ሠላሳ አንደኛ ዓመት ቍጥር ፲፪
የ ኢ ት ዮ ጵ ያ ን ጉ ሠ ነ ገ ሥ ት መ ን ግ ሥ ት E
ነ ጋ ሪ ት ጋ ዜ ጣ ።
፡
የጋዜጣው ዋጋ
ባገር ውስጥ ባመት
በ፮ ወር ለውጭ አገር እጥፍ ይሆናል "
ማ ው ጫ ።
፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት
በጽሕፈት ሚኒስቴር ተጠባባቂነት የቆመ "
አዋጅ ቊጥር ፪፻፺፰ ፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
የአዲስ አበባ ከተማ የውሃና የፍሳሽ አገልግሎት ባለሥልጣን አዋጅ
ቊጥር ፪፻፺፰ ፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
የአዲስ አበባ ከተማ የውሃና የፍሳሽ አገልግሎት ባለሥ ልጣን ሥልጣኖችን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ፤
ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
ገጽ ፷፱
የአዲስ አበባ ከተማ የውሃና የፍሳሽ አገልግሎት ባለሥ ልጣን እንዲቋቋም ያዘዝን ስለሆነ ፤
ለዚህም ባለሥልጣን ዓላማዎቹን ከግቡ ለማድረስ የሚ ያስችሉትን ሥልጣኖች መስጠት ስለሚያስፈልግ ፤
በሕገ መንግሥታችን በ፴፬ኛውና በ፹፰ኛው አንቀጾች የተጻፈውን ተመልክተን የሕግ መምሪያና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቶቻችን የመከሩበትን ፈቅደን ቀጥሎ ያለውን አው ጀናል ።
፩- አጭር አርእስት ፤
ይህ አዋጅ « የ፲፱፻፷፬ ዓ. ም. የአዲስ አበባ ከተማ የው ሃና የፍሳሽ አገልግሎት ባለሥልጣን አዋጅ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ።
፪ ትርጉም ፤
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም ካልሰጠው በስተቀር በዚህ አዋጅ ፤
፩ « ባለሥልጣን » ማለት የአዲስ አበባ ከተማ የውሃና የፍሳሽ አገልግሎት ባለሥልጣን ነው ፤
፪ « ቦርድ » ማለት የባለሥልጣኑ የውሃና የፍሳሽ አገል ግሎት ቦርድ ነው ፤
፫ « የውሃ መሰብሰቢያ ሥፍራ » ማለት ውሃው በባለሥ ልጣኑ የአስተዳደር ክፍል ውስጥ ወደውሃ አገልግ ሎት ሥራዎች ውሃውን የሚሰበስብበት የየብስ ወይም የውሃ ቦታ ነው ።
አዲስ አበባ መጋቢት ፯ ቀን ፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
ቢንስ በወር አንድ ጊዜ ይታተ "
የፖስታ ሣጥን ቍጥር ፩ሺ | ፻፷፬ (1364)