×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁ 30/1990 የውሽውሽ ሻይ ልማትድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ የውሽውሽ ሻይ ልማት ድርጅትን ለማቋቋም ይ ) \ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፳፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲስ አበባ የካቲት ፲ ቀን ፲ህየ ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፲ ዓ • ም • የውሽውሽ ሻይ ልማት ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፭፻፴፬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፲ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻፲፫፯ አንቀጽ ፭ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፷፬ አንቀጽ ፵፯ / ፩ / / ሀ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የውሽውሽ ሻይ ልማት ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስ ትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፲ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . መቋቋም ፩ . የውሽውሽ ሻይ ልማት ድርጅት ( ከዚህ በኋላ “ ድርጅቱ ” እየተባለ የሚጠራ ) የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ያንዱ ዋጋ 2.30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ዝሺ፩ ገጽ ፮፻፲ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፩ የካቲት ፲ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ፪ . ድርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፳፬ መሠረት ይተዳደራል ። ፫ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በመንግሥት የሚሰየም አካል የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ይሆናል ። ፬ . ዋና መሥሪያ ቤት የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በውሽውሽ ይሆናል ። እንደአስፈላጊ ነቱም በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ፭ ዒላ ማ ድርጅቱ የተቋቋመባቸው ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው ። ፩ የሻይ ተክል ልማት ማካሄድ ፡ ፪ የሻይ ቅጠልን በመጀመሪያ ደረጃ ማዘጋጀት ፡ ፫ ዓላማዎቹን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ተዛማጅ ሥራዎችን ማካሄድ ። ፮ ካፒታል ለድርጅቱ የተፈቀደው ካፒታል ብር ፵፩ ሚሊዮን ፳፻፮ ሺህ ( አርባ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ስድስት ሺህ ብር ) ሲሆን ከዚህ ውስጥብር ፳ሚሊዮን ፯፻፶፪ ሺህ ፭፻፳፮ ( ሃያ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ ስድስት ብር ) በጥሬ ገንዘብና በዓይነት ተከፍሏል ። ፯ ኃላፊነት ድርጅቱ ካለው ጠቅላላ ንብረት በላይ በዕዳ ተጠያቂ አይሆንም ። ፰ ድርጅቱ የሚቆይበት ጊዜ ድርጅቱ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል ። ፀ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፲፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓ.ም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?