×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፫/፲፱፻፶፭ የዓሣ ሀብት ልማትና አጠቃቀም አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፴፪ አዲስ አበባ ጥር፳፯ ቀን ፲፱፻፶፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፫ / ፲፱፻፶፭ ዓም የዓሣ ሀብት ልማትና አጠቃቀም ገጽ ፪ሺ፳፫ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፭ / ፲፱፻፶፭ የዓሣ ሀብት ልማትና አጠቃቀም አዋጅ ኢትዮጵያ ለምግብናለኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚውል የዓሣ ሀብት ክምችት ያላት ሀገር በመሆኗ ይህ የሀገሪቱ የዓሣ ሀብት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲለማና በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ በማስፈለጉና ቀደም ሲል | for the development and rational utilization of this resource , የወጣ የዓሣሀብትሕግባለመኖሩናሀብቱን በዘላቂነት ለማልማትና ለመጠበቅ ሕግማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | such law does not exist so far ; መንግሥት አንቀጽ ፶፭ / ፩ / መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የዓሣ ሀብት ልማትና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር ፫፻፲፭ / ፲፱፻፶፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ጅ ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡ ፩ “ ዓሣ ” ማለት ማንኛውም የዓሣ ዝርያ፡ ሽርጠን፡ አስተኔ ( ክሩስተሺያን ) ፡ ጐል ለበስ ( መለስ ) ፡ እንዲሁም እነሱ የጣሉትን እንቁላል'የተፈለፈለ ወይም ታዳጊ ጫጩትን ያጠቃልላል፡ ጅ “ የዓሣ ሀብት ” ማለት በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ የውሃ አካላት ውስጥ የሚገኝ የዓሣ ክምችት ነው ፤ ያንዱዋጋ I ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ • ፰ሺ፩ ገጽ ፪ሺ፳፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፪ ጥር ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ • ም • ፫ . “ የዓሣ ግብርና ” ማለት ቁጥጥር በሚደረግበት ሁኔታ በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ የውሃ አካላት ዓሣን ማርባት እና ወይም ማምረትና ከዚህ ጋር የተያያዙ ሌሎች ሥራዎችንም የሚጨምር ነው ፣ “ የዓሣ ግብርና ተቋም ” ማለት የዓሣ ግብርና ሥራ የሚካሄድበት ማንኛውም የተወሰነ ቦታ ወይም አካባቢ ሲሆን ለግል መዝናኛነት የሚዘጋጀውን መርዕየ ገንዳን አይጨምርም ፣ ፭ “ ዓሣ ማስገር ” ማለት ማን ንም ዘዴ በመጠቀም ከማንኛውም የውሃ አካል ለተለያየ ዓላማ ዓሣ የመያዝ ፣ የመግደል ወይም የማውጣት ተግባር ነው ፣ ፮ “ ለግል ፍጆታ ዓሣ ማስገር ” ማለት ዓሣ አስጋሪው ለራሱና ለቤተሰቡ ፍጆታ ብቻ የሚያካሂደው የዓሣ ማስገር ሥቆ ነው ፣ ፯ “ ለንግድ ዓሣ ማስገር ” ማለት በሙሉ ወይም በከፊል ለመሸጥ ወይም ለመለወጥ ዓሣ ማስገር ነው ፣ ፰ “ ለመዝናኛ ዓሣ ማስገር ” ማለት ለመዝናኛ ተብሎ ልሙጥ የሆነ ነጠላ መንጠቆና የናይለን ክር በመጠቀም የሚካሄድ ዓሣ ማስገር ነው ፣ ፀ • “ ለምርምር ዓሣ ማስገር ” ማለት ለሳይንሳዊ ምርምር ለሙከራ ፣ ለሌሎች ጥናታዊ ሥራዎች ወይም ሥነ በማንኛውም የውሃ አካል ለመጨመር መያዝንና ለመርዕየ ገንዳና ለቤተመዘክር ዓሣ መሰብሰብን ይጨምራል ፣ ፲ . “ ሰው ” ማለት ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ድርጅት ነው ፤ ፲፩ “ ዓሣ አስጋሪ ” ማለት የዓሣ ማስገር ሥራ የሚያካሂድ ሰው ነው ፣ ፲፪ “ ጥብቅ የዓሣ ሀብት ክልል ” ማለት በማንኛውም የውሃ አካል ውስጥ የዓሣውን ዝርያ ለመጠበቅ ወይም ለሌላ ተግባር ሲባል በሙሉ ወይም በከፊል የተከለለና ለምርምር ካልሆነ በስተቀር ለማንኛውም የዓሣ ማስገር ሥራ የተከለከለ አካባቢ ነው ፣ ፲፫ . “ የዓሣ ማስገሪያ ጀልባ ” ማለት ለዓሣ ማስገር ሥራ ከብረት ፣ ከጣውላ ፣ ከእንጨት ፣ ከቀርክሃ ፣ ከደንገል ወይም ከመሳሰሉት የተሠራ ማንኛውም ትንሳፋፊ አካል ፣ ነው ፣ ፲፬ “ የዓሣ ማስገሪያ መሣሪያ ” ማለት ለዓሣ ማስገር ሥራ የሚያገለግል ማንኛውም መረብ ፣ ወጥመድ ፣ ወንፊት ፣ ነጠላ የናይለን ክር ፣ መንጠቆናእንዲሁም ሌላ ተመሣሣይ መሣሪያ ነው ፣ - ፲፭ “ ሚኒስቴር ” ወይም “ ሚኒስትር ” ማለት እንደቅደም ተከተሉ የግብርና ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው ፣ ፲፮ • “ ክልል ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፯ ( ፩ ) መሠረት የተመለከተ ማንኛውም የክልላዊ መስተዳድር ሲሆን ለዚህ ኣዋጅ አፈጻጸም የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደ ሮችንም ይጨምራል ፣ ፲፯ “ የዓሣ ሀብት ተቆጣጣሪ ” ማለት ይህን አዋጅና በአዋጁ መሠረት የሚወጡ ደንቦችንና መመሪያዎችን ካለባቸው ኃላፊነት አንፃር ለማስፈፀም እንደአግባቡ በሚኒስቴሩ ወይም በሚመለከተው የክልል ባለሥልጣን ሥልጣን የተሰጠው አግባብ ያለው ማንኛውም ሰው ነው ፣ የዚህ አዋጅ ዓላማዎች፡ ፩ የዓሣ ብዝሀ ሕይወትና አካባቢው እንዲጠበቅ ፣ ዓሣ ሀብቱ ከሚገባው በላይ እንዳይመረት መከላከልና መቆጣጠር ፣ ፪ ጥራቱና ንጽሕናው የተጠበቀ የዓሣ ምርት አቅርቦትን ማሳደግና ለምግብ ዋስትና የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ በዘላቂነት ማረጋገጥ እና ፣ የዓሣ ግብርና ልማትን ማስፋፋት ፣ ገጽ ፪ሺ፳፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፪ ጥር ፳፯ ቀን ፲፱፻፷፭ ዓም : ፬ . የአፈጻጸም ወሰን ይህ አዋጅ በኢትዮጵያ ውስጥ ዓሣ በሚረባባቸውና በሚመረ ትባቸው የውሃ አካላት ሁሉ ማለትም በሐይቆች ፣ በወንዞች ፣ በጅረቶች ፣ በግድቦች ፣ በኩሬዎችና በረግረጋማ ቦታዎች እንዲሁም የዓሣ ምርት ዝግጅትና ግብይት በሚካሄድባቸው ቦታዎች ተፈጻሚነት ይኖረዋል ። ክፍል ሁለት የዓሣ ሀብት አጠቃቀም ፭ ከተፈጥሮና ሰው ሠራሽ የውሃ አካላት የሚገኝ የዓሣ ሀብት ለንግድ ሥራ ከተፈጥሮ እና ከሰው ሠራሽ የውሃ አካላት ዓሣ ለማስገር የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ሕጋዊ የዓሣ ማስገር ፈቃድ መያዝ አለበት ። የዓሣ ማስገር ፈቃድን በማንኛውም መልኩ ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠት የተከለከለ ነው ። ማንኛውም ሰው ከብሔራዊ ዱር እንስሳት ፓርክ ወይም ጥብቅ ቦታ ለፍጆታ ፣ ለንግድ ወይም ለመዝናኛ ዓሣ ለማስገር ፓርኩን ለማስተዳደር ሥልጣን ከተሰጠው አካል የተሰጠ የፅሑፍ ፈቃድ መያዝ አለበት ። ፬ • ከጥብቅ የዓሣ ሀብት ክልል ለፍጆታ ፣ ለንግድ ወይም ለመዝናኛ ዓሣ ለማስገር የፈለገ ማንኛውም ሰው ከሚኒ ስቴሩ ወይም ከሚመለከተው የክልል ባለሥልጣን የፅሑፍ ፈቃድ ማግኘት አለበት ። ለመዝናኛ ዓሣ ለማስገር የሚፈልግ ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ እንደአግባቡ ከሚኒስቴሩ ወይም ከሚመለ ከተው የክልል ባለሥልጣን የፅሑፍ ፈቃድ ማግኘት አለበት ። ፮ : ማንኛውም ሰው ለፍጆታ ፣ ለንግድ ወይም ለመዝናኛ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ በተደነገገው መሠረት በኮንሴሽን ከተሰጠ የዓሣ ሀብት ዓሣ ለማስገር ኮንሴሽን ከተሰጠው ሰው ፈቃድ ማግኘት አለበት ። ለምርምርሥራካልሆነ በስተቀርሕጋዊከሆኑየማስገሪያ መሣሪያዎች ውጭ በፈንጂ ፣ በጦር መሣሪያ ፣ በመርዝ ፣ ዓሣውን በሚያደነዝዝ ዕፅ ወይም በኤሌክትሪክ ሞገድ ከማንኛውም የውኃ አካል ዓሣ ማስገርና እነዚህን ነገሮች በውሃ አካላት ላይና ዳርቻ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው ፣ ከማንኛውም የውሃ አካል ውሃውን በማጠንፈፍ ዓሣን ማስገር የተከለከለ ነው ። ፱ በሀገሪቱ የውኃ አካላት ለምርምር ዓሣ ማስገር የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የምርምር ሥራን ለመምራትእና እንደአ ስፈላጊነቱ ውሃን ለማስተዳደር ሥልጣን ከተሰጠው የፌዴራል ወይም የክልል መንግሥት አካል ፈቃድ ማግኘት አለበት ። ፲ ማንኛውም ሰው ከውጭ ሀገር ማንኛውንም ዓይነት ሕይወት ያለው የዓሣ ዝርያ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ወይም ከሀገር ለማስወጣት ፣ ከሚኒስቴሩ የጽሑፍ ፈቃድ ማግኘት አለበት ። ፲፩ . ማንኛውም ሰው ከውጭ ሀገር በፈቃድ ወደ ሀገር ውስጥ የገባውን ወይም በሀገር ውስጥ የሚገኝን ማንኛውም ሕይወት ያለው ዓሣ ከአንዱ ክልል የውሃ አካል ወደ ሌላ ክልል ለማዘዋወር ከሚኒስትሩ የጽሑፍ ፈቃድ ማግኘት አለበት ። ፲፪ ማንኛውም ሰው ሙሉ በሙሉ በክልሉ ውስጥ በሚገኙና ወደ ውጭ የመፍሰስ ባህርይ በሌላቸው የውሃ አካላት መካከል ካንዱ የውሃ አካል ወደ ሌላ የውሃ አካል የዓሣ ዝርያ ለማዘዋወር ከሚመለከተው የክልል ባለሥልጣን የጽሑፍ ፈቃድ ማግኘት አለበት ። ገጽ ፪ሺ፳፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፪ ጥር ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም : የዓሣ ግብርና ፩ . ማንኛውም ሰው ለንግድ የዓሣ ግብርና ተቋም ለማቋቋም ግብርና ለማካሄድ እንደአግባብነቱ ከፌዴራል ወይም ከክልል ባለሥልጣን ፈቃድ ማግኘት አለበት ። ለንግድ የዓሣ ግብርና ተቋም ለማቋቋም ወይም ለማካሄድ ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ፈቃድ የሚሰጠው፡ ሀ ) በቂ መሬት ያለውና ለሥራው የሚያስፈልገውን የውኃ መጠን ለመጠቀም ወይም ከመሬት ውስጥ ለማውጣት ወይም በተፈጥሮ የውሃ አካላት ላይ ለመጠቀም ካለው አካል የተሰጠው ፣ እና ለ ) የሚቋቋመው የዓሣ ግብርና ተቋም አካባቢን የማይ በክል ወይም በተፋሰሱ ባሉ የውሃ አካላት በሚገኙ የዓሣ ዝርያዎች ላይ ጉዳት የማያደርስ ፣ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው ። የዓሣ በሽታ ከዓሣ ግብርና ተቋም ወደ አካባቢው ወይም ተፋሰሱሊዛመት ይችላል ብሎ ሲያምን ሚኒስቴሩ ወይም አግባብ ያለው የክልል ባለሥልጣን አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ፣ የዓሣ ግብርናና የዓሣ ግብርናተቋም ግንባታና አጠቃቀም ደረጃዎችን በተመለከተ ሚኒስቴሩ እንደ አስፈላጊነቱ መመሪያ ያወጣል ። • የዓሣ ሀብትን በኮንሴሽን ስለመስጠት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወይም ክልላዊ መንግሥታት የኣንድ የውሃ አካል ዓሣ ሀብትን ለአንድ ወይም ለብዙ ሰዎች በኮንሴሽን የሚሰጡበትና የዓ ሀብቱ በዘላቂነት መልማቱን የሚቆጣጠሩበት ሕግ ማውጣት ይችላሉ ። ፰ አካባቢን ስለመጠበቅ በማናቸውም ተፋሰስ ለማካሄድ የሚታቀዱ የልማት ፕሮግራ ሞችና ፕሮጀክቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በተፋሰሱ በሚገኝ የዓሣ ሀብት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የማያደርሱ መሆናቸውን በሚመለከተው የፌዴራል ወይም የክልል መንግሥት አካል መረጋገጥ አለበት ። ወሰን እና ክልል ተሻጋሪ የዓሣ ሀብት ልማት ፩ : ወሰን ተሻጋሪ የዓሣ ሀብት ልማትን በተመለከተ ሚኒስቴሩከሚመለከታቸው ጐረቤት ሀገሮች ጋርመደራ ደርና ስምምነት ማድረግ ይችላል ፣ ፪ • እያንዳንዱ ክልል ከሌሎች ክልሎች ጋር በሚያዋስኑ የውሃ አካላት ውስጥ የሚገኝ የዓሣ ሀብት በዚህ አዋጅ በተደነገጉት መርሆዎች መሠረት መጠበቁን ለማረጋገጥ መተባበር ይኖርበታል ፣ ፫ ክልሎችን በሚያዋስኑ የውሃ አካላትየሚገኝ የዓሣ ሀብት በሚመለከታቸው ክልሎች መካከል ሀብቱን በጋራ ለማልማት በሚደረግ ስምምነት መሠረት አለመካሄዱ ሲረጋገጥ የዓሣ ሀብቱን በአግባቡ ለማልማት የሚያ ስችልደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊያወጣ ይችላል ። ፲ የዓሣ ምርት አያያዝ የዓሣና የዓሣ ውጤት አያያዝ ፣ ዝግጅት ፣ ክምችት ፣ ማጓጓዝና ንግድ ሥራዎች ተገቢውን የጥራትና የንግድ ደረጃዎችንና ሥርዓቶችን የጠበቀ መሆን አለበት ። ዝርዝሩም በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ። ገጽ ፪ሺ፳፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፪ ጥር ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ፲፩ የዓሣ ሀብት መረጃ ልውውጥ ለዚህ አዋጅ አፈፃፀም እንዲረዳ ክልላዊ መስተዳድሮች የዓሣ ሀብት መረጃዎችን በመሰብሰብና በማጠናቀር ለሚኒስቴሩ ይልካሉ፡ ፪ ሚኒስቴሩ ከተለያዩ ምንጮች ስለ ዓሣ ሀብት የሚሰበስባ ቸውን መረጃዎችና የምርምር ውጤቶች በመገምገምና በማዘጋጀት ለክልል መስተዳድሮችና ለሌሎች ተጠቃ ሚዎች እንዲደርሱ ያደርጋል ፣ ፲፪ • የዓሣ ሀብት ልማት እና አጠቃቀም ሕግ መሠረታዊ ጉዳዮች በዚህ አዋጅ መሠረት የሚወጣ ማንኛውም የዓሣ ሀብት ሕግ ጥብቅ የዓሣ ሀብት ክልልን ፣ ዓመታዊ የዓሣ ምርት መጠንን ፣ የማስገሪያ መሣሪያ ዓይነትንና ብዛትን ፣ የማስገሪያ ወቅትን ፣ የማስገር ፈቃድ አሰጣጥን ፣ እድሳትንና እገዳን ፣ የዓሣ ዝውውርን ፣ የዓሣ ግብርናን ፣ የዓሣ ንግድን ፣ የዓሣ ውጤቶች ጥራትና የንጽሕና ደረጃን ፣ የተከለከሉ ተግባሮችን ፣ የኅብረ ተሰብ ተሳትፎን ፣ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማንና ሌሎች ተጓዳኝ ጉዳዮችን በግልጽ ያስቀመጠ መሆን አለበት ። ክፍል ሦስት አዋጁን ስለማስፈጸም ፲፫ የዓሣ ሀብት ተቆጣጣሪ ሥልጣንና ኃላፊነት ይህን አዋጅና በአዋጁ መሠረት የሚወጡደንቦችንና መመሪያ ዎችን ተግባራዊነት ለማረጋገጥ የዓሣ ሀብት ተቆጣጣሪ ሥልጣን የተሰጠው መሆኑን የሚገልጽ መታወቂያ በማሳየት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ፤ ሀ ) በማንኛውም የውኃ አካል ላይ የሚገኝ ዓሣ አስጋሪን አስቁሞ መፈተሽ ጀልባውን ወይም የማስገሪያ መሳሪ ያውን መመርመር ለ ) ይህን አዋጅና በዚህ አዋጅ መሠረት የሚወጡትን ደንቦችና መመሪያዎች ጥሷል ተብሎ አጥጋቢ በሆነ ሁኔታ የተጠረጠረ ማንኛውንም ሰው ስሙንና አድራ ሻውን እንዲነግር፡ መታወቂያውንና ሌሎች ከዚህ ጋር አግባብነት ያላቸውን መረጃዎች እንዲያሳየው ወይም እንደአስፈላጊነቱ እንዲሰጠው መጠየቅ፡ ሐ ) ማንኛውም ዓሣ የተያዘው፡ የተጓጓዘው ፥ ለገበያ የቀረበውሃ ወደ ሀገርእንዲገባ የተደረገው ወይም ከሀገር እንዲወጣ የተዘጋጀው ይህን አዋጅ በመጣስ ነው ብሎ አጥጋቢ በሆነ ምክንያት ሲያምን ዓሣውን መያዝ፡ መ ) ማንኛውም የዓሣ ማስገሪያ ጀልባና መሣሪያ ይህን አዋጅ እና በዚህ አዋጅ መሠረት የሚወጡትን ደንቦችና መመሪያዎች በተፃረረ ሁኔታ ጥቅም ላይ መዋሉን አጥጋቢ በሆነ ሁኔታ ሲያረጋግጥ እነዚህን መሣሪያዎች መያዝ ሠ ) ማንኛውንም ሰው ይህን አዋጅ በመተላለፍ ወንጀል ፈጽሟል ብሎአጥጋቢ በሆነ ምክንያት ሲያምን በተቻለ ፍጥነት ሥልጣን ባለው አካል ክስ እንዲመሠረት ማድረግ፡ ረ ) ማንኛውም ዓሣ መታመሙን ፡ መበከሉን ወይም መበላ ሽቱን አጥጋቢ በሆነ መንገድ ሲያረጋግጥ ዓሣው እንዲ ወገድ ወይም ጉዳት እንዳያደርስ ማድረግ ሰ ) ማንኛውንም ዓሣ አስጋሪ ስለተጠቀመበት ማስገሪያ መሣሪያ፡ ስለያዘው ዓሣ ዓይነትና መጠን ' እንዲሁም ዓሣውን ያሰገረበትን አካባቢ መረጃ እንዲሰጠው መጠየቅ፡ ሸ ) ማንኛውንም የዓሣ ግብርና የዓሣ ማደራጃ፡ ማከማቻ ማጓጓዣና መሸጫ ተቋማትንና መሳሪያዎችን መፈተሽና ተፈላጊውን ደረጃ አሟልተው በማይገኙበት ጊዜ ማሸግ ወይም ማገድ፡ ይችላል ። ዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሠረት ይቃወመ ገጽ ፪ሺ፳፰ ፈዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፪ ጥር ፳፯ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም : ፲፬ • የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ሰው የዓሣ ሀብት ተቆጣጣሪ ለሥራው የሚፈልጋ ቸውን መረጃዎች በመስጠት የመተባበር ግዴታ አለበት ። ፲፭ ስለተያዘ ዓሣ የማስገሪያ መሳሪያና ሌሎች ዕቃዎች ፩ . የዓሣ ሀብት ተቆጣጣሪ ፤ ሀ ) በዚህ አዋጅ መሠረት የተያዘና ለገበያ መቅረብ የሚችል ማንኛውንም ዓሣ እንዳይበላሽ ለመከ ላከል ዓሣው የተያዘበት ሰው ባለበት በህጋዊ መንገድ እንዲሸጥ ያደርጋል ፤ ለ ) በዚህ አዋጅ መሠረት የተያዘ የማስገሪያ መሳሪያን ወይም የማጓጓዣና ሌሎች እቃዎችን ፍርድ እስኪ ሰጥባቸው ድረስ በጥንቃቄ እንዲቆዩ ማድረግ ይኖርበታል ሐ ) የተያዘ ዓሣ የማስገሪያ መሣሪያ ወይም ሌላ እቃ ዓይነትና መጠን የተያዘበትንና ዓሣው የተሸጠ በትን ወይም የተወገደበትን ቀን እንዲሁም ከሽያጭ የተገኘውን ገንዘብ መጠን የሚገልጽ ህጋዊ ደረሰኝ ለተያዘበት ሰው ይሰጣል ። ፪ . በዚህ አዋጅ መሠረት ዓሣ የተያዘበት ሰው በወንጀል የመጠየቁ ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ፡ ከዓሣ ሽያጭ የተገኘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል ። ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፮ ወንጀልና ቅጣት ማንኛውም ሰው ፩ . ያለፈቃድ ወይምከተሰጠው ፈቃድተቃራኒ በሆነ ሁኔታ ሕይወት ያለው ዓሣ ከውጭ ሀገር ካስገባ በኢትዮጵያ የውኃ ኣካላት ከጨመረ ከሀገር ካስወጣ ወይም ከአንድ የውኃአካል ወደ ሌላ የውኃ አካል ካዛወረከአንድ ዓመት በማያንስና ከሶስት ዓመት በማይበልጥ እስራት ወይም እስከ ብር ፲ሺ በሚደርስ መቀጮ ወይም በሁለቱም ይቀጣል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ላይ ከተጠቀሰው ወንጀል ውጪ ይህን ኣዋጅና በዚህ አዋጅ መሠረት የሚወጡ ደንቦችንና መመሪያዎችን ከተላለፈ በኢት ፲፯ ሌሎች እርምጃዎች ፩ . ማንኛውም ሰው ይህን አዋጅ በመተላለፍ ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ ጥፋተኛነቱ ሲረጋገጥ በተከሣሹ ላይ ከሚሰጠውማንኛውም ዓይነት ቅጣት በተጨማሪ ፍርድ ሀ ) ለወንጀል ተግባር የዋሉትን ማናቸውንም የዓሣ ማስገሪያ ጀልባና የዓሣ ማስገሪያ መሣሪያ እንዲ ለ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ የዓሣ ማስገር ሥራ ለማካሄድየዋለንማናቸውንም መርዝ ወይም ፈንጂ ወይም ሌላ ዓይነት መሣሪያ እንዲወረስ ሐ ) የዓሣ ማስገር ሥራው ወይም የንግድ ፈቃዱ እንዲታገድ፡እንዲሰረዝ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል ። ፪ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የተያዙት ዕቃዎች እንዲወረሱ ትዕዛዝ ካልተሰጠ በስተቀር ውሳኔው በተሰጠ በ፴ ቀናት ውስጥ የገንዘብ ቅጣቱ ካልተከፈለ የተያዙት ዕቃዎች ተሽጠው ከሽያጩ በሚገኘው ገንዘብ የገንዘብ ቅጣቱ እንዲሸፈን ይደረጋል ። ፫ የወንጀል ክስ ከተመሠረተ በኋላ ተከሳሹ በነጻ ቢለቀቅ የተያዘው የማስገሪያ መሳሪያ ወይም ሌላ እቃ ለተከሣሹ ይመለሳል ። የተያዘው ዓሣ ከሆነ ግን ዓሣው የተሸጠበት ዋጋ ለግለሰቡ ተመላሽ ይሆናል ። አልደጊዮርጊስ ገጽ ፪ሺ፳፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፪ ጥር ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም : ፲፰ ወንጀል እንደተፈጸመ የሚያስቆጥሩ ሁኔታዎች ፩ . ማንኛውም ሰው አግባብነት በሌለው ሁኔታ በኢትዮጵያ የውኃ አካላት ወይም ዳርቻ ላይ ፈንጂ፡ የጦር መሣሪያ የኤሌክትሪክ ንዝረት የሚሰጥ መሳሪያ፡ መርዝ ወይም ዓሣን የሚያደነዝዝ ዕፅ ይዞ ቢገኝ የዚህን አዋጅ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀፅ ( ፯ ) ድንጋጌ በመተላለፍ ሕገ ወጥ ድርጊት እንደፈጸመ ይቆጠራል ። ፪ . ማንኛውም ሰው ፈቃድ ሳይኖረው ሕይወት ያለው ዓሣ ሲያዘዋውር ቢገኝ የዚህን አዋጅ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፬ ) ( ፲፩ ) እና ( ፲፪ ) ድንጋጌዎች በመተላለፍ በሕገ ወጥ ሥራ ላይ እንደተሰማራ ይቆጠራል ። ፲፱ • ከሌሎች ሕጐች ጋር ስላለው ግንኙነት ይህን አዋጅ የሚቃረን ማንኛውም አዋጅ ደንብ ፣ መመሪያና ልምድ በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። አዋጁን ለማስፈጸም የሚረዱ ሕጎችን ስለማውጣት ይህን አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲረዳ ፩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ፡ ፪ ክልሎች የየራሳቸውን ሕግ ፫ : ሚኒስቴሩ መመሪያ ሊያወጡ ይችላሉ ። ፳፩ . አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ቁጥር ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥር ፳፯ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?