የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፲፬ አዲስ አበባ ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፲፪ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የደቡብ ዩኒቨርሲቲን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት | Council of Ministers Regulations No. 62/1999 ገጽ ፩ሺ፪፻፮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፪ ፲፱፻፲፪ የደቡብ ዩኒቨርሲቲን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱የዝጊ አንቀጽ ፩ መሠረት ይህን አውጥቷል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የደቡብ ዩኒቨርሲቲን ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፪ ፲፱፻፲፪ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ፡ ፩ . “ መንግሥት ” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ነው ፡፡ ፪ “ ቦርድ ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ ፮ መሠረት የተቋ ቋመው የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ነው ፡፡ “ ጉባዔ ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጸ ፲ መሠረት የተቋ ቋመው የዩኒቨርሲቲው ጉባዔ ነው፡ ፬ . “ የአካዳሚክ ሠራተኛ ” ማለት በማስተማር ወይም በምርምር ተግባር ላይ የተሠማራ ሠራተኛ ነው፡ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ዝሸ b ገጽ ፩ሺ፪የጊ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ 0 ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም ፭ . “ ፕሬዚዳንት ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ ፯ መሠረት የሚሾም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ነው፡ ፮ . “ ዩኒቨርሲቲ ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ ፫ መሠረት የተቋቋመው የደቡብ ዩኒቨርሲቲ ነው፡ ፫ . መቋቋም ደቡብ ዩኒቨርሲቲ ( ከዚህ በኋላ “ ዩኒቨርሲቲው ) ራሱን | 3 . የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ ዩኒቨርሲቲው የሚከተሉት የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞችን ያካትታል፡ ሀ ) አዋሳ እርሻ ኮሌጅ፡ ለ ) ወንዶ ገነት የደን ኮሌጅ፡ ሐ ) ዲላ የመምህራን ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፡ መ ) ወደፊት በቦርዱ የሚቋቋመ ሌሉች ፋኩልቲዎችና ኮሌጆች ። • የዩኒቨርሲቲው ተጠሪነት ለትምህርት ሚኒስቴር ይሆናል ። ዩኒቨርሲቲው የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡ ፩ ዕውቀትን ማዳበር፡ ማስፋፋትና ማስተላለፍ፡ ፪ ከዘር፡ ከብሔር፡ ካዖታ ፡፡ ከሃይማኖትና ከመሳሰሉት አድል ዖዎች ነፃ የሆነ በመከባበር፡ መተማመን፡ መተሳሰብና መቻቻል ላይየተመሠረተና ሁለንተናዊ ስብዕናን የሚያበ ለዕግና የሰው ልጅ ክቡርነትን የሚያጠናክር ትምህርት መስጠት፡ የሥራ ክቡርነትንና የኅብረተሰብ ብልዕግናን የሚያ ራምድ አስተሳሰብ እንዲሰርጽ ማድረግ፡ ፬ . የኢትዮጵያን ሕዝብ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማፋጠን በሳይንስ በቴክኖሎጂ፡ በሥነ ጥበባትና በልዩ ልዩ ሙያዎች የሠለጠኑ፡ ኅብረተሰብን በሚገባ ሊያገ ለግሉ የሚችሉ ሰዎች ማፍራት፡ በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች የኅብረተሰቡን ችግር ለመፍታት የሚረዳ ጥናትና ምርምር ማካሄድ፡ ጠቃሚ ውጤቶችን ማሠራጨት፡ የክልሉን ሕዝብም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማፋጠን የሚረዱ ሙያዊ ግልጋ ሎቶች ማበርከት፡ ፯ የአገልግሎት ክፍያን በመቀበል የምክርና ሥልጠና አገል ግሎት መስጠት ። ፭ የዩኒቨርሲቲው ሥልጣንና ተግባር ዩኒቨርሲቲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡ ፩- ፋኩልቲዎች፡ ኮሌጆችና ሌሎች የትምህርትና የምርምር ተቋሞች ማቋቋምና ማካሄድ፡ ፪ የቅድመ ምረቃና የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም መቀየስና ሥራ ላይ ማዋል፡ የምስክር ወረቀት፡ ዲፕሎማና ዲግሪእንዲሁም ለከፍተኛ ውጤትና አስተዋጽኦ አካዳሚክ ሜዳይ ሽልማትና ማዕረግ መስጠት፡ ፬ . ሴሚናሮች ወርክሾፖችና ሲምፖዚየሞችን ማዘጋጀትና ማካሄድ፡ ገጽ ፩ሺ፪፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ 0 ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፺፪ ዓ.ም የአገልግሎት ክፍያ በመቀበልና በገበያ ውስጥ በመግባት የማማከርና የሥልጠና አገልግሎት መስጠት፡ በሀገሪቱ ውስጥና በሌሎች ሀገሮች ከሚገኙ አቻ ዩኒቨር ሲቲዎች፡ የምርምር ተቋሞችና ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ጋር ግንኙነት መመሥረት፡ ጊ የትምህርት መጽሔቶችና ማቋቋምና ማሠራጨት፡ ፰ የንብረት ባለቤት የመሆን፡ ውል የመዋዋል፡ በስሙ የመክሰስና የመካሰስ፡ ዓላማውን የሚያራምዱ ሌሎች ተግባሮችን ማከናወን ። ክፍል ሁለት ስለዩኒቨርሲቲው የፖሊሲና የሥራ አስፈጻሚ አካላት ፮ ስለዩኒቨርሲቲው ቦርድ መቋቋም ፩ ዩኒቨርሲቲው በመንግሥት የማ ሙ አንደ ሊቀመን በርና ቁጥራቸው እንደ አስፈላጊነቱ የሚወሰን አባላት የሚገኙበት ቦርደ ይኖረዋል ። ቦርዱ የራሱ ፀሐፊ ይኖረዋል ። የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡ ፩ . የዩኒቨርሲቲውን የአካዳሚክና የአስተዳደር አጠቃላይ ፖሊሲ ያወጣል ከመንግሥት ፖሊሲዎችና ሕጎች ጋር በተገናዘበ መልኩ ይወስናል፡ ፪ . የዩኒቨርሲቲውን አደረጃጀት ይወስናል፡ ፫ ዩኒቨርሲቲው ወደፊት የሚደራጅበትንና የሚተዳደር በትን ቻርተር እንዲዘጋጅ በማድረግ ለመንግሥት ያቀርባል፡ ፬ . የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያፀድቃል፡ ፭ . የዩኒቨርሲቲውን ዕቅድና በጀት ለመንግሥት አቅርቦ ያስፀድቃል፡ ፮ የዩኒቨርሲቲውን ም ፕሬዚዳንቶች ሹመት ለትምህርት ሚኒስቴር አቅርቦ ያስጸድቃል፡ ጊ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ሠራተኞች የሚቀጠሩበ ትንና የሚተዳደሩበትን ሁኔታ የሚወስን የውስጥ አስተ ዳደር ደንብ ከመንግሥት ፖሊሲዎችና ሕጎች ጋር በማገናዘብ ያወጣል፡ ፰ ዩኒቨርሲቲውን በሚመለከት በማንኛውም የዩኒቨር ሲቲው አካል ወይም በዩኒቨርሲቲው በተሰጠ ውሳኔ የሚቀርቡ ኣቤቱታዎችን መርምሮ ውሣኔ ይሰጣል፡ ፱ ዩኒቨርሲቲው ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር የትምህርት ተቋማት ጋር የሚያደርጋቸውን የአካዳሚክ ስምምነቶች መርምሮ ያፀድቃል፡ ፲ የዩኒቨርሲቲው መለያ ምልክት የሚሆነውን ዓርማ ያጸደቃል፡ ፲፩ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ይወስናል፡ ፲፪ • ዩኒቨርሲቲው የሚያስከፍላቸውን ክፍያዎች በመን ግስት በዐደቀው መመሪያ መሠረት ይወስናል፡ ፲ - የዩኒቨርሲቲውን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል ። ን ብርዱ ሃሳብ ገጽ ፩ሺ፪፻፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም ፰ . የዩኒቨርሲቲው ጉባዔ ( ሴኔት ) መቋቋም ፩ . ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አባላት የያዘ የዩኒቨርሲቲው ጉባዔ ይቋቋማል፡ ሀ ) የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ለ ) የዩኒቨርሲቲው ም / ፕሬዚዳንቶች ሐ ) የየፋኩልቲው ዲኖች መ ) የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ሠ ) በተቋሙ የአካዳሚክ ሠራተኞች የሚመረጡ ሁለት ወኪሎች ረ ) ሁለት የተማሪዎች ተወካዮች ቦርዱ የሚሰይማቸው አግባብነት ያላቸው ሌሎች የዩኒቨርሲቲው አካላት ፪ . የጉባዔው ተጠሪነት ለቦርዱ ይሆናል ። ፬ . የጉባዔው ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚያወጣው አጠቃላይ መመሪያ እንደተጠበቀ ሆኖ ጉባዔው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡ ፩ . የዩኒቨርሲቲውን የትምህርት ካሌንደር ያጸድቃል፡ ፪ • የዩኒቨርሲቲውን ልዩ ልዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ያጸደቃል፡ ፫ ዲግሪዎች፡ ዲፕሎማዎችና የምስክር ወረቀቶች እንዲሁም ሜዳይና ሽልማቶች የሚሰጡበትን ሁኔታ ይወስናል፡ የተማሪዎች አቀባበልን፡ የትምህርት ደረጃ አወሳሰንን፡ የዲሲፒሊን ጉዳዮችንና ምረቃን የሚመለከቱ መመዘኛ መስፈርቶችን ያወጣል፡ በነዚህምጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፡ ፭ : አጠቃላይ የፈተና አሰጣጥና ደረጃዎች አቅጣጫዎችን ይወስናል፡ ፮ የዩኒቨርሲቲውን የአካዳሚክ ሠራተኞች ቅጥር መርምሮ ያጸድቃል፡ ፯ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጥ ያቀርባል፡ ፰ ዩኒቨርሲቲው የሚያስከፍላቸውን ክፍያዎች እንዲወስን ለቦርዱ ሃሳብ ያቀርባል፡ ፬ . የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ይወስናል፡ በቦርዱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። ፲ . የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንትና ም ፕሬዚዳንቶች ሹመትና ተጠሪነት ፩ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት በመንግሥት ይሾማል፡ ተጠሪ ነቱም ለቦርዱ ይሆናል ። ፪ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶች በዚህ ደንብ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ይሾማሉ፡ ተጠሪነታ ቸውም ለፕሬዚዳንቱ ይሆናል ። ፲፩ . የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ሥልጣንና ተግባር የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የዩኒቨርሲቲው ዋና መሪና አስፈጻሚ ሆኖ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡ ፩ የዩኒቨርሲቲውን ሥራ በበላይነት ይመራል፡ ያስተዳ ድራል፡ ይቆጣጠራል፡ በቦርዱና በጉባዔው የተላለፉ ውሳኔዎች ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል፡ ገጽ ፩ሺ፪፻፲ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፱ ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም . Federal Negarit Gazeta No.14 22 December , 1999– Page 1210 ፫ . የዩኒቨርሲቲውን የአካዳሚክ ሠራተኞች ቦርዱ በሚያ ወጣው መተዳደሪያ ደንብና መንግሥት ባጸደቀው የደመወዝ ስኬል መሠረት ይቀጥራል፡ ያስተዳድራል፡ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን የአስተዳደር ሠራተኞች በመንግሥት ሠራተኞች ሕግ መሠረት ይቀጥራል፡ ያስተዳድራል፡ ፬ . የዩኒቨርሲቲውን ዓመታዊ ዕቅድና በጀት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል፡ ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል፡ ፭ . በቦርዱ ሲፈቀድ በዩኒቨርሲቲው ስም የሚደረጉ ማናቸ ውንም ስምምነቶችንና የውል ሰነዶች ይፈርማል፡ ፮ ዩኒቨርሲቲው ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ሁሉ ዩኒቨርሲቲውን ይወክላል፡ – በዩኒቨርሲቲው ስም የባንክ ሂሳብ እንዲከፈትና እንዲን ቀሳቀስ ያደርጋል፡ ስለዩኒቨርሲቲው የሥራ እንቅስቃሴ ለቦርዱ በየሦስት ወሩ ሪፖርት ያቀርባል፡ • እንደአስፈላጊነቱ፡ ሥልጣኑን በውክልና ይሰጣል፡ በቦርዱና በጉባኤው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። ፲፪ . ስለዩኒቨርሲቲው ም ፕሬዚዳንት ሥልጣንና ተግባር ፩ . የዩኒቨርሲቲውም ፕሬዚዳንቶች በዩኒበርሲቲው ፕሬዚ ዳንት በሚሰጣቸው መመሪያ መሠረት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩዋቸዋል፡ ሀ ) የዩኒቨርሲቲውን ሥራ በሚመለከት የዩኒቨርሲ ቲውን ፕሬዚዳንት ያማክራሉ፡ ይረዳሉ ፡፡ ለ ) ለእነርሱ ተጠሪ የሆኑ የሥራ ክፍሎችን ሥራ ይቆጣጠራለ፡ በቦርዱና በጉባዔው የተላለፉ ውሣ ኔዎችና መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላለ፡ ሐ ) በቦርዱ፡ በጉባዔውና በፕሬዚዳንቱ ተለይተው የሚሰጧቸውን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናሉ፡ ፪ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት በማይኖርበት ጊዜ የዩኒቨር ሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም ፕሬዚዳንትፕሬዚዳንቱን ተክቶ የዩኒቨርሲቲውን ሥራ ይመራል፡ ያስተባብራል ። • የዩኒቨርሲቲው ሌሎች ኣካላት የዩኒቨርሲቲው ልዩ ልዩ ፋኩልቲዎች፡ የትምህርትና የምርምር ክፍሎች አመሠራረትና አሠራር እንዲሁም የአመራር አካላት አሰያየም በቦርዱ ይወሰናል ። ክፍል ሦስት ልዩ ልዩ ፲፬ . በጀት የዩኒቨርሲቲው በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል፡ ሀ ) ከመንግሥት ከሚመደብለት በጀት፡ ለ ) ዩኒቨርሲቲው ከሚሰበስባቸው የአገልግሎት ክፍያዎች፡ እና ሐ ) ከሌሎች ምንጮች ። ፲፭ የሂሣብ መዛግብት ፩ ዩኒቨርሲቲው የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ . የዩኒቨርሲቲው የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ገጽ ፩ሺ፪፻፲፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፱ ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፵፪ ዓ ም • Federal Negarit Gazeta No.14 22 December , 1999– Page 121 1 ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች ይህን ደንብ የሚቃረኑ ደንቦችና መመሪያዎች ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ። ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ