የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፴፯ አዲስ አበባ የካቲት ፪ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፵፯ ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ከኩዌት መንግሥት ጋር የተደረገ የአየር ትራንስፖርት አገል ግሎት ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ . ገጽ ፬፻፳፭ አዋጅ ቁጥር ፩፻፯ ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኩዌት መንግሥት መካከል የተደረገውን የአየር አገልግሎት ስምምነት ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኩዌት መንግሥት መካከል እ.ኤ.አ ኦክቶበር ፳፮ ቀን ፲፱፻፲፰ ኩዌት ላይ በመፈረሙ ፣ ስምምነቱ ሥራ ላይ የሚውለው ተዋዋዮቹ አገሮች ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መዋዋልና ተፈጻሚ ማድረግን በተመለከተ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቶቻቸው መፈጸማቸውን በዲፕሎማቲክ መስመሮች በመጨረሻ ከተገላለጹበት ወር የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እንደሚሆን በስምምነቱ ውስጥ የተመለከተ በመሆኑ ፤ ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት ፪ ቀን ፲፱፻፵፩ዓ.ም . ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፲፪ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ « ከኩዌት መንግሥት ጋር የተደረገ የአየር ትራንስ ፖርት አገልግሎት ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፵፯ ፲፱፻፲፩ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፬፻፷፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፯ የካቲት ፪ ቀን ፲፱፵፩ ዓም . Federal Negarit Gazeta – ፪ ስምምነቱ ስለመጽደቁ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኩዌት መንግሥት መካከል እኤአ ኦክቶበር ፳፮ ቀን ፲፱፻፶፰ ኩዌት ላይ የተፈረመው የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ስምምነት ጸድቋል ። ፫ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር ሥልጣን የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር ስምምነቱ በሥራ ላይ እንዲውል አስፈላጊውን እርምጃ የመውሰድ ሥልጣን በዚህ አዋጅ ተሰጥቶታል ። ፬ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም • ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ