ዓለጥ ፍ ር ድ
የሰበር መ / ቁ 18419
ግንቦት 4/1998 ዳኞች ፦ 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
ዓብዱልቃድር መሐመድ ጌታቸው ምህረቱ መስፍን እቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ አመልካች ፦ ሐመረወርቅ ቅ / ማርያም ቤ / ክርስቲያን ሰበካ ጉባዔ ጽ / ቤት መልስ ሰጭዎች ፦ 1. ዲያቆን ምህረት ብርሃን
2. አጋፋሪ አብርሃም ታደሰ 3. ዲያቆን አስራት ወ / ትንሣይ 4. ዲያቆን ገዛኸኝ ከበደ 5. ዲያቆን ስመኘው ግርማይ 6. ዲያቆን
ጉዳዩ ለዚህ ችሉት የቀረበው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት መ / ሰጭዎች
በአመልካች ቤተክርስቲያን ውስጥ መንፈሣዊ አገልግሉት ተቀጥረን ስናገለግል ከቆየን በኋላ
አመልካች ሕገወጥ በሆነ መንገድ ከስራ ያሰናበተን በመሆኑ ወደ ስራ እንድንመለስ
ይወሰንልን በሚል ባቀረቡት ክስ የአዋጅ ቁ 42/85 ድንጋጌዎችን ተፈፃሚ በማድረግ
ስንብቱ ሕገወጥ ነው በማለት መ / ሰጭዎች ወደስራ እንዲመለሱ የሰጠውና የፌዴራል
ከፍተኛ ፍ / ቤት ያፀናው ውሣ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል አመልካች
የሰበር አቤቱታ በማቅረቡ ነው :: ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ በተሰጠው ትእዛዝ
መሠረት መ / ሰጭዎች የአመልካች አቤቱታ ደርሷቸው መልስ የሰጡ ሲሆን አመልካችም
የመልስ መልስ እንዲያቀርብ ተደርጓል ፡፡
እንደሚሆን ይ ኣል ፡፡ የኃይማኖት ተቋማት መንፈሣዊ ተግባር ከሚያከናውኑ ሰራተኞች
ግንኙነት አና . በጉዳዩ በዚህ ችሎት መታየት ያለበት የሕግ ነጥብ በአዋጅ ቁ .42 / 85 አንቀጽ 3 ( 3 ) ( ለ ) መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊያወጣው የሚችለው ደንብ የኃይማኖት ተቋማት መንፈሣዊ አገልግሎት ከሚሰጡ ሰራተኞቻቸው ጋር ያላቸውን የስራ ግንኙነቶችም ሊጨምር ይችላል ? ወይስ አይችልም ? የሚለው በመሆኑ ችሉቱም ነጥቡን መርምሯል ፡፡ አዋጅ ቁ .42 / 85 በአዋጅ ቁጥር 377/96 የተሻረ ቢሆንም ነጥቡን በሚመለከት ሁለቱ አዋጆች አንድ ዓይነት ድንጋጌዎች የያዙ በመሆኑ ችሎቱ የአዋጅ ቁ 42/85 ድንጋጌዎች መሠረት አድርጎ በተጠቀሰው ነጥብ ላይ የሚሰጠው የሕግ ትርጉም ለአዋጅ ቁ . 377/96 ድንጋጌዎችም አግባብነት ያለው ነው ::
ይህ ችሎት በዚህ ጉዳይ የሕግ ትርጉም ለሚሰጥበት ከላይ ለተመለከተው ነጥብ ቀጥተኛ አግባብነት ያለው የአዋጅ ቁ 42/85 አንቀጽ 3 ነው ፡፡ ይኸው አንቀጽ አወጁ በንዑስ አንቀጽ 2 ከተመለከቱት በቅጥር ላይ ከተመሠረቱት የስራ ግንኙነቶች ውጭ በሰራተኛና በአሰሪ መካከል በሚደረግ በቅጥር ላይ በተመሠረተ የስራ ግንኙነት ላይ ተፈፃሚ
ተፈፃሚ አንደማይሆንባቸው በአንቀጽ 3 ( 2 )
ከተዘረዘሩት የስራ ግንኙነቶች
ያልተካተተ ሲሆን ይልቁንም የአዋጁ አንቀጽ
3 ( 3 ) ( ለ ) የኃይማኖት ወይም የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በሚመሠርቱት የስራ ግንኙነቶች
ላይ አዋጁ ተፈፃሚ እንዳይሆን የሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብ ሊወስን ይችላል በሚል
ይደነግጋል ፡፡ የስር ፍ / ቤት ጉዳዩን በአዋጅ ቁ 42/85 መሠረት ለማየት ውጭ የሰጠው
በአንቀጽ 3 ( 3 ) ( ለ ) መሠረት የተጠቀሱት ድርጅቶች በሚመሠረቱት የስራ ግንኙነት አዋጁ
እንዳይሆን
የሚኒስትሮች
እስካላወጣ
ድርጅቶቹ
በሚመሠረቱት የስራ ግንኙነቶች ላይም አዋጁ ተፈፃሚ ይሆናል በሚል ነው :: ይህም በስር
ፍ / ቤት ለአንቀጽ 3 ( 3 ) ( ለ ) የተሰጠው ትርጓሜ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኃይማኖት
ድርጅቶች መንፈሣዊ አገልግሎት ከሚሰጡ ሰራተኞቻቸው ጋር ባላቸው የስራ ግንኙነቶች
ላይ የአዋጅ ቁ 42/85 ተፈፃሚ እንዳይሆን በደንብ ሊወስን ይችላል የሚል ድምዳሜን
መሠረት ያደረገ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል ፡፡ ይህ አተረጓጎም የሕጉን መንፈስ ተከትሉ
j ቀን /
የተሰጠ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የሚሸፍናቸውን የስራ
ግንኙነት ጉዳዮች መመልከት የግድ ይላል ፡፡
የአሰሪና
ሰራተኛ አዋጅ
ስለሚመሰረትበት ሁኔታ የስራ
ስለሚቆይበት
የሰራተኛውና
የአሰሪው
ግንኙነት
ስለሚቋረጥባቸው
ውስን ሁኔታዎች ፣ የስራ ውሉ ሕጋዊ ወይም ሕገወጥ በሆነ መንገድ
በሚቋረጥበት ጊዜ ስለሚከተሉ ውጤቶች የሚደነግጉ ድንጋጌዎች የያዘ ሆኖ ይታያል ።
በአጠቃላይ ሕጉ ከአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን በአንዳንድ
ሁኔታዎች ከሚያጋጥሙ ልዩ ጉዳዮች በቀር አካቶ የያዘ መሆኑን መረዳት ይችላል ፡፡
ከላይ የተመለከቱት ከአሠሪና ሠራተኛ ግነኙነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ነጥቦች
መንፈሣዊ
አገልግሎትን
በሚመለከት የኃይማኖት ተቋማት በሚመሠርቷቸው
ግንኙነቶች ውስጥም የሚነሱ ቢሆንም በሌሎች የስራ ግንኙነቶች ከሚያጋጥሙበት አኳኋን
ለየት ባለ መንገድ የሚያጋጥሙ ሁኔታዎችም አሉ ። ምክንያቱም በአንድ የኃይማኖት ተቋም
ውስጥ ሊመሠረት
የሚችል የተለያየ የሥራ ግንኙነት በመኖሩ ነው ። በአንድ በኩል
የሚሠጡት አገልግሎት ድርጅቱ ከሚከተለው እምነት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለውና
ከእምነቱ ጋር ተነጥሎ ሊታይ የማይችል ሠራተኛን ፤ እንደ ቄስ ፣ ካህን ፣ ዲያቆን ወዘተ ያሉ
ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የሚሠጡት አገልግሎት ከእምነቱ ጋር ያልተቆራኘ እንደ ሂሣብ
ሠራተኛ የንብረት ክፍል ሠራተኛ የስታትስቲክስ ሠራተኛ ወዘተ አሉ ። በመሆኑም
የሃይማኖት ሥራውን ከሚሠሩት ሠራተኞች ጋር የሚነሣው የአሠሪና ሠራተኛ ሁኔታ
ከሌሉቹ ሠራተኞች ጋር ከሚነሣው የተለየ ነው :: ቀጥተኛ የሃይማኖቱን ወይም መንፈሣዊ
ስራ የሚሠሩትን ሠራተኞች ስንመለከት የስራቸው ፀባይ የኃይማኖት ተቋሙ ከሚከተለው
እምነት የሚመነጭና ከእምነቱ ጋር ጥብቅ ትስስር ያለው በመሆኑ መንፈሣዊ አገልግሎቱን
ለመስጠት ብቁ ሆኖ ለመገኘት መሟላት የሚገባቸው ነገሮች ለምን ያህል ጊዜ አገልግሎቱ
ላይ መቆየት እንደሚችል የኃይማኖቹ እና የመንፈሣዊ አገልግሎት ሠጪው መብትና ግዴታ
አገልጋዩ መንፈሣዊ አገልግሉቱን እየሠጠ እንዲቀጥል የሚያደርጉ ሁኔታዎች አገልጋዩ
አግባብ ባልሆነ መንገድ አገልግሎቱን እንዳይሠጥ በተደረገ ጊዜ የሚከተሉት ሁኔታዎች እና ሌሎች
ፌ , i ..
ችል “ ፊንጭ
ታ ! - 9
3 ( 3 ) ( ለ ) መሠረት ሊያወጣ የሚችለው
3 ር የሚያደርጉትን ግንኙነቶች የሚጨምር ሊሆን
በስራ ግንኙነቱ ሊነሱ የሚችሉ ጉዳዮች እያንዳንዱ የኃይማኖት ተቋም ከሚከተለው እምነት ጋር
የተያያዙ ናቸው ። የመንፈሣዳዊ ስራ ግንኙነቱ የሚያስነሣቸው የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳዮች ከእምነቱ
ተነጥለው የሚታዩ ባለመሆናቸው በስራ ግንኙቱ ውስጥ ጣልቃ መግባቱ በእምነት ውስጥ ጣልቃ
መግባትን ያስከትላል ፡፡
በሌላ በኩል ግን ከእምነቱ ጋር ተያያዥነት ያለውን ሥራ የሚሠሩ ሠራተኞች ከድርጅቱ
ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት ሊያስነሣ የሚችለው ጉዳዩ ከእምነቱ ጋር የማይያያዝና ይልቁንም
በማንኛውም የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ከሚነሱ ሁኔታዎች የተለየ አይደለም ፡፡
ከላይ እንደተመለከተው የመንፈሣዊ የስራ ግንኙነቱ የሚያስነሣቸው ሁኔታዎች ከኃይማኖቱ
ተነጣጥለው ሊታዩ የማይችሉ በመሆናቸው የሥር ፍ / ቤት ለተጠቀሰው አንቀፅ በሰጠው ትርጉም
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመንፈሣዊ ስራ ግንኙነትን በሚመለከት ሕግ የሚያወጣ ከሆነ በኃይማኖት
ጉዳዮችም ጣልቃ መግባቱ ይሆናል ይህ ደግሞ የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀት 11 " መንግሥትና
ኃይማኖት የተለያዩ ናቸው ፤ መንግሥት በኃይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ አይገባም " በማለት ከተደነገገው
ጋር የሚጋጭ ይሆናል ፡፡ ነገር ግን የሃይማኖቱን ሥራ ከሚሠሩት ሠራተኞች ውጪ ያሉና በሃይማኖት
ተቋም ከሚሰሩ ሰራተኞች ጋር ያለው የሥራ ግንኙነት የሚያስነሳው ጉዳይ ሌላው የአሠሪና ሠራተኛ
ግንኙነት ከሚያስነሳው ጋር ተመሣሣይ በመሆኑ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢቁ .42 / 85 አንቀጽ
እነዚህን ሠራተኛን በተመለከተ እንጂ መንፈሣዊ
አገልግሎት ለመስጠት ከኃይማኖት ተቋማት
አይችልም ፡፡
በመሆኑም ደንቡ እስካልወጣ ድረስ የአዋጅ ቁጥር 42/85 በመንፈሣዊ የሥራ ግንኙነቶች
ላይም ተፈፃሚ ይሆናል የሚለው ትርጉም የሕግ መሠረት የሌለው ይሆናል ፡፡
ከፍ ሲል በተዘረዘሩት ምክንያቶችም ማንኛውም የሥራ ክርክር ሰሚ አካላት መንፈሣዊ
የሥራ ግንኙነቶች ተመስርቶ የሚነሱ ክርክሮች በአ / ቁ 42/85 መሠረት አይቶ ለመወሰን
ሥልጣን የሌላቸው ሲሆን ክርክሮቹ የኃይማኖት ተቋማቱ በሚኖራቸው አለመግባባቶች በሚፈቱበት
መንገድ የሚታዩ ናቸው ። ይህ ችሉትም የስር ፍ / ቤት በዚህ ጉዳይ በታየው የሕግ ነጥብ የሰጠው
የሕግ ትርጉም መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝቶታል ፡፡
ው ሣ ኔ
1 / የፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት በመ / ቁ 13549 ህዳር 24 ቀን 1997 የሰጠው ውሣና
የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ 35562 ጥር 17 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ተሽሯል ፡፡
2 / ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራቸውን የየራሣቸውን ይቻሉ ።
መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡ ይመለስ ፡፡
የዳኞች አምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
You must login to view the entire document.