፱፻፪ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፵፯ / ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት አስተዳደር ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፭ሺ፫፻፲፪ የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት አስተዳደርን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ዥ፯ አንቀጽ ፭ እና በአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ T ፯ አንቀጽ ፮ | Ethiopia Proclamation No. 4/1995 and Article 6 ( 3 ) of the ( ፫ ) መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ክፍል አንድ አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት አስተዳደር ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፷፯ ፲፱፻ን፪ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ፡ ፩ “ ኮሚሽን ” ወይም “ ኮሚሽነር ” ማለት እንደአገባቡ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ወይም ኮሚሽነር ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፱ሺ፩ ገጽ ፭ሺ፫፻፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ሣሀ ጳጉሜ ፩ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ • ም • ፪ . “ አስቸኳይ የምግብ እጥረት ” ማለት የሰብል መጥፋት ወይም የከብቶች እልቂትና እንደነገሩ ሁኔታ በድርቅ፡ በጎርፍ፡ በመሬት መንቀጥቀጥና መናድ፡ በፀረ ሰብል ተባይ ወይም በሰብል በሽታ ምክንያት ወይም እንደ ጦርነት ባሉ ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት ሊከሰት የሚችል አስከፊና ሰፊ የሆነ በተለይም ደግሞ በኅብረ ተሰቡ ላይ ረሃብና መፈናቀልን የሚያስከትል የምግብ እጥረትና ይህንኑ ችግር በመደበኛ የምግብ አቅርቦት አሠራር ለመቋቋም የማይቻልበት ሁኔታ መከሰት ነው፡ ፫ “ በዝግመት የሚከሰቱ አደጋዎች ” ማለት ለዝግጅት በቂ ጊዜ በሚሰጥ ሁኔታ በድርቅ፡ በሰብል ተባይ ፣ በሰብል በሽታ፡ ወዘተ..ችግሮች ምክንያት የሚከሰቱና አስቀድሞ ሊተነበዩ የሚችሉ አደጋዎችን የሚያካትት “ በድንገት የሚከሰቱ አደጋዎች ” ማለት ለዝግጅት በቂ ጊዜ በማይሰጥ ሁኔታ የሚከሰቱ ጎርፍን ፣ የመሬት መንቀጥቀጥን ወይም መናድን፡ ወዘተአደጋዎች የሚ ያካትት ነው፡ “ ምግብ - ነክ ያልሆኑ የእርዳታ ቁሳቁሶች ” ማለት በድንገት በሚከሰቱ አደጋዎች ምክንያት ሊያጋጥም የሚችለውን ጉዳት ለመከላከልና ለመቀነስ የሚያስችል የፈልጎ ማዳኛ መሣሪያዎች፡ የመጠለያ ቁሳቁሶች፡ የማ ብሰያና የመመገቢያ ቁሳቁሶች፡ የውሃ ማጠራቀሚያ ቁሳቁሶች፡ የእርዳታ ሰጪ ሠራተኞች መገልገያዎችና ሌሎች የሎጂስቲክ ቁሳቁሶች ናቸው፡ “ ክምችት ” ማለት አስቸኳይ የምግብ እጥረትን ለመቋ ቋምና በድንገት ወይም በዝግመት በሚከሰቱ አደጋዎች ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመከላከል እንዲ ያስችል የሚያዝ የመጠባበቂያ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ክምችት ነው ። ክፍል ሁለት ስለመጠባበቂያ ክምችት ፫ የክምችቱ፡ ዓላማ ክምችቱ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፣ ፩ : የመጠባበቂያ ምግብ ክምችቱ ዓላማ በዝግመትና በድንገት የሚከሰቱ አደጋዎች ሲያጋጥሙ፡ በተለያዩ መንገዶች ተጨማሪ ምግብ ማሰባሰብ እስኪቻል ፣ በብድር መልክ ለኮሚሽኑና በእርዳታ ሥራ ለተሠማሩ ድርጅቶች ከክምችቱ አውጥቶ በመስጠት አደጋን ለመከ ላከል የሚያስችል አቅም መፍጠር፡ ፪ : የመጠባበቂያ ምግብ ነክ ያልሆኑ የእርዳታ ቁሳቁሶች ክምችት ዓላማ በድንገት የሚከሰቱ አደጋዎች ሲያጋጥሙ፡ በተለያዩ መንገዶች ተጨማሪ ምግብ - ነክ ያልሆኑ የእርዳታ ቁሳቁሶች ማሰባሰብ እስኪቻል፡ በብደርና በትውስት ለኮሚሽኑና በእርዳታ ሥራ ለተሠማሩ ድርጅቶች ከክምችቱ አውጥቶ በመስጠት አደጋን ለመከላከል የሚያስችል አቅም መፍጠር ። ፬ . የክምችቱ ምንጭ ክምችቱ ከሚከተሉት ምንጮች የሚገኝ ይሆናል፡ ፩ ለክምችቱ ማሳደጊያ ከሚደረግ የመንግሥት ድጋፍ ፣ እና ፪ • ከእርዳታ ሰጪዎች ከሚገኝ ልገሳ ። ፭ የክምችቱ ዓይነትና መጠን ፩ በመጠባበቂያነት የሚያዘው ዋና ዋና የምግብ ክምችት ዓይነት ስንዴ፡ በቆሎ፡ ማሽላና እንዳስፈላጊነቱ ሌሎችንም የሚጨምር ሲሆን ፣ መጠኑም በመንግሥት ይወሰናል ። ፪ በመጠባበቂያነት የሚያዘው ምግብ - ነክ ያልሆኑ የእርዳታ በቁሳቁሶች ክምችት የመጠለያ፡ የማብሰያና መመገቢያ፡ የውሃ ማጠራቀሚያ ቁሳቁሶችን ፣ የፈልጎ ማዳኛ መሣሪያዎችን፡ በእርዳታ ሥራ ለሚሠማሩ ሠራተኞች የሚሆኑ መገልገያዎችንና ሌሎች መሰል ቁሳቁሶችን የሚያካትት ሲሆን ፣ ከእያንዳንዱ ዓይነት የሚያዙ ቁሳቁሶችን ብዛት ኮሚሽኑ በጥናት ላይ ተመርኩዞ ይወስናል ። ገጽ ፩ሺ፫የን 0 ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ሣሀ ጳጉሜ ፩ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም ፮ የክምችቱ ባለቤት በክምችቱ ላይ የባለቤትነት መብት የሚኖረው የፌዴራሉ መንግሥት ይሆናል ። ክፍል ሦስት የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት አስተዳደርን ስለማቋቋም ፯ መቋቋም ፩ የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት አስተዳደር ከዚህ በኋላ “ አስተዳደሩ ” እየተባለ የሚጠራ በዚህ ተቋቁሟል ። ፪ • የአስተዳደሩ ተጠሪነት ለኮሚሽኑ ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የአስተዳደሩ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖ ለክምችት አያያዝ አመቺ በሆኑ ስትራቴጂክ ቦታዎች የማከማቻ መጋዘኖ ችንና ቅርንጫፍ የመጋዘን አስተዳደር ጽ / ቤቶችን ሊያቋቁም ይችላል ። ፬ የአስተዳደሩ ሥልጣንና ተግባር አስተዳደሩ የሚከተለው ሥልጣንና ተግባር ይኖረዋል፡ ፩- ክምችቱን የማስተዳደር፡ ፪ . ለክምችት አስፈላጊ የሆነውን ምግብና ምግብ - ነክ ያልሆኑ የእርዳታ ቁሳቁሶችን በእርዳታ የማግኘትና የመቀበል፡ እንዳስፈላጊነቱም ከሀገር ውስጥ ወይም ከውጭ ሀገር የመግዛት፡ በእርዳታ ወይም በግዥ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ የእርዳታ ቁሳቁሶችን የማከማቸት፡ ፬ አስቸኳይ የምግብ እጥረትን ለመቋቋም ይቻል ዘንድ የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት ቦርድ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ከክምችቱ ምግብ በብድር እንዲወጣ የማድረግ፡ የምግብ ክምችቱን ከተባይ ጥቃት ለመከላከል የሚያስ ፈልጉ ፀረ - ተባይ ኬሚካሎችንና መድሃኒቶችን የመያዝ፡ በክምችት የቆየ እህልን የማለዋወጥ፡ የምግብ ክምችቱ ላይ የጥራት ቁጥጥር ለማድረግ የሚረዳ ላቦራቶሪ የማደ ወደ ክምችቱ የሚገባውንና ከክምችቱ የሚወጣውን ምግብ ጥራት የመመርመርና የመቆጣጠር፡ የጥራት ደረጃውን ያልጠበቀ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ የእርዳታ ቁሳቁሶች ወደ ክምችቱ እንዳይገቡ የማድረግ ፣ ፯ ምግብ ነክ ያልሆኑ የእርዳታ ቁሳቁሶችን የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት ቦርድ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት በብድርና በትውስት መልክ ጥቅም ላይ እንዲውል የማድረግ፡ ፯ መጋዘኖችንና የማከማቻ አገልግሎቶችን የማሠራትና የማከራየት፡ ሀ . የንብረት ባለቤት የመሆን፡ ውል የመዋዋል፡ በስሙ የመክሰስና የመከሰስ፡ ፲ . የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የሚያግዙ ሌሎች | 10. Organiazation of the Administration ተመሳሳይ ተግባሮችን የማከናወን ። የአስተዳደሩ አቋም አስተዳደሩ ፩ : የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) ፡ ፪ • የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት የቴክኒክ ኮሚቴ ( ከዚህ በኋላ “ የቴክኒክ ኮሚቴው ” እየተባለ የሚጠራ ) ፣ ፫ • በኮሚሽነሩ አቅራቢነት በመንግሥት የሚሾም አንድ ሥራ አስኪያጅ፡ ፬ . አስፈላጊ ድርጅታዊ መዋቅርና ሠራተኞች ፣ ይኖሩታል ። ገጽ ፩ሺ፪፻፲፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፬ ጳጉሜ ፩ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም : የቦርዱ አባላት ቦርዱ በኮሚሽነሩ ሰብሳቢነት የሚመራ ሆኖ አግባብ ካላቸው የመንግሥት ተቋሞች በመንግሥት የሚሰየሙ አባላት ይኖሩታል ። የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ ከክምችቱ ጋር የተያያዙ የፖሊሲ ሃሳቦችን የማመ ንጨት፡ ለመንግሥት የማቅረብና ሲፀድቁም ተግባራዊ ነታቸውን የመከታተል፡ ፪ ክምችቱን ለማሳደግና ደህንነቱን ለመንከባከብ የሚያ ስችሉ ጉዳዮች ላይ የመወሰን፡ ፫ ምግብና ምግብ – ነክ ያልሆኑ የእርዳታ ቁሳቁሶች በብድር ወይም በትውስት እንዲሰጡ የመወሰን ፣ በየጊዜው በብድር ወይም በትውስት የተሰጠውምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ የእርዳታ ቁሳቁሶች በወቅቱ መመለ ሳቸውን የማረጋገጥ፡ ፭ አስተዳደሩ ከሚኖረው ክምችት ውስጥ በማንኛውም ጊዜ በክምችትነት ሊኖር የሚገባውን አነስተኛ መጠን የመወሰን፡ በማንኛውም ጊዜ በክምችት ሊኖርከሚገባው አነስተኛ መጠን ላይ በብድር ወይም በትውስት ወጥቶ ሊሰጥ የሚያስፈልግበት ሲያጋጥም እንዲሰጥ የመወሰን፡ ጊ ከላይ ከተጠቀሱ ሥራዎች ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ መመሪያ የማውጣት ። የቦርዱ ስብሰባ ቦርዱ በየሶስት ወር ቢያንስ አንድ መደበኛ ስብሰባ ይኖረዋል፡ እንዳስፈላጊነቱም በማናቸውም አስቸኳይ ስብሰባዎች ሊኖሩት ይችላል ። የቦርዱ መደበኛ ስብሰባ የሚጠራው በሰብሳቢው ሲሆን አስቸኳይና ልዩ ስብሰባ ግን በሰብሳቢው ወይም ሁለትና ከሁለት በላይ የቦርዱ አባላት በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት ሊጠራ ይችላል ። ከአባላቱ ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል ። የቦርዱ ውሳኔ የሚተላለፈው በስብሰባው ላይ በተገኙ አባላት ድምጸ ብልጫ ይሆናል፡ ድምጹ እኩል ለእኩል ከተከፈለ ግን ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት የሚመለከት ውስጠ ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። የቴክኒክ ኮሚቴው አባላት የቴክኒክ ኮሚቴው በአስተዳደሩ ሥራ አስኪያጅ ሰብሳቢነት የሚመራ ሆኖ አግባብነት ካላቸው የመንግሥት ተቋማት፡ የውጪ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶችና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች በቦርዱ የሚሰየሙ አባላት ይኖሩታል ። የቴክኒክ ኮሚቴው ሥልጣንና ተግባር የቴክኒክ ኮሚቴው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡ ለአስቸኳይ የምግብ እጥረት መቋቋሚያ እንዲሆን ለአስ ተዳደሩ የሚቀርቡ የእህል ብድር ጥያቄዎችን በመመ ርመር የውሳኔ ሃሳብ በኣስተዳደሩ በኩል ለቦርዱ ማቅረብ፡ ፪ ክምችቱን ለማሳደግ በሚቻልበት መንገድ አስተዳ ደሩን ማማከር፡ በብድር የሚሰጠውን የምግብ ክምችትመጠን፡ በብድር የተሰጠው ምግብ በወቅቱ ስለሚመለስበትና በክምችት ላይ ለረኝዥም ጊዜ የቆየ እህል በአዲስ የሚቀየርበትን ሁኔታ በሚመለከት ለአስተዳደሩ ምክር መስጠት፡ ገጽ ፩ሺ፪፻፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ጳጉሜ ፩ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም • ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት አስቸኳይ የምግብ እጥረትን ለመቋቋም እንዲቻል ምግብ ከክምችቱ በብድር እንዲሰጥ መፍቀድ ፤ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት በድንገት የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቋቋም እንዲቻል ምግብ - ነክ ያልሆኑ የእርዳታ ቁሳቁሶች በብድር ወይም በትውስት መልክ ከክምችቱ ወጥቶ እንዲሰጥ መፍቀድ ፤ ምግብ ነክ ያልሆኑየእርዳታቁሳቁሶችን ክምችት አስተ ዳደር፡ ኣያያዝና አጠቃቀም በሚመለከት ለአስተዳደሩ ምክር መስጠት፡ ፯ ምግብ - ነክ ያልሆኑ የእርዳታ ቁሳቁሶች ክምችቱን ዓይነት፡ መጠንና ደረጃ በሚመለከት በአስተዳደሩ በኩል ለቦርዱ የውሳኔ ሃሳብ ማቅረብ ፣ ፰ ምግብ ነክ ያልሆነውን ክምችት አወጣጥ አጠቃቀም / ፡ ጥቅም ላይ የዋለውን ክምችት መልሶ ለመተካት የሚኖ ረውን ሥርዓት ለመዘርጋትና ለማሻሻል የሚረዱ ሀሳቦችን አጥንቶ በአስተዳደሩ በኩል ለቦርዱ ውሳኔ ማቅረብ ፣ እና ሀ . ሌሎች ቴክኒክ ነክ ጉዳዮችን በተመለከተ በራሱ አነሳ ሽነት ወይም ከአስተዳደሩ ጥያቄ ሲቀርብለት ምክር መስጠት ። ፲፮ የቴክኒክ ኮሚቴው ስብሰባ ፩ የቴክኒክ ኮሚቴው ሰብሳቢው በሚያቀርበው ጥሪ መሠረት ይሰበሰባል ። ፪ : አስቸኳይ ስብሰባ ግን በሰብሳቢው ወይም ከግማሽ በላይ የኮሚቴው አባላት በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት ሊጠራ ይችላል ። ፫ ከቴክኒክ ኮሚቴው አባላት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በስብሰባ ላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል ። ፬ . የቴክኒክ ኮሚቴው ውሳኔ የሚተላለፈው በስብሰባው ላይ በተገኙ አባላት ድምጽ ብልጫ ይሆናል ፤ ድምጹ እኩል ከተከፈለ ግን ሰባሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ፲፯ የሥራ አስኪያጁ ሥልጣንና ተግባር አስኪያጁ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡ ፩ . ሥራ አስኪያጁ የአስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ፤ ቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የአስታ ዳደሩን ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል ፤ በዚህ አንቀጽ፡ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ላይ የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ሥራ አስኪያጁ፡ ሀ ) በዚህ ደንብ በአንቀጽ ፬ የተመለከተውን የአስተ ዳደሩን ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ ያውላል ፤ . አስተዳደሩን ያደራጃል ፣ በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግና ደንብ መሠረት ሠራተኞችን ይቀጥራል፡ ያስተዳድራል ፣ ሐ ) እያንዳንዱ የበጀት ዓመት ከመጀመሩ ከሦስት ወር በፊት የአስተዳደሩን ዓመታዊ በጀትና የሥራ ዕቅድ በማዘጋጀት ለቦርዱ አቅርቦ በማስ በኮሚሽኑ አማካኝነት ለመንግሥት ያቀርባል፡ መ ) ለአስተዳደሩ በተፈቀደው በጀትና የሥራ ዕቅድ መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፣ ሠ ) ተጠሪነታቸው ለራሱ የሆኑትን የአስተደደሩን የሥራ ኃላፊዎች በመምረጥ ለቦርዱ አቅርቦ ያሾማል፡ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረትከክምችቱ ምግብ በብድር፡ ምግብ ነክ ያልሆኑ የእርዳታ ቁሳቁሶችን ደግሞ በብድር ወይም በትውስት ይሰጣል፡ ገጽ ፩ሺ፫የኝ ፤ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፱ ጳጉሜ ፩ ቀን ፲፱፻፲፪ ዓም ሰ ) የቴክኒክ ኮሚቴውን እያማከረ በእያንዳንዱ ማከማቻ | ( g ) upon the advice of the technical Committee , execute the ቦታ የሚቀመጠውን የምግብ ክምችት መጠንና ስብጥር ያስፈጽማል፡ ሽ ) በብድርና በትውስት የተሰጠው ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ የእርዳታ ቁሳቁሶች በወቅቱ መመለሳቸውን ይከታተላል፡ ቀ ) አስተዳደሩ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ሁሉ አስተዳደሩን ይወክላል፡ በ ) ለአስተዳደሩ ሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ከሥል ጣንና ተግባሩ በከፊል ለአስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። የበጀት ምንጭ የአስተዳደሩ የበጀት ምንጭ፡ ፩ መንግሥት ከሚመድብለት ዓመታዊ በጀት፡እና ፪ • ከሌሎች ምንጮች ይሆናል ። ስለ ሂሣብ መዛግብት አያያዝና ስለ ምርመራ ፩ አስተዳደሩ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብ ቶችን ከደጋፊ ሰነዶች ጋር በተሟላ መልኩ ይይዛል ። ፪- የአስተዳደሩ የሂሣብ መዛግብትና የገንዘብ ነክ ጉዳዮች እንዲሁም የክምችቱ ሁኔታ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ በዋና ኦዲተር ወይም እርሱ በሚወክለው ኦዲተር ይመረመራል ። ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፳ ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ደንቦችና መመሪያዎች ከዚህ ደንብ ጋር የሚቃረኑ ደንቦችና መመሪያዎች በዚህ ደንብ ውስጥ የተካተቱ ጉዳዮችን በሚመለከት ተፈጸሚነት አይኖራቸውም ። ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጳጉሜ ፩ ቀን ፲፱፻፲፪ ዓ.ም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?