የመ / ቁ .18342
ታህሣሥ 17 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኞች 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ 3. ኣቶ ተገኔ ጌታነህ 4. አቶ ዳኜ መላኩ 5. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
አመልካች፡- የማህበራዊ ዋስትና ባለስልጣን መልስ ሰጭዎች፡- 1 ኛ- አቶ ብርሃኑ ህሩይ
2 ኛ- አቶ ከበደ ገ / ማርያም
ስለማኀበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ - የማኅበራዊ ዋስትና ባልስልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 38/1988 አንቀጽ 11 / 1 / : - ስሰፍርድ ቤቶች ስልጣን የፍትሐ ብሄር ሥነ ስርዓት ህግ ቁጥር 4
የማህበራዊ ዋስትና መብትንና ጥቅምን በሚመለከት የማኅበራዊ ዋስትና ባለስልጣን በሰጠው ውሳኔ ይግባኝ የቀረበለት የማኀበራዊ
ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ የመጨረሻ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ የፌዴራል - ' 4 የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት ጉዳዩን አይቶ ውሳኔ ስለሰጠና ውሳኔውንም
? የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ስላደናው የቀረበ አቤቱታ ።
ውሣኔ፡- የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት የሰጠውና የፌዴራል
ከፍተኛ ፍ / ቤት ያጸናው ውሳኔ ተሽሯል ፡፡
1. በህግ ተለይተው በአስተዳራዊ ውሳኔ እንዲቋጩ በተባሉ ጉዳዮች ላይ
መደበኛ ፍ / ቤት የመዳኘት የስረ ነገር ስልጣን የለውም ፡፡
2. የማህበራዊ ዋስትና መብትንና ጥቅምን በሚመለከት የማኅበራዊ
መደበኛ ፍ / ቤቶች ጉዳዩን ለማየት የስራ ነገር ስልጣን የላቸውም ፡፡
የሰ / መ / ቁ 18342
ታህሣሥ 17 ቀን 1998 ዓም
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ
እብዱልቃድር መሐመድ
ተጉ ጌታነህ
ዳኜ መላኩ
መስፍን ዕቁበዮናስ
አመልካች፡- የማህበራዊ ዋስትና ሳለሥልጣን ነገረፈጁ አቶ ፈርተውሃል ኃ / ጊዮርጊስ ቀረበ
ተጠሪዎች ፤ 1 ኛ / አቶ ብርሃኑ ሕሩይ ቀረበ
2 ኛ / አቶ ከበደ ገ / ማርያም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል ፡፡
ፍ ር ድ የሰበር አቤቱታው ክሩን በመጀመሪያ ያየው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት ከሣሾች የሆኑት የአሁኑ ተጠሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተቀጥረን ስናገለግል በቆየንባቸው ለጡረታ አበል እየተባለ ከደመወዛችን ከመቶ አራት ፣ ከአሠሪው መሥሪያ ቤት ደግሞ በመቶ ስድስት እየተቀነሰ ለማህበራዊ ዋብትና ባለሥልጣን ገቢ ተደርጓል ያሉትን ገንዘብ የሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት ወደነበረበት እንዲመልስ ፣ • የማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን በበኩሉ ያለአግባብ ከከሣሾች ሂሣብ ወጪ በማድረግ ለትምህርት ቤቱ የሰጠውን ገንዘብ ወደነበረበት ሂሣብ ተመላሽ እንዲያደርግ በሚል የሰጠውን ውሣኔ ከፍተኛው ፍ / ቤት ትክክል ነው ብሉ በማጽናቱ ምክንያት የቀረበ
አመልካች በዚህ ጉዳይ በተሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚልባቸው ምክንያቶች የአሁኑ ተጠሪዎች ይህንኑ ከጡረታ አበል ጋር የተያያዘውን ገንዘብ ጉዳይ በሚመለከት ለማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን ጥያቄ አቅርበው መሥሪያ ቤቱ ሰሕጉ መሠረት አይቶ ከወሰነ በኋላ ለይግባኝ ሰሚ ጉባዔ አመልክተው የመጨረሻ ውሣኔ ሰጥቶበታል ጉባዔው በአዋጅ ቁጥር 38/88 አንቀጽ 11 ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚስጠው ውሣኔም
የመጨረሻ ስለሆነ ከዚህ በኋላ በዚሁ ጉዳይ ለፍ / ቤት ክሥ ልቀርብበት
ር ሶት ሆኖ በመገኘቱ አይችልም ። ፍ / ቤት በፍ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ 5 መሠረት ክሱ ተቀባይነት የለውም መወሰን ነበረበት ፡፡ ከጡረታ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የተነሣውን ጥያቄ መደበኛ ፍ / ቤት አይቶ የመወሰን ሥልጣን የለውም ፡፡ የህንን ጉዳይ በየደረጃው የተመለከቱት ፍ / ቤቶች ሕጉን በአግባቡ ሣይተረጉሙ ቀርተዋል በሚል የቀረቡ ናቸው ፡፡ ጉዳዩ ለሰበር ችሉት እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን በአመልካች በኩል የቀረበው ማመልከቻም ለአሁኑ ተጠሪዎች ተልኮ ግንቦት 15 ቀን 1997 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል ፡፡ አመልካች በበኩሉ የመልስ መልስ ሰጥቶበት ተከራክሯል ።
በተጠሪዎች በኩል የቀረበው ክርክር ጠቅለል ባለ አመልካች ያለኣግባብ ከእኛ ሂሣብ አውጥቶ የሰጠውን ገንዘብ በሚመለከት የጡረታ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ለማህበራዊ ዋስትና ሳለሥልጣንም ሆነ ለይግባኝ ሰሚ ጉባዔ ክሥ አቅርበን በሥማችን ውጭ ስለመስጠቱ የሚያስረዳ
ማሥረጃ አላቀረበም ፡፡ የአገልግሉት ዘመናችን ተቀንሶብናል ወይም ያለአግባብ ዕ
ድሜአችን ለጡረታ ሣይደርስ በጡረታ እንድንገለል ተደርጓል በሚል ያቀረብነው ክስ ስለሌለ በጡረታ ሕጉ መሠረት የሚታይ ጉዳይ የለም ፡፡ አመልካች አላገባብ ከሃሣባችን አውጥቶ የሰጠውን ገንዘብ ተቀብሉ ወደነበረበት ሂሣብ እንዲያስገባ በሚል የቀረበውን ክሥ አይቶ የመወሰን ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት ነው ። የሊሴ ገ / ማርያም ትምህርት ቤት አመልካቹ መሥሪያ ቤትን ጠይቆ የወሰደው ገንዘብ አላገባብ መሆኑን አምኖ ፍ / ቤት በሰጠው ውሣኔ መሠረት መልሶ ገቢ ስላደረገ አመልካች አልፈጽምም የሚልበት ምክንያት የለም የሚል ይዘት ያለው
ችሉቱም የአሁኑ ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ ይፈፀምልን ያሉትን ጉዳይ ፍርድ ቤት አይቶ የመወሰን ሥልጣን ያለው መሆን አለመሆኑን መርምሯል ፡፡ በአዲስ መልክ የማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣንን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ቁጥር 38/88 ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የሚፈጽማቸውን ተግባሮች እና የትሰጠውን ሥልጣን የሚዘረዝር ሲሆን በዚህ አንቀጽ ሥር ከታቀፉት ንዑስ አንቀጾች መካከል በንዑስ አንቀጽ 8 ላይ የተመለከተው ሲታይ የማህበራዊ ዋስትና . ባለሥልጣን አግባብ ባላቸው ሕጉች መሠረት በሚቀርቡ የማህበራዊ ዋስትና መብትና ጥቅም ጥያቄዎች ላይ ውሣኔ የመስጠት
የተሰጠው ያረጋግጣል ። የማህበራዊ
መብትና ጥቅም በሚመለከት በሚሰጠው ውጭ ላይ ይግባኝ የሚቀርበው በአዋጁ
አንቀጽ 11 ላይ ሥልጣን ለተሰጠው ለማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ ነው :: ይግባኝ ሰሚው ጉባዔ የማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን ሰሚሰጠው ውሣኔ ላይ የሚቀርቡትን ይግባኞች መርምሮ የማሳጠው ውሣኔ የመጨረሻ ነው ። በሕጉ የማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ በአንድ የማህበራዊ ዋስትና ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ውሣኔ የመጨረሻ ነው ከተባለ ከዚህ በኋላ በይግባኝ ደረጃም ሆነ በክሥ ወደ መደበኛ ፍ / ቤት የሚሄድበት መንገድ የለም ማለት ነው ። በሕግ ተለይተው በኣስተዳደራዊ ውሣኔ እንዲቋጩ በተባሉ ጉዳዮች ላይ መደበኛ ፍ / ቤት የመዳኘት የሥረ ነገር ሥልጣን ስለሌለው በሕጉ መሠረት ለአንድ
አስተዳደር አካል ቀርቦ አስተዳደራዊ ውጭ የተሰጠበትን ጉዳይ
ጉዳይ ወይም ለእስተዳደር መቅረብ የሚገባውን ጉዳይ ፍ / ቤት ሊያስተናግድም ሆነ ኣከራክሮ ውሣኔ ሊሰጥበት አይችልም ፡፡ ለአንዳንድ የመንግሥት አስተዳደር አካላት በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የመወሰን ስልጣን የሚሰጡት ሕጉች መጠበቅና መከበር ይኖርባቸዋል ፡፡ የዳኝነት ሥልጣንም በሕግ የተወሰነ ስለሆነ የመተርጉም ሥራው በሕግ ማቀፍ የሚመራ ነው ። ስለዚህ በአስተዳደራዊ ውሣኔ የመጨረሻ እልባት እንዲያገኙ በሕግ ተለይተው የተቀመጡ ጉዳዮችን ሁሉ ፍርድ ቤት አይቶ ከመወሰን ሊገደብ አይችልም የሚለው አስተሳሰብ ተቀባይነት የለውም ፡፡ በፍ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ 4 ላይ ሰፍርድ ቤቶች እንደተገለፀው ሕግ በግልጽ ከታገዱ በጉዳዩ ላይ እከራክሮ የመወሰን የላቸውም ፡፡
ተጠሪዎች አመልካችን ሊከሱ የቻሉበት ምክንያት በቀረቡት ክስ ይፈፀምልን በሚል ያነሱት ጥያቄ ከማህበራዊ ዋስትና ጉዳይ ጋራ ተያያነት ያለው ስለመሆን አለመሆኑ ሲመረመር በመጀመሪያ በትምህርት ሚኒስቴር ተቀጥረው ሲሰሩ ቢቆዩባቸው አመታት ለጡረታ መዋጮ እየተባለ ከእያንዳንዳቸው ደመወዝ በወር በመቶ አራት ፣ ከአሠሪው መሥሪያ ቤት ደግሞ ስድስት እየተዋጣ
እየተዋጣ በማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን በየሥማቸው በተከፈተ ሂሣብ ገቢ ሲደረግ የቆየው ገንዘብ በኋላ ወደተዛወሩበት የሌሴ ገ / ማርያም ትምህርት ቤት መተላለፉን ገልፀዋል ።
ተጠሪዎች አመልካች የጡረታ ' መዋጮውን / ማርያም ትምህርት ቤት ያስተላለፈው አላገባብ ነው ይበሉ እንጅ በክሣቸው ላይ ከገለፁት ፍሬ ነገር እንደሚታየው ከጥር ወር 1989 ዓ.ም ጀምሮ በጡረታ እንዲገለሉ ተደርጓል ። ወደ ሊሴ ገ / ማርያም ትምህርት ቤት እንዲተላለፍ ተደርጓል የሚሉት ትምህርት ሚኒስቴር ሲሰሩ በነበረበት ወቅት ' የተዋጣው
የጡረታ መዋጮ ወደ ማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን እንዲመለስ የሚጠይቁትም
ይኸው ታስቦ በጡረታ አበላቸው ላይ እንዲጨመር ለማድረግ ወይም በሕጉ
መሠረት ይገባናል የሚሉትን መብት ለማስከበር እንጅ ለሌላ ጉዳይ ለማመቻቸት አይደለም :: የምናነሣው የማህበራዊ ዋስትና መብትም ሆነ ጥቅም የለም የሚሉ ከሆነ ደግሞ የጡረታ መዋጮው ቀደም ሲል በማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን በሥማቸው ተከፍቶ ወደነበረው ሂሣብ እንዲመለስ የሚጠይቁበት ምክንያት አይኖርም ፡፡ የጡረታ መዋጮም በቀጥታ ከማህበራዊ ዋስትና መብትና ጥቅም ጋራ ተያይዞ የሚታይ ነው ። ተጠሪዎች ወደሊሴ ገ / ማርያም ትምህርት ቤት ተላልፏል የሚሉት የጡረታ መዋጮ ወደ ማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን እንዲመለስ ተደርጉ በሕጉ መሠረት የሚገባን የማህበራዊ ዋስትና መብትና ጥቅም ኣለ ካሉ ከላይ በተጠቀሰው አዋጅ ቁጥር 38/88 አንቀጽ 5 ( 8 ) መሠረት ለማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን ጥያቄአቸውን አቅርበው እንዲሰጥበት ማድረግ አለባቸው ፡፡ ተጠሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር ተቀጥረው ሲሰሩ በቆዩባቸው አመታት ተዋጥቷል የሚሉት የጡረታ መዋጮ እንዲተላለፍ ከተደረገበት የሊሴ ገ / ማርያም ትምህርት ቤት ወደማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን ካዝና እንዲመለስ መጠየቁ ብቻ በሕጉ ትርጉም የለውም ።
የለውም ፡፡ ወደ ሊሴ ገ / ማርያም ትምህርት ቤት ተላልፋል የተባለው የጡረታ መዋጮ እንዴት ይሆናል ? በጡረታ አበል ሊታሰብላቸው ይገባል አይገባም የሚለውን ጥያቄ በሕጉ የመወሰን ሥልጣን ያለው ራሱ የማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን እና በይግባኝ ደረጃ የሚያየው ይግባኝ ሰሚው ጉባዔ እንጅ ፍርድ ቤት አይደለም ፡፡
በሌላም በኩል የአሁኑ አመልካች በክርክሩ ላይ እንደገለፀው ይኼው ጉዳይ ቀደም ሲል ለማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን ቀርቦ እስከ ይግባኝ ሰሚው ጉባዔ ደርሶ ታይቶ ውሣኔ ከተሰጠበት እንደገና የሚታይበት የሕግ አግባብ የለም :: በሕጉ ይግባኝ ሰሚው ጉባዔ የሚሰጠው ውሣኔ የመጨረሻ በመሆኑ ያበቃለት ጉዳይ ይሆናል ።
በአጠቃላይ በዚህ ጉዳይ ፍርድ ቤት ሰሥረ ነገሩ ላይ የመዳኘት ሥልጣን የሌለው መሆኑ ተረጋግጧል ፡፡ በዚህ ረገድ የተሰጠው መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል ።
ው ሣ ኔ . * 1. ! ይህንን በማስመልከት የፌዴራል ፍ / ቤት
በፍ / ይ / መ / ቁ 2384 ታህሣሥ 15 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሣም - . ሆነ ጽርክሩን በመጀመሪያ ያየው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት
- የወሰነው በፍ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ .348 / 1 / መሠረት ተሽሯል ። 2. በክርክሩ ምክንያት የደረሰውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን
ይቻሉ ፡፡
3. የውጭው ግልባጭ ይተላለፍ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
You must login to view the entire document.