የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አንደኛ ዓመት ቁጥር ፲፪ አዲስ አበባ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፳፯ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፲፪ / ፲፱፻ዥ፯ ዓ . ም የስፖርት ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ . . . . . . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፳፩ ኣዋጅ ቁጥር ፲፪ / ፲፱፻ጡ ፤ የስፖርት ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የስፖርት ኮሚሽንን ማቋቋም በማስፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የስፖርት ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፲፪ | 1 . Short Title ፲፱፻m፯ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይቻላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፡ ፩ . “ የኢትዮጵያ ኦሎምፒያዊ ኮሚቴ ” ማለት በኢንተርና ሽናል ኦሎምፒክ ኮሚቴ ደንብ መሠረት በስፖርት ፌዴሬ ሽኖች የተቋቋመ ኮሚቴ ነው ፤ ፪ . “ ስፖርት ” ማለት ኣካል ማሠልጠኛንም ይጨምራል ! | ፫ . “ የስፖርት ማኅበር ” ማለት በዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች | መሠረት የተቋቋመ የስፖርት ክበብ ፡ የኢትዮጵያ ኦሎም | ፒያዊ ኮሚቴ ወይም የስፖርት ፌዴሬሽን ነው ፤ ፬ . “ የስፖርት ፌዴሬሽን ” ማለት በሀገሪቱ ውስጥ አንድን ስፖርት ለማስፋፋትና ለመምራት ኃላፊነት የተጣለበት ተቋም ነው ። ያንዱ ዋጋ ) ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ . ፱ሺ፩ ገጽ ፳፪ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፳፯ ዓም _ ፫ መቋቋም ፩• የስፖርት ኮሚሽን ( ከዚህ በኋላ “ ኮሚሽኑ ” ተብሎ የሚጠራ ) | ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ ኣዋጅ ተቋቁሟል ። ፪• ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ይሆናል ። ፬ ዋና መሥሪያ ቤት የኮሚሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ይሆናል ። ፭ የኮሚሽኑ ዓላማ የኮሚሽኑ ዓላማ ስፖርት በኅብረተሰቡ ውስጥ እንዲደራጅ | 5 . Objective እንዲስፋፋና ሰፊ ሕዝባዊ ተሣትፎ እንዲኖረው ማድረግ ነው ። ፮ . የኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባር ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩• የሀገሪቱን የስፖርት ፖሊሲ ያዘጋጃል ፡ ሲፈቀድም ተግባራዊ | መሆኑን ይከታተላል ፣ ፪• የስፖርት ማኅበራት ስለሚቋቋሙበትና ደረጃቸው ስለሚወሰ ንበት ሁኔታ መመሪያ ያወጣል ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚቋቋሙት የስፖርት ማኅበሮች ፈቃድ ይሰጣል ፡ ፕሮግራ | ሞቻቸውንና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶቻቸውን ያስተባብራል ፡ ይቆጣጠራል ፣ ፫ ሀገር አቀፍና ኢንተርናሽናል የስፖርት ውድድሮችን ያዘጋጃል ፡ እንዲዘጋጁም ፈቃድ ይሰጣል ፡ የኢትዮጵያ | አጠቃላይ ጨዋታዎችን ከኢትዮጵያ ኦሎምፒያዊ ኮሚቴ ጋር በመተባበር ያዘጋጃል ፤ ፬• ብሔራዊ የስፖርት ቡድኖች አባላት በእንክብካቤ እንዲያዙና በሚገባ እንዲሠለጥኑ ያደርጋል ፤ ፭ አገር አቀፍ የስፖርት ውድድሮችን በሚመለከት በስፖርት ማኅበሮች መካከል የሚነሳውን ክርክሮች ይዳኛል ፤ ፮ አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የስፖርት ትጥቅና መሣሪያ በሀገር ውስጥ እንዲመረት ያበረታታል ፡ ከውጭ የሚገቡበትንም ሁኔታ ያመቻቻል ፤ ፯ ባህላዊ ስፖርቶች የበለጠ እንዲታወቁ ፡ እንዲሻሻሉና እንዲያድጉ ይረዳል ፤ ቿ የኣገር አቀፍ ስፖርት ማኅበሮች ገቢ ለዓላማቸው ብቻ መዋሉን ለማረጋገጥ ሂሣባቸውን ይመረምራል ፤ ፱ በአገር አቀፍና በኢንተርናሽናል ደረጃ የሚያገለግሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ያዘጋጃል ፡ በክልሎች ለሚዘጋጁ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል ፤ ፲ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ስፖርታዊ | ሕክምናን ያደራጃል ፡ በክልሎች ለሚደረጉ ዝግጅቶችም ድጋፍ ይሰጣል ፤ ፲፩ የንብረት ባለቤት ይሆናል ፡ ውል ይዋዋላል ፡ በራሱ ስም ይከሳል ፡ ይከሰሳል ፤ ፲፪• ዓላማውን ለማስፈጸም የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን ያከና ቪ• የኮሚሽኑ አቋም ፩ . የፌዴራል የስፖርት ምክር ቤት ( ከዚህ በኋላ “ ምክር ቤቱ ” እየተባለ የሚጠራ ) ፤ ፪• በመንግሥት የሚሾም አንድ ኮሚሽነር እና አንድ ምክትል | 1 ) a Federal Sports Council ( hereinafter “ the Council ” ) : ኮሚሽነር ፤ እና ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ፤ ይኖሩታል ። ፰ የምክር ቤቱ አባሎች ምክር ቤቱ የሚከተሉት አባሎች ይኖሩታል ፤ ገጽ ፫ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻ዥ፯ ዓም _ Negarit Gazeta No . 12 - 24 August 1995 – Page 83 ፩ በመንግሥት የሚሰየም ተወካይ • የክልሎችና የአዲስ ኣበባ ስፖርት ምክር ቤቶች ተወካዮች . . . . . . . . . . አባሎች ፫• የኢትዮጵያ ኦሎምፒያዊ ኮሚቴ ሊቀ መንበር . . . . . . አባል ፬ . የእያንዳንዱ ብሔራዊ ስፖርት ፌዴሬሽን ሊቀ ፭ በመንግሥት የሚሰየሙ ለሥራው አግባብ ያላቸው ሌሎች መንግሥታዊ ወይም ሕዝባዊ ድርጅቶች ተወካዮች ፮• ኮሚሽነሩ አባል ፱ የምክር ቤቱ ስብሰባ ፩ ምክር ቤቱ በዓመት አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል ። ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል ። ፪• ከምክር ቤቱ አባላት አብዛኞቹ በስብሰባው ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይኖራል ። ፫• የምክር ቤቱ ውሣኔዎች በድምጽ ብልጫ ያልፋሉ ። ሆኖም ድምጽ እኩል በእኩል የተከፈለእንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ፬ . የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፤ ምክር ቤቱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲ የምክር ቤቱ ሥልጣንና ተግባር ምክር ቤቱ የሚከተለው ሥልጣንና ተግባር ይኖረዋል ፤ ፩ ስፖርት ስለሚስፋፋበትና ስለሚዳብርበት ሁኔታ ይመክራል ፡ ሃሣብ ያቀርባል ። ፪• ለመንግሥት የሚቀርቡ የፖሊሲ ውሣኔዎችንና የረጅም ጊዜ እቅዶችን ያጸድቃል ። ፫ ኮሚሽኑ የሚያወጣቸውን መመሪያዎች ያፀድቃል ። ፬ . የኮሚሽኑን የሥራ ሪፖርት ይገመግማል ። ፲፩ : ስለኮሚሽነሩ ሥልጣንና ተግባር ፩• ኮሚሽነሩ የኮሚሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን የኮሚ ሽኑን ሥራዎች ይመራል ፡ ያስተዳድራል ። ፪ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽነሩ ፡ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ የተመለከተውን የኮሚሽኑን ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) በፌዴራል የሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት የኮሚሽኑን ሠራተኞች ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፤ ሐ ) የኮሚሽኑን የሥራ ፕሮግራምና በጀት ያዘጋጃል ፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ መ ) ለኮሚሽኑ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጭ ያደርጋል ፤ ሠ ) ኮሚሽኑ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነትቶች ሁሉ ኮሚሽኑን ይወክላል ፤ ረ ) ስለኮሚሽኑ የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ያቀርባል ። ፫ ኮሚሽነሩ ለኮሚሽኑ የሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለባለሥልጣኑ ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ገጽ ፳፬ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፫፯ ዓም _ Negarit Gazeta No . 12 - 24 August 1995 – Page 84 ፲፪• በጀት የኮሚሽኑ በጀት በመንግሥት ይመደባል ። ፲፫• የሂሳብ መዛግብት ፩ ኮሚሽኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ የኮሚሽኑ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይምእርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲፬ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻ዥ፯ ዓ . ም . ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻ዥ፯ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ