×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
እዋጅ ቁጥር ሃረ/ የሣዚ ዓ.ም ሊሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትንና ለንብረት ካሣ የማhፊልበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የመሬት ይዞታ እንዲለቀቅ ሲደረግ ለባለይዞታው { WHEREAS , it has becomie necessary to define the የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አሥራአንደኛ ዓመት ቁጥር በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኣዲስ ኣበባ- ሐምሌ ፰ ቀን ፲ህየ ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፫ / ፲ህየን፯ ዓ.ም ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትንና ለንብረት ካግ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ.ገጽ ፫ሺ፩፻፳፬ ኣዋጅ ቁጥር ፬፻፲፭ / ፲፱፻፵፯ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትንና ለንብረት ካሣ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ መንግሥት ለሕዝብ አገልግሎት ለሚያከናውና ቸው የልማት ሥራዎች መሬትን መጠቀመ አስፈላጊ ስለሆነ ፣ የአገሪቱ እያደጉና የነዋሪዎችም ቁጥር እየጨመረ በመሄዱ በከተሞቹ ፕላን መሠረት ለመኖሪያ ቤት ግንባታ ፣ ለመሠረተ ልማት ፣ ለኢንቨስትመንትና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውል የከተማ መሬትን መልሶ ማልማት አስፈላጊ በመሆኑ ፣ እንዲሁም } their respective plans as well as preparation and provision of በገጠር ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች መሬት አዘጋጅቶ ማቅረብ በማስፈለጉ ፣ የሚከፈለውን ካሣ ለመተመን እንዲቻል ግምት ውስጥ in determining compensation to መግባት የሚገባቸውን መሠረታዊ መርሆዎች ለይቶ | landholding has been expropriated ; መወሰን በማስፈለጉ ፣ ካሣውን የመተመን ሥልጣንና የመክፈል ኃላፊነት ያሰባቸውን አካላት በግልጽ ለይቶ መወሰን ሰግስፈለጉ ፣ የፌዴራል መንግሥቱ የመሬት አጠቃቀም ሕግ | empowers the Federal Government to enact laws የማውጣት ሥልጣን እንዳለው በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ | regarding the utilization of land and it is deemed ፲፩ / ፭ / ሰመደንገጉና ለሕዝብ ጥቅም የሚለቀቅ ንብረትን necessary በሚመለከት በቅድሚያ ተመጣጣኝ ካሣ እንዲከፈል በሕገ | requirement of advance payment of compensation for መንግሥቱ አንቀጽ ፵ / ፰ / የተቀመጠውን መሠረተ ሃሳብ | private property expropriated for public purpose as በመመርኮዝ በዝዘርዝር መደንገግ በማስፈለጉ ፣ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣ.ቁ ¥ ሺ ፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ሓምሌ ፰ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ታውጇል ፡፡ ክፍል አንድ አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትንና ለንብረት ካሣ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር ፬፻፵፭ / ፲፱፻፮፯ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ፡፡ ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ / ካሣ ” ማለት የመሬት ይዞታውን እንዲለቅ ለሚወሰንበት ባለይዞታ በመሬቱ ላይ ለሰፈረው በዓይነት በገንዘብ በሁለቱም የሚከፈል ክፍያ ነው ፣ ፪ / “ ክልል ” ማለት በሕገ - መንግሥቱ አንቀጽ ፵፯ የተመለከተው ማንኛውም ክልል ሲሆን የአዲስ የድሬዳዋ አስተዳደርችን ይጨምራል ፣ ፫ / “ የመሬት ባለይዞታ ” እንዲለቀቅ በሚወሰነው መሬት ላይ ሕጋዊ የባለይዞታነት መብት ያለው ሆኖ በመሬቱ ላይ ንብረት ያፈራ ግለሰብ ፣ የመንግሥት ወይም የግል ድርጅት የሰውነት መብት የተሰጠው ማንኛውም አካል ነው ፣ ፬ / “ የከተማ አስተዳደር ” ማለት በሚመለከተው መንግሥታዊ የከተማ አስተዳደር ሥልጣንና ተግባር የተሰጠው ኣካል ነው ፣ ፭ / “ የሕዝብ በተዘዋዋሪ ያላቸውን ተጠቃሚ ነት ለማረጋገጥና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን በቀጣይነት ለማጉልበት ኣግባብ ያለው አካል በከተማ መዋቅራዊ ፕላን ወይም በልማት እቅድ መሠረት የሕዝብ ጥቅም ብሎ የሚወስነው ነው ፣ ፮ / “ የአገልግሎት መስመር ” ማለት ለሕዝብ ጥቅም ሲባል እንዲለቀቅ በሚፈለግ መሬት ላይ ወይም ውስጥ ቀደም ሲል የተዘረጋ የውሃ ፣ የፍሳሽ ኤሌክትሪክ ወይም የስልክ መስመር ነው ፣ ገ፡ ፫ሺ፩፻፳፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ሓምሌ ፮ ቀን ፲፱፻፯ ዓ.ም ፯ / “ አስፈፃሚ መሥሪያ ቤት ” ማለት በራሱ ኃይል ወይም በሥራ ተቋራጭ አማካኝነት የልማት ሥራዎችን የሚያካሂዱ ወይም .. እንዲካሄዱ የሚያደርግ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም የልማት ድርጅት ነው ፡፡ ክፍል ሁለት የመሬት ይዞታን ስለማስለቀቅ መሬት የማስለቀቅ ሥልጣን ፩ / የወረዳ አስተዳደር በመንግሥት አካላት ፣ ባለሃብቶች ፣ በሕብረት ሥራ ማህበራት ወይም በሌሎች አካላት የተሻለ ልማት ሊካሄድበት ይገባል ብሎ ያመነበትን ወይም አግባብ ባለው የክልሉ ወይም የፌዴራል መንግሥት የበላይ አካል ለዚሁ ዓላማ እንዲውል የወሰነውን የገጠር ወይም የከተማ መሬት በቅድሚያ በዚህ አዋጅ መሀረት ካሣ እንዲከፈል በማድረግ የማስለቀቅ ሥልጣን አለው ፡፡ ፪ / የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / ድንጋጌ ቢኖርም በሊዝ አዋጅና ደንብ መሠረት የገባውን ውል መንግሥት ለሚያካሂደው የልማት ሥራ አስፈላጊ ካልተገኘ በቀር መሬት በሊዝ የተከራየ ሰው አይወሰድበትም ፡፡ መሬት የማስለቀቂያ ትዕዛዝን ስለማሳወቅ ፩ / የወረዳው ወይም የከተማው አስተዳደር በዚህ ኣዋጅ ኣንቀጽ ፫ መሠረት መሬት እንዲለቀቅ ሲወስን መሬቱ የሚለቀቅበትን ጊዜ በመጥቀስና የካሣውን ግምት በመግለጽ የማስለቀቂያ ትዕዛዝ ለባለይዞታው በጽሁፍ ይሰጣል ፡፡ ፪ / በዚህ አንቀጽ / ፩ / መሠረት የሚሰጠው የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመመሪያ ይወሰናል ፣ ሆኖም በማንኛውም ሁኔታ ከ 90 ቀናት ያነሰ ሊሆን አይችልም ፡፡ ፫ / በዚህ አንቀጽ / ፩ / መሠረት ማስጠንቀቂያ የደረሰው ባለይዞታ ካሣ ከተከፈለው ቀን ወይም ካሣውን ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆነ ደግሞ ካሣው እንደአግባቡ በወረዳው በከተማው አስተዳደር ስም በዝግ የባንክ ሂሳብ ከተቀመጠበት ቀን ጀምር በ፲ ቀናት • ውስጥ ለወረዳው ለከተማው አስተዳደር ማስረከብ አለበት ፡፡ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 9 ሐምሌ ፳ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፫ / ድንጋጌ ቢኖርም በሚለቀቀው መሬት ላይ ሰብል ፣ ቋሚ ተክል ባለይዞታው የማስለቀቂያ ትዕዛዝ በደረሰው በ፴ ቀናት ውስጥ መሬቱን ለወረዳው ወይም ለከተማው አስተዳደር ማስረከብ አለበት ፡፡ የማስለቀቂያ ትእዛዝ የደረሰው የመሬት ባለይዞታ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፫ / ወይም / ፬ / በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ መሬቱን ለማስረከብ ፈቃደኛ ካልሆነ የወረዳው ወይም የከተማው አስተዳደር መሬቱን ለመረከብ የፖሊስ ኃይል መጠቀም ይችላል ፡፡ ጅ የአስፈፃሚው መሥሪያ ቤት ኃላፊነት አስፈፃሚው መሥሪያ ቤት የሚከተሉት ኃላፊነቶች ይኖሩታል ፣ የሚፈልገውን የሚገኝበትን ትክክለኛ ስፍራ የሚያሳይ መረጃ ቢያንስ ሥራው ከመጀመሩ ከአንዱ ዓመት በፊት አዘጋጅቶ ለማስለቀቅ ሥልጣን ላላቸው አካላት የመላክና የማስፈቀድ ፣ ይዞታቸውን እንዲለቁ ለተደረጉ ባለይዞታዎች በዚህ አዋጅ መሠረት ተገቢውን ካሣ የመክፈል ፡፡ ፮ . የአገልግሎት መስመሮች ስለሚነሱበት ሥርዓት የፌዴራል ወይም የክልል መንግሥታዊ መሥሪያ ቤት ወይም የልማት ድርጅት ንብረት የሆነ የአገልግሎት ያረፈበት የሚለቀቅ ሆኖ ሲገኝ መሬቱን የሚፈልገው አካል የሚገኝበትን ትክክለኛ በማመልከት ባለቤት ለሆነው አካል መስመሩ እንዲነሳ ጥያቄውን በጽሑፍ ያቀርባል ፡፡ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / መሠረት ጥያቄ የደረሰው አካል የሚነሣውን ንብረት ለመተካት የሚያስፈልገውን ተገቢ ካሣ በመተመን ዝርዝሩን ጥያቄው በደረሰው በ፴ ቀናት ውስጥ ለጠያቂው ይልካል ፡፡ የአገልግሎት መስመሩ እንዲነሳለት የጠየቀው አካል በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፪ / መሠረት ግምቱ በደረሰው በ፴ ቀናት ውስጥ የንብረቱን ግምት ለባለንብረቱ፡ ይከፍላል ፡፡ ባለንብረቱ በተፈጸመለት በኋ ቀናት ውስጥ ካሣ የተከፈለበትን የአገልግሎት መስመር አጠናቆ በማንሳት መሬቱን ይለቃል ፡፡ i ሽ እ፻፳፰ የማጓጓገርና መጮ በመር እና ገርገር ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፫ ሐምሌ ፳ ቀን ፲ህየን፯ ዓ.ም ክፍል ሦስት የካሣ አወሳሰን ፯ . የካሣ መሠረትና መጠን የመሬት ይዞታውን እንዲለቅ የሚደረግ ባለይዞታ ለሚገኘው ንብረት እንዲሁም ላደረገው ማሻሻል ካሣ ይከፈለዋል ፡፡ በሚለቀቀው የመሬት ይዞታ ላይ ለሚገኝ ንብረት የሚከፈል ንብረቱን በአለበት ለመተካት የሚያስችል ይሆናል ፡፡ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፪ / የተቀሰው ካሣ የሚከፈለው ለከተማ ነዋሪ በሚሆንበት ጊዜ በማንኛውም የሚመለከተው ባወጣው ስታንዳርድ መሠረት ኣንዱ ክፍል የቁጠባ ቤት ሊያሠራ ከሚችል ያነሰ መሆን የለበትም ፡፡ በመሬት ላይ ለተደረገ ቋሚ መሻሻል የሚከፈል ካሣ በመሬቱ ላይ የዋለውን ገንዘብና የጉልበት ዋጋ የሚተካ ይሆናል ፡፡ ከሚገኝበት መሬት ወደሌላ መሬት በመዛወር እንደገና ሊተከልና እንደነበረ አገልግሎት ለመስጠት ለሚችል ንብረት ንብረቱን የማንሻ ፣ የመትከያ ወጪ የሚሸፍን ካሣ ይከፈላል ፡፡ የተለያዩ ንብረቶች ካሣ አፈፃፀም በደንብ ይወሰናል ፡፡ ፰ . ስለመፈናቀያ ካሣ ፩ / የመሬት ይዞታውን በቋሚነት እንዲለቅ የሚደረግ የገጠር መሬት ባለይዞታ መሬቱን እንዲለቅ ከመደረጉ በፊት በነበሩት አምስት ዓመታት ያገኘው አማካይ ዓመታዊ ገቢ በ፲ ተባዝቶ በዚህ ኣዋጅ ኣንቀጽ ፯ ከሚከፈለው ካሣ በተጨማሪ የመፈናቀያ ካሣ ይከፈለዋል ፣ የመሬት ይዞታውን ለተወሰነ ጊዜ እንዲለቅ ለሚደረግ መሬት ባለይዞታ ባለይዞታዎች እንዲለቁ ከመደረጉ በነበሩት አምስት ዓመታት ያገኙት አማካይ ዓመታዊ ገቢ መሬቱ እስከሚመለስ ድረስ ባለው ጊዜ ታስቦ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ መሠረት ከሚከፈለው ካሣ በተጨማሪ የመፈናቀያ ካሣ ይከፈላቸዋል ፡፡ ሆኖም ይህ ክፍያ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / መሠረት ከሚከፈለው ካሣ መብለጥ የለበትም ፡፡ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵ ሐምሌ ፳ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም ፫ / ተመጣጣኝ ገቢ የሚያስገኝና በቀላሉ ሊታረስና ምርት ሊያስገኝ የሚችል ተተኪ መሬት ለባለይ ቦታው የተገኘለት መሆኑን የወረዳው አስተዳደር ሲያረጋግጥ ፣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / እና / ፪ / የተጠቀሰው ክፍያ ባለይዞታው መሬቱን እንዲ ለቅ ከመደረጉ በፊት በነበሩት አምስትዓመታት ያገ ኘው አማካይ ዓመታዊ ገቢውን የሚያህል ብቻ ይሆናል ፡፡ ፬ / በዚህ አዋጅ መሠረት የመሬት ይዞታውን እንዲለቅ ለተደረገ የከተማ ነዋሪ ለንብረቱ ከሚከፈለው ካሣ በተጨማሪ ፣ ሀ / መጠነ : በከተማው አስተደደር የሚወሰን የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ምትክ የከተማ መሬት ይሰጠዋል ፣ ለ / የፈረሰው የመኖሪያ ቤት የአንዱ ዓመት ኪራይ ግምት ተሰልቶ የመፈናቀያ ካሣ ይከፈለዋል ወይም የከተማው አስተዳደር ንብረት የሆነ ተመጣጣኝ ዓመት ያለኪራይ እንዲኖርበት ይሰጠዋል ፡፡ ፭ / የፈረሰው ቤት የመሥሪያ ቤት ከሆነ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፬ / የተደነገገው በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈፃሚ ይሆናል ፡፡ ፮ / በሊዝ የተሰጠን መሬት የሊዝ ዘመነ ከማለቁ በፊት እንዲለቀቅ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ እና በዚህ አንቀጽ መሀ ) ረት ከሚከፈለው ካሣ በተጨማሪ የሊዝ ባለይዞ ታው ለቀረው የሊዝ ዘመን የሚጠቀምበት ተመ ጣጣኝ ምትክ መሬት ይሰጠዋል ፡፡ በምትክነት የሚሰጠው መሬት ኪራይ ከተለቀቀው መሬት ኪራይ ያነሰ ከሆነም መሬቱን ረዘም ላለ ጊዜ እን ዲጠቀምበት በማድረግ ይካካስለታል ፡፡ ወይም ባለ ይዞታው መሬቱን መረከብ ከፈለገ የቀረው የሊዝ ዘመን ኪራይ ተሰልቶ እንዲመለስለት ይደረጋል ፡፡ ፯ / በዚህ አንቀጽ መሠረት የሚከፈለው የመፈናቀያ ካሣ ገርገር አፈፃፀም በደንብ ይወሰናል ፡፡ ፱ . ንብረት ስለመገመት እንዲለቀቅ ሰሚፈለግ መሬት ላይ የሚገኝ ንብረት ካሣ የሚወጣውን አገር አቀፍ ቀመር በማድረግ በተመሰከረላቸው ወይም የመንግሥት ተቋማት ወይም ግለሰብ አማካሪዎች ይገመታል ፡፡ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / መሠረት የካሣውን ለመገመት የሚቻልበት አቅም መፈጠሩን የፈዴራል ሚኒስቴር የፌዴራልና መንግሥት በመመካከር እስኪያረጋግጥ የሚገመተው በዚህ አዋጅ አንቀጽ / 1 / መሠረት በሚቋቋመ ኮሚቴዎች እና በዚህ አዋጅ አንቀጽ / ፯ / መሠረት በአገልግሎት መስመር ባለቤት ይሆናል ፡፡ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 1 ሓምሌ ፮ ቀን ፲፱የገጊ ዓ.ም ፲ የንብረት ገማች ኮሚቴዎች ፩ / የሚለቀቀው መሬት የሚገኘው በገጠር ሲሆን የሚገመተው የወረዳው አስተዳደር በሚያቋቁመውና ከአምስት ያልበለጡ ባሉት ኮሚቴ ይሆናል ፡፡ ፪ / የሚለቀቀው መሬት የሚገኘው በከተማ ውስጥ ሲሆን የሚገመተው የከተማው አስተዳደር በሚያቋቁመውና ተገቢው መያ ያላቸው አባላት በሚገኙበት ኮሚቴ ይሆናል ፡፡ ፫ / ከሚለቀቀው መሬት የሚነሳው ንብረት የተለየ እውቀትና ልምድ የሚጠይቅ ንብረት ሲሆን የሚገመተው የከተማው ኣስተዳደር የሚሰይማቸው ባለመያዎች በሚገኙበት የተለየ ኮሚቴ ይሆናል ፡፡ ፬ / በዚህ አንቀጽ መሠረት የሚቋቋመት የንብረት ገማች ኮሚቴዎች ሥራቸውን የሚያከናውነበት የአሠራር ሥረርዓት በመመሪያ ይወሰናል ፡፡ ፲፩ . ካሣን አስመልክቶ ስለሚቀርብ አቤቱታና ይግባኝ የመሬት ነክ አስተዳደራዊ አካል ባልተቋቋመባቸው ከተሞች የካሣ መጠንን አስመልክቶ አቤቱታ የሚቀርበው ሥልጣን ላለው መደበኛ ፍርድ ቤት ይሆናል ፡፡ ፪ / የከተማ መሬት ይዞታውን እንዲለቅ የሚደረግ ባለይዞታ የተወሰነለትን በሚመለከት ቅር ከተሰኘ አቤቱታውን በከተማው አስተዳደር ለተቋቋመው የመሬት ነክ አቤቱታ ሰሚ ኣስተዳደራዊ አካል ሊያቀርብ ይችላል ፡፡ ፫ / በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፪ / የተጠቀሰው አካል የሚቀርብለትን አቤቱታ ከመረመረ በኋላ በሚያወጣው በሚወሰነው ይሰጣል ፣ የሚሰጠውን ውሳኔ ለተከራካሪ ወገኖች በጽሁፍ ያሳውቃል ፡፡ ፬ / በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / እና / ፪ / መሠረት በተሰጠው ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ተከራካሪ ወገን እንደአግባቡ ለመደበኛው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ወይም ለከተማ ነክ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን አንስቶ በ፴ ቀናት ውስጥ ይግባኝ ማቅረብ ይችላል ፡፡ ፍርድ የሚሰጠው የመጨረሻ ይሆናል ፡፡ * ኣግስፈጸም እንዲችሉ የቴክኒክና ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ሓምሌ ፳ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም ፭ / በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፬ / የተመለከተው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ አመልካቹ ይግባኝ ሲጠይቅ የውሳኔውን ግልባጭ አዘጋጅቶ ለመስ ጠት የሚወስደውን ጊዜ አይጨምርም ፡፡ ፮ / በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፬ / መሠረት ይግባኝ የሚያቀርብ የመሬት ይዞታ ማስለቀቂያ ትእዛዝ የደረሰው ባለይዞታ ሊታይለት የሚችለው እንዲለቀቅ ትእዛዝ የተሰጠበትን መሬት ለከተማው ወይም ለወረዳው አስተዳደር ማስረከቡን የሚያረጋግጥ ከይግባኝ አቤቱታው ጋር አያይዞ ካቀረበ ብቻ ይሆናል ፡፡ ፯ / የካሣ መጠንን አስመልክቶ በሚቀርብ አቤቱታ ምክንያት የመሬት ማስለቀቅ ውሳኔ አፈጻጸም መዘግየት አይችልም ፡፡ ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፪ . የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሥልጣንና ተግባር የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ይህን አዋጅ በማስፈጸም ረገድ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፡፡ ፩ / የአዋጁ ድንጋጌዎች በሁሉም ክልሎች መከበራ ቸውን ይከታተላል ፣ ያረጋግጣል ፣ ፪ / ክልሎች አዋጁን የአቅም ግንባታ ድጋፍ ያደርጋል ፣ ፫ / በዚህ አዋጅ መሠረት ለሚወሰን ካሣ አገር አቀፍ የአተማመን ኣግባብ ካላቸው ሌሎች የፌደራል መንግሥቱ አካላት ጋር በመሆን ኣዘጋጅቶ ለሚኒስትርች ምክር ቤት በማቅረብ ያፀድቃል ፡፡ የወረዳው የከተማ አስተዳደሮች ኃላፊነት የወረዳና የከተማ አስተዳደሮች ይህን አዋጅ በማስ ፈጸም ረገድ የሚከተሉት ኃላፊነቶች ይኖራቸዋል ፣ ፩ / መሬት እንዲለቁ ለተደረጉ ባለይዞታዎች በዚህ አዋጅ መሠረት ተገቢውን ካሣ የመክፈል ወይም እንዲከፈል የማድረግና አቅም በፈቀደ መጠን የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ የማድረግ ፣ ሸ የብዙ ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፫ ሐምሌ ፭ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም ፪ / እንዲለቀቅ በሚወሰን መሬት ላይ የሚገኘውን ንብረት በሚመለከት መረጃ የመያዝ ፣ የሚያው መረጃ ዝርዝርና የአያያዙ ሁኔታ በመመሪያ ይወሰናል ፡፡ ፲፬ . ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ፩ / የሚኒስትርች ምክር ቤት ይህን አዋጅ በሚገባ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ደንቦችን ይችላል ፡፡ ፪ / ክልሎች የሚወጡ ደንቦችን በሚገባ ለማስፈጸም የሚያስ ፈልጉ መመሪያዎችን ሊያወጡ ይችላሉ ፡፡ ፲፭ የተሻሩና ተፈፃሚነት የማይኖራቸው ሕጉች ፩ / ለመንግሥት ሥራዎች መሬት የሚለቀቅበትንና ለንብረት የሚከፈልበትን ሁኔታዎች ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር ፬፻፩ / ፲፱፻፶፮ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ፡፡ ፪ / ከዚህ ኣዋጅ ጋር የሚቃረን ማንኛውም ሕግ ፣ መመሪያ ወይም የተለመደ አሠራር በዚህ አዋጅ ውስጥ በተመለከቱት ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም ፡፡ ፲፮ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሐምሌ ፳ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል ፡፡ አዲስ አበባ ሐምሌ ፳ ቀን ፲፱፻፵፯ ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?